ዛሬ ብአዴን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መግለጫ ማውጣቱን ሳውቅ ተለውጨ ለአማራ ሕዝብ ቆሜያለሁ!” ማለቱን ሕዝብ እንዲያምንለት ለማድረግ ፈርጠም ቆፍጠን ብሎ በሕገወጥ መንገድ ወደ ትግራይ እንዲከለሉ የተደረጉት ራያ ወልቃይትና አካባቢያቸው በነባር ሕዝቡ ውሳኔ እጣ ፋንታቸውን እስኪወሰን ድረስ ከራያና ከወልቃይት የትግራይ ታጣቂዎች ወጥተው ገለልተኛ የማዕከላዊ መንግሥት የጸጥታ ኃይል (ፌዴራል ፖሊስ) በቦታው ይስፈር!” ሲል ማዕከላዊ መንግሥት ነው የሚለውን የዐቢይን አሥተዳደር ይጠይቃል የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ አየ ቂልነቴ!

ብአዴን ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ ላይ “….የተከሰተው ግጭት መነሻው የራያ አካባቢ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ሲሆን ይሄንን ጥያቄ ከሕዝቡ ጋር በመነጋገር ሕገመንግሥታዊ ምላሽ መስጠት እንደሚገባ በአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም ሆነ በኢሕአዴግ ጉባኤዎች አቅጣጫ መቀመጡ ይታወሳል፡፡ አሁንም ቢሆን መፍትሔው ጥያቄውን ከሚያነሣው የአካባቢው ሕዝብ ጋር የሰከነ ውይይት በማድረግ ሕገመንግሥቱ ላይ በመመሥረት መፍትሔ መስጠት እንጂ የኃይል እርምጃ መውሰድ አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል….!” በማለት በሕዝባችን ላይ በስፋት እየተፈጸመ ያለውን አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻውን ግፍ ፈጽሞ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ የለዘበ መግለጫ አውጥቷል፡፡

የመግለጫው ዋነኛ ችግር ግን ይሄ አይደለም፡፡ የመግለጫው ችግር የወልቃይት ራያና ዓለምአጣ ችግር ሕገ መንግሥቱ ላይ በመመሥረት መፍትሔ ይሰጥ!” ማለቱ ላይ ነው፡፡

እንደምታስታውሱት ከዓመታት በፊት ጀምሬ በእነዚህ በሕገወጥ መንገድ የሕዝቡ ፈቃድና ይሁንታ ሳይጠየቅ ከጎንደርና ከወሎ ተቆርሰው ወደ ትግራይ በተከለሉ ስፍራዎች ጉዳይ በጻፍኩ ቁጥር የወልቃይት የራያና በዙሪያቸው ያሉ ስፍራዎች ዕጣ ፈንታና የኗሪው ሕዝባዊ የማንነት ጥያቄ ጉዳይ በፍትሕ እንጅ በሕገመንግሥታዊ መንገድ ሊፈታ እንደማይችል፣ በሕገመንግሥታዊ መንገድ ለመፍታት ከተሞከረ ውጤቱ ኢፍትሐዊ እንደሚሆን አጥብቄ ሳሳስብ ቆይቻለሁ፡፡

ለምሳሌ ዐቢይ ጎንደርን በጎበኘ ጊዜ በተናገረው ላይ ተመሥርቸ በዕለቱ የሚከተለውን ብየ ነበረ፦

“””ዐቢይ የወልቃይት ጥያቄ ሕገ መንግሥቱንና ሕጉን መሠረት አድርጎ ይመለሳል!” ማለቱን ሰማን፡፡

ምን ማለቱ እንደሆነ ገብቷቹሃል? ሪፈረንደም (ሕዝበ ውሳኔ) ይደረጋል ማለቱ እኮነው! ይሄም ማለት እዚያ ቦታ ላይ መኖር ከጀመረ አምስት ዓመት የሞላውና ከዚያ በላይ የሆነው ሁሉ ድምፅ ሰጥቶ እንዲወሰን ይደረጋል ማለቱ ነው፡፡ ሕገመንግሥቱ የሚለው ይሄንን ነው፡፡ ዓያቹህት እንዴት እንደሚሸፍጥ???

ወያኔ አማራን ከወልቃይት መንጥሮ የዘር ማጽዳት ወንጀል መፈጸም ከጀመረ 40 ዓመታት አልፎታል፡፡ ሥልጣን ሲይዝም አማራን እየመነጠረ ወገኑን ከትግራይ እያጋዘ አምጥቶ በማስፈር ሀገሩ በሙሉ በትግሬ እንዲሞላ አድርጓል፡፡

ይህችን ነገር ዐቢይ በሚገባ ታውቃለችና ሕዝበ ውሳኔው ትግሬን እንጅ አማራን አሸናፊ እንደማያደርግ ስለምታውቅ ሕገመንግሥቱ በሚያዘው የመፍትሔ አሰጣጥ ዘዴ ወይም የችግር አፈታት ዘዴ በሕዝበ ውሳኔ ይፈታል!” አለች፡፡

ዐቢይሻ ስታይን ቂል እንመስልሻለን???

ዐቢይ ጆሮ ካለሽና ማመዛዘን የምትችይ ከሆነ ያቀረብሽው የመፍትሔ ሐሳብ ኢፍትሐዊ ነውና መልሰሽ ዋጭው!!! ወይም ደግሞ ሕዝበ ውሳኔው የሰፋሪ (የትግሬ) ድምፅ ሳይካተት በነባር ነዋሪው ሕዝብ ድምፅ ብቻ ነው የሚደረገው ካልሽ መልካም! ካልሆነ ግን ተጭነሽው የመጣሽውን የጅል ሐሳብ ይዘሽ አሁኑኑ ውልቅ በይልን???””” ብየ ነበረ፡፡

አሁን ደግሞ ቅጥረኛው ብአዴን የወያኔ ሕገመንግሥት የወያኔን የዝርፊያንና የውንብድና ተግባሮችን ሕጋዊ ለማድረግ ታስቦ የተቀረፀና የወያኔን ኢፍትሐዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ተቀምሮ የተቀመጠ ሸፍተኛና ኢፍትሐዊ የወያኔ የውንብድና ሰነድ መሆኑን እያወቁ ከጎንደርና ከወሎ በሕገወጥ መንገድ የተወሰዱ ስፍራዎች ሕገመንግሥቱ መሠረት ተደርጎ መፍትሔ ይሰጠው!” ሲሉ መግለጫ አውጥተውላቹህ አረፉት፡፡

ይሄም ማለት ደግሞ አማራው ከአካባቢው በግፍ እየተገደለና እየተፈናቀለ እንዲጸዳ ተደርጎ በቦታው ከትግራይ እየተጋዘ ወልቃይትና ራያ እንዲሰፍሩ የተደረጉ ትግሬ ሰፋሪዎች በሕዝበ ውሳኔው ላይ ተሳትፈው ሕዝበ ውሳኔው ይደረግ!” ማለት ነው፡፡ እጅግ በጣም ያሳዝናል!!! እንዲያው ዝም ብላቹህ ድከሙ ብሏቹህ ትደክማላቹህ እንጅ ይሄ ብአዴን የሚባለው የእርጉማን ቡድን በምንም ተአምር መቸም ቢሆን ለአማራ ሕዝብ ጥቅም፣ መብት፣ ደኅንነትና ህልውና መቸም ቢሆን ሊቆም አይችልም!!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com