October 22, 2018 – Konjit Sitotaw
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እና ውይይት ተጠናቀቀ::
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ:-
* ከ20ውም የሚኒስቴር መ/ቤት የሚጠበቁ ያሏቸውን ዋና ዋና የውጤት አመልካቾችን ባጭሩ ገልጸው እነዚህ ተዘርዝረው በየሚኒስቴር መ/ቤቱ የ100 ቀናት ዕቅድ ውስጥ እንዲካተቱ አመራር ስጥተዋል::
የተዋሃዱ የሚንስቴር መ/ቤቶች ወይም ተጠሪዎች ወይም ሌላ የተልዕኮ ወይም የአደረጃጀት ለውጥ የተደረገባቸው ተቋማት ፈጥነው በማስተካከልና ለሰራተኞቻቸው በቂ ኦረንቴሽን በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስበዋል::
በቢሮና ንብረት ርክክብ ብዙ ጊዜ መባከን እንደሌለበትም አስገንዝበዋል::
ለምሳሌ:-
1) የሰላም ሚኒስቴር :-
* ሰላምና ደህንነትን የማረጋገጥ
* ብሔራዊ መግባባትን የማስፈን
* ግጭቶችን የመፍታትና የማስወገድ
* የዲሞክራቲክ ተቋማትን አሰራር የማዘመን
2) የመከላከያ ሚኒስቴር:-
* ጠላት የመከላከል ብቃትን የማሳደግ
* ብቃት ያለው የመከላከያ የሰው ኃይል የማዘጋጀት
* ባህር ኃይልን የማደራጀት
3) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር:-
* ከጎረቤት እንዲሁም ከሌሎች ስትራቴጂክ ከሆኑ አገሮች ጋር ወዳጅነትን የማጠናከር
* የዳያስፖራ ተሳትፎን በሙያም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ የማጠናከር
* ውጭ የሚኖሩ ዜጎችን መብት የማስከበር
* የአገሪቱን ገጽታ የመገንባት
* የዲፕሎማቶች እና የሌሎች ሙያተኞችን ስምሪትን የማሻሻል
4) የገንዘብ ሚኒስቴር
* የኃብት ምንጭን የማሳደግ
* ብድር የመክፈል አቅምን የማሻሻል: የኮሜርሺያል ብድር ወደ ኮንሴሽናል ብድር እንዲቀየር የመስራት
* ወደግል መዞር የሚገባቸውን ተቋትማት ህጉን ተከትሎ እንዲዛወሩ የማድረግ
* የዋጋ ንረትን /ግሽበትን የመቆጣጠር
5) ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
* የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ
* የህግና ፍትህ ሪፎርምን በብቃት የመምራት (የሚሻሻሉ ህጎችን ማሻሻልን ጨምሮ)
* የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት የማክበር: በህጉ መሰረትም እንዲታረሙ የማድረግ
6) ግብርና ሚኒስቴር
* ዘርፉ በርካታ ተግባራትን በመያዝ የተደራጀ በመሆኑ በአግባቡ በሚ/ር መ/ቤቱ ውስጥም ሆነ ከሌሎች ጋር አቀናጅቶ የመምራት
* የግብርና ዘርፉን ምርታማነት የማሻሻል:
* የማዳበሪያ: የምርጥ ዘርና ሌሎችም ግብዓቶችን በወቅቱና በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ:
የሚሉት በምሳሌ ደረጃ ተጠቃሽ ናቸው::
በመጨረሻም በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች እና ሰራተኞች የስራ ጊዜን በማይሻማ መልኩ ከየተልዕኮአቸው ጋር የተቃኘ ስልጠና ሊሰጥ እንደሚገባ ተገልጾ ስልጠናው ተጠናቋል::
መረጃውን ያገኘነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ የፌስቡክ ገፅ ነው፡፡