ዐቢይ ዳያስፖራውን (ግዩራኑን) ለማለብ ለመዝረፍ የትረስት ፈንድ ኮሚቴ (የድጋፍ መዋጮ ደርግ) ማቋቋሙ ይታወሳል፡፡ የዚህ ኮሚቴ (ደርግ) ሰብሳቢ ደግሞ ፕሮ. (ሊጠ.) ኃይለማርያም ሆኖ መሾሙ ይተወቃል፡፡ እነ ታማኝ በየነም እንዳሉበት ይታወቃል፡፡ ታማኝ ዕድሜ ልኩን ዐቢይን ለማገልገል ቃል ገብቶ የለ??? አዎ! በዛ መሠረት እንግዲህ ሥራቸውን ለመጀመር መዘጋጀታቸውን ዛሬ አስታውቀዋል፡፡ ይሄንን ሲያደርጉ ግን ገንዘቡ ለምን ዓላማ ይዋል ብለው እየሰበሰቡ እንደሚልኩት ለማሳወቅ ይህችን አጭር ጽሑፍ ለመጻፍ ፈለኩ፡፡
ፕሮ. (ሊጠ.) ኃይለማርያምም ሆነ ታማኝ በየነን ወያኔን በመቃወማቸው ብዙ የሚታወቁ ሰዎች ናቸው፡፡ ሴረኛው ሸፍጠኛው አሻጥረኛው ወያኔ ዐቢይን “አል ማርያምየ የጠፋውን ታላቅ ወንድሜን ነውኮ የሚትመስለኝ!” እያስባለ ላከበት፡፡ አል ማርያም የተማረው ትምህርቱ ከዐቢይ “የጠፋብኝ ታላቅ ወንድሜ!” ከሚለው የማቄያ፣ የማጃጃያ፣ የማታለያ ቃል ከመጃጃል አልታደገውም አላዳነውም፡፡ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ፣ ያለምንም ምርመራና ጥርጣሬ ተንበረከከለት፡፡
ታማኝም እንዳያቹህት ያውም ተገፍቶ ወይም ተገልሎ እያለ ዓይኑን አፍጥጦ ሔዶ በግድ አቋጥሩኝ ብሎ ሔዶ ሕዝብ አስጩኾ በማስገደድ ቀርቦ ጫማ ስሞ ዕድሜ ልኩን ዐቢይን ለማገልገል ቃል በመግባቱ ለባለሟልነት ታጨና በዚሁ ኮሚቴ (ደርግ) ለመካተት በቃ፡፡
ይህ ሁለቱ ግለሰቦች የተንበረከኩበት ቀደም ሲል የነበረው ሁኔታ አይደለም የሚገርመው፡፡ ነገር ግን አሁን በዚህ ወቅት ዐቢይ በሸንጋይ ቃላት የሸፈነው ወያኔያዊ ገጽታው ወይም ማንነቱ ቡራዮ ላይ በኦሮሚያ ፖሊስና በጃዋር የተቀናጀ አረመኔያዊ ጥቃት ያን ሁሉ ፍጅት እንዲያደርሱ በማድረግ፣ አዲስ አበባም ላይ የአዲስ አበባን ወጣቶች በአደባባይ ከመረሸን ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ ማለትም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝና በሕገወጥ ምክንያቶች ማለትም በሕግ “ወንጀል ናቸው!” ተብለው ባልተደነገጉ ምክንያቶች “ጫት ቤት ሺሻ ቤት ተገኝታቹሀል!” በማለት እንዲሁም ማሳወቅ እንጅ ለሰልፍ ፈቃድ የመጠየቅ ሕጋዊ አሠራር በሌለበት ሁኔታ “ፈቃድ ባልተሰጠው ሰልፍ ተገኝታቹሃል!” በሚሉ ሕጋዊ መሠረት በሌላቸው ምክንያቶች በጅምላ እስከማፈስና ጦላይ እስከማጋዝ የደረሰ ግፍ በመፈጸም፣ መብታቸውን ለማስጠበቅ የሚንቀሳቀሱ ዜጎችን ሐሰተኛ የክስ ምክንያት በመፍጠር እስርና ወከባ እንደገና በማስቀጠል፣ የሕግ አካላት እንዳይከላከሉ በማድረግ የአዲስ አበባን መሬት በጠራራ ፀሐይ በወረራ የማዘረፍን የውንብድና ተግባር ያለአንዳች እፍረት በማስፈጸም ወዘተረፈ. ማንነቱ ግልጥ በሆነበት በዚህ ጊዜ ሰው እንዴት አይነቃም??? ምን ዓይነት ያፍዝዝ ያደንዝዝ ነው ያደረጉባቸው ሰዎቹን??? በተለይ ፕሮ. ኃይለማርያም በዚህ ደረጃ የተማረ ሰው እንዴት ማሰብ ማገናዘብ ይሳነዋል???
