ከ20 አመት ስደት በኋላ ወደ ሀገሩ የመጣው የሞገድ ጋዜጣ አዘጋጅ እና የኢትዮ ሚዲያ ፎረም መስራቹ ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ አስገራሚ ታሪኩን ነግሮናል፡፡ “ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በደህንነት ከተመዘገቡ 23 ሺ ሰዎች መካከል የኔም ስም ነበረበት” የሚለው ጋዜጠኛው አቶ መለስ ዜናዊ ከሆስኒ ሙባረክ ጋር በሚስጥር ያደረጉትን ውል ይፋ በማድረጋችን መከራ ደርሶብናል ይላል፡፡ እንዲሁም በሞገድ ጋዜጣ ላይ አብረውት ይሰሩ ከነበሩት የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በምን ምክንያት እንደተለያዩ ያልተሰማ ታሪክ ያካፍለናል፡፡ ከአንዳፍታ እና ሸገር ታይምስ መጽሔት ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ ይመልከቱት::