“በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች እንዲፈጠር እያደረገ ያለው አዴፓ ነው”
አቶ አብርሃ ደስታ
የዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት ሊቀ መንበር
“በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችና በህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ያለው አዴፓ ነው” ሲሊ የዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት ሊቀ መንበር አቶ አብርሃ ደስታ አስታወቁ።
አቶ አብርሃ ደስታ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጥይቅ ላይ እንደተናገሩት፤ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችና በህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ያለው አዴፓ መሆኑን አረና ገምግሟል፡፡
በአማራም ሆነ በኦሮሚያ ክልል የለውጥ መንፈስ እየታየ ሲሄድ አዴፓ ከስልጣን እንዳይባረር በመፍራት በትግራይና በክልሉ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ችግሮች እየፈጠረም መሆኑን የፓርቲው ሊቀ መንበር ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡
ሊቀ መንበሩ አክለው እንዳሉትም፤ በሁለቱ ክልሎች መካከል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችና በህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ያለው በአዴፓ የሚመራው የአማራ ክልል መንግስት ነው፡፡ ለችግሩም ዘላቂ መፍትሔን ለማምጣት የፌደራል መንግስት በሁለቱም ክልሎች የሚገኙ ወንድማማች ህዝቦች መካከል አለመግባባት እንዳይፈጠር ችግር ፈጣሪውን አካል እንዲታረም ሊያደርገው ይገባል፡፡