ዐቢይ በብዙኃን መገናኛ ቀርቦ “እኔነኝኮ ይሄንን ሁሉ አዝዠ የማስፈጽመው!” እንዲል ነው እንዴ የሚጠብቁት??? ቆይ ቆይ እነኝህ ቂሎች መለስን ሲቃወሙት የነበረው መለስ በብዙኃን መገናኛ ቀርቦ “እኔ እኮነኝ ተጋዳላዮቸን ዝረፉ ብየ የማዘርፋቹህ፣ ግደሉ አሰቃዩ ብየ መከራቹህን እንዲያሳዩዋቹህ የማደርገው!” ስላለ ነበር እንዴ በመለስ ላይ ስንፈርድ እሱን ስንኮንን ዝናወግዝ የነበረው???
ለነገሩ በዚህ ደረጃ ከሆነም ዐቢይ እንዲናገር የሚፈልጉት “የሕዝብ ተወካዮች” ላይ ቀርቦ ይሄንን በወጣቶች ላይ የተወሰደውን ሕገወጥ እርምጃ ያስፈጸመው እሱ መሆኑን በግልጽ ተናገረ አይደለም ወይ??? ታዲያ ከዚህ በላይ እነ ነፈዞ ምንድን ነው የሚፈልጉት???
ይሄን ሁሉ ግልጽ ዐቢይ በሸንጋይ ቃላት የደበቀውን ወያኔያዊ ማንነቱን የሚያሳዩ ነገሮች እያሉ አሁንም ቀደም ሲል በተጃጃሉበት መንፈስ ውስጥ ሆነው ትረስት ፈንድ ምንትስ እያሉ ገንዘብ የሚያሰባስቡት እኛን ለማስገደያ ለማስጨረሻ ነው ወይስ ለምንድን ነው???
ጃዋር መሪ በሆነበት የዐቢይ አሥተዳደር ገንዘብ ለዐቢይ አሥተዳደር መስጠት ወይም ማስገባት ማለት ለሜንጫ መግዣና ለኦነግ ሠራዊት ማስታጠቂያ ካልሆነ በስተቀር ጭንቅላት ያለውና ማሰብ የሚችል ሰው እንዴት ለታለመለት ዓላማ ይውላል ብሎ ያስባል??? ነው ወይስ ገንዘቡ ለዚህ የጥፋት ዓላማ እንደሚውል አውቀው ተስማምተውበት ነው???
እባካቹህ የምትቀርቧቸው ሰዎች እስኪ ቆም ብለው እንዲያስቡበት አሳስቧቸው??? በውጭ ሀገራት የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንም ለዚህ የድጋፍ መዋጮ (Trust fund) ድምቡሎ እንኳን ብትሆን እንዳትሰጡ አጥብቀን እናሳስባለን!!! የሚሰጥ ሰው ቢኖር እኛን ለማስገደያ ለማሳረጃ አስተዋጽኦ እንዳበረከተና የሀገር የሕዝብ ጠላት መሆኑን ይወቀው!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com