ራያ በጥንት ስሙ አንጎት ይባል ነበር፥ አንጎት በአማራ ወሰን ውስጥ ይገኝ የነበረ ግዛት ነው። የ15ኛው መክዘ የጣሊያናዊው ፔትሮ ዴል ማሳዦ ካርታም ይሄኑን ያረጋግጣል።
ethiopian itineraries, circa 1400–1524: including those collected by alessandro zorzi at venice in the years 1519–1524»
=>የራያ ህዝብ ሰቆቃ የጀመረው አጼ ዮሐንስ 4ኛ ለምን የእንግሊዝ ጦር ወጋችሁ በማለት በ1872 አ.ም አድዋ ላይ “ራያ ይጥፋ ዱር ይገፋ” በማለት አዋጅ አስነገረ።
ከዛም የራያን ህዝብ ለማጥፋት ተነሱ።አጼ ዮሐንስ ከኮረም ጀምሮ ገባቲ፣ ወረባየ፣ ኩፍኩፍቶ፣ መኾኒ እና መቻሬ ድረስ አጠፋው፤
በደጃች/ራስ አርኣያ የሚመራው ከአላማጣ ጀምሮ ዋጃ፣ ቆቦ፣ ሮቢት እና ጎብየ ድረስ አጠፋው፤እንደገና አጼ ዮሐንስ መልክተኛ ከቆቦ ከተማ ወደ ዞብል ሲያመራ አርቋቴ ባልታወቀ ምክንያት በመገደሉ 3000 ሺህ የራያ ሰው የእንጎዬ ሜዳ ሰብስዞ አንገት አንገቱን በመቅላት አንድም ሳይቀር ፈጀው፡፡
ከመቶ አመት በኋላ ከ1968 ዓ/ም ጀምሮ ህወሓት በራያ ህዝብ ላይ ተነሳ።በ1985 ዓ/ም ከትግሬ ጋር በታሪክ፣ በማንነት እና በአስተደደራዊ አከላለል የማይገናኘው ህዝብ የሚኖርበትን ገሚሱን የራያ መሬት (ኮረም፣ አላማጣ፣ ጨርጨር ወረዳዎች) በግድ ወደ ትግሬ እንዲካተት አደረገ።የተቃወሙትን በጠራራ ፀሐይ በጥይት እየደበደበ ገደላቸው።ተቃውሞው በረሀ የገቡትን የራያ ወጣቶች ህወሓት “ሽፍታ ማጥራት” በሚል ዘመቻ ሁሉንም ገደላቸው።
ወደ ትግሬ በግድ የተካተተው የአንጎት(ራያ) ህዝብ ብዛት በ አሀዛዊ መረጃ፤
አላማጣ፤ 286,118
ኮረም/ወፍላ፤ 262,114
ራያ አዘቦ፤ 162,106
ድምር፤ 710,338
ከፊል የራያ አካባቢዎች
እንዳ መኾኒ/ማይጨው፤ 116,262
አምባላጌ፤ 152,174
ድምር፤ 268,436
አጠቃላይ ድምር፤ 978,774
/የሲሳይ መንግስቴ እና አለሙ ከሳ መጽሀፍ (2005) ይመልከቱ/
የራያን ህዝብ የማንነት ጥያቄ አፍኖ ማስቀረት አይቻልም፥አስፈላጊም ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም አጭሯን ጦርነት በማድረግ ማስመለስ ነው።