ከመንግስቱ ሙሴ ፌስቡክ የተወሰደ

አይጋ ፎረም የተባለው ድህረገጽ ላይ ነው በ 11/01/2018 በፍስሀ ከበደው በሚል ስም የወጣች የሰይጣን ምኞት አየሁ። ጸሀፊው የህወሓት መዋቅር አባል ለመሆኑ እርግጠኛ ነው። ምኞቱ የህወሓት የከሸፈ ዳር ያልደረሰ ግን ቀላል የማይባል ጉዳት ያደረሰ ስራን ይገልጣል። እርዕሱ እንዲህ ይላል

“አገሪቱ መበታተኗ አይቀሬ እየሆነ ነው” ይላል
መቸም የትግራይ ጽንፈኞች “ኢትዮጵያ” የሚልን ስም ይፈሩታል እና “አገሪቱ” ይሉናል

Adios TPLF (Goodbye)

ሁልግዜም የህወሃት ምኞት እና ቋሚ አላማ ይህ ኢትዮጵያን መበተን ነበር። ኢትዮጵያን ለመበተን “ከአልኋ ምላሽ” የሚል ካርታ መሳል ነው። ሁሉም ተደርጓል። ጸለምትን፣ ወልቃይትን፣ ጸገዴን፣ ሁመራን ወስደዋል።፡የምናውቀው የትግራይ ክፍለ ሀገር (ጠቅላይ ግዛት) ተከዜ ምላሽ ነበር በምእራብ ከኤርትራ የተሰኔ ግዛት የሚዋሰን እንደነበርም የቅርብ ግዜ እውነተኛ ታሪክ ነው። የህወሓት አላማ እና ህልም ግን በሙሉ የምእራብ ኢትዮጵያን ወደትግራይ መጠቅለል ሲሆን ለዚያ የጎንደርን ከሁመራ እስከ መተማ፣ ሰሜን ወሎን ወስደው የጦር ቀጠና አረገዋል፡፡ የጎጃም መተከልን እና የወለጋ አሶሳን በጉምዝ ቤንሻንጉል ክልል ስም መውሰድ። ይህ አዲስ ልትፈጠር የነበረችን ትግራይ የኢኮኖሚ እና የውጭ ግንኙነት ፍላጎት እና ጥቅም ያሟላል ተብሎ የታሰበ ነበር። ያ ከሸፈ የኢትዮጵያ ሕዝብ ህወሓት ከዘረኝነት ወደ ሀገራዊ አጀንዳ ትመጣለች ብሎ ቢጠብቅ እየቆየች መዝረፍ ሕዝብን ማሰደድ የነቁትን ማሰር እና ዳብዛ ማጥፋት ሆነ። አልጠግብ ባይ ይባላል የመጨረሻ የህወሓትን ወርድ እና ቁመት አሳያት። መትረጌስ ተሸክሞ፣ ታንክ አንከባሎ ሳይሆን በባዶ እጅ ወጥቶ መድረሻዋን አሳጣት። ዛሬ የህወሓት መሪወች እና ዘር በማጥፋት የሚታወቁት ወንጀለኞች ጠቅልለው መቀሌ ከትመዋል። ቢችሉ ትግራይን ገንጥለው አዲስ ሪፖብሊክ መስርተው ነበር ግን አይችሉም ህልማቸውም በኢትዮጵያ ጥፋት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ቀቢጸ ተስፋ ሆኗል