ወያኔ ራያ ላይ በሚፈጽመው ግፍ ዙሪያ ዜናዎች ሲዘገቡ አመኔታ እንዲያጡ አድርጎ እንደፈለገ ግፍ ለመፈጸም እንዲያስችለው እንዲሁም የብዙዎቻችንን ተአማኒነት ለማሳጣት በማሰብ ትናንትና ይህችን ሕፃን እንደተገደለች አድርጎ በማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛዎች እንዲለቀቅ አድርጎ ነበረ፡፡ ብዙዎቻችንም ተቀባብለነዋል፡፡

ወያኔ ዜናው በደንብ ከተዘዋወረለትና ብዙዎቻችንን ካሳሳተ በኋላ እንደገና የልጅቷን ቤተሰቦች እንዲያስተባብሉ በማድረግ ዜናው ሐሰተኛ መሆኑን የሚገልጽ ዜና እንዲዘዋወር አደረገ፡፡

እኔ በግሌ ዜናውን ተጋርቸ ሽፋን በመስጠቴ አላፍርም፣ አልሸማቀቅም፣ ፈጽሞም ይቅርታም አልጠይቅም!!! በሁለት ምክንያቶች፦

1. ስሕተቱን እንድንፈጥር የተደረገው ሆን ተብሎ ለሸፍጠኛ የጥፋት ዓላማ በተቀናበረ ተንኮል፣ ሸፍጥና ሴራ ነውና፡፡

2. ወያኔ በ27 ዓመታት የአገዛዝ ዘመኑ በተለይም 1996 .. በገጠር በርካታ የአማራ ሕፃናትንና ነፍሰጡር እናቶችን የትራኮማ ክትባት እያለ ገዳይ መርፌ በመውጋት እንደገደለ በሚገባ ይታወቃልና ነው፡፡

በዚያ ዘመን የገጠር አብያተክርስቲያናት የመቃብር ስፍራዎች በሕፃናትና በነፍሰጡር እናቶች ተሞልተው ሁኔታው አስደንጋጭና አስጨናቂ ድባብ ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የወያኔ የዘር ማጥፋት ጥቃት በተለያየ ዘዴ ሲፈጸም እንደቆየና እየተፈጸመም እንዳለ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡

በመሆኑም በወያኔ አረመኔያዊ የዘር ማጥፋት ጥቃት በሚሊዮኖች (በአእላፋት) የሚቆጠሩ ጨቅላ ሕፃናት አማራ በመሆናቸው ብቻ በጭካኔ እንደተበሉ እያወኩ እንዴት ብየ ነው ወያኔ ይሕችን ሕፃን ገደለ መባሉ ሐሰት ነውና ተገደለች ብየ ያልተጣራ ወሬ በመዘገቤ ይቅርታ!” ልል የምችለው???

ይህችም ሆነች ሌሎች የአማራ ሕፃናት ከዛሬ የወያኔ ቅስፈት ቢያልፉ ከነገ ያልፋሉ ወይ??? ለኔ እግዚአብሔር ይድረስልን እንጅ ማንኛውም አማራ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ የተበላ ዕቁብ ነው!!! በሕይዎት እንዳለን አልቆጥረውም፡፡

በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ በጠየቁ ወገኖች በእጅጉ ማፈሬን መግለጥ እወዳለሁ!!! የፈለገው ነገር ሆነ ተብሎ ቢወራ ወያኔ ፈጸመው የሚባል ነገር ሁሉ ሐሰት ነው መባል የለበትም!!! በስውር ስለሚፈጸምና መረጃ ያለማግኘት ጉዳይ ነው እንጅ ወያኔ በእኛ ላይ ያልፈጸመው የግፍ ዓይነት ፈጽሞ የለምና!!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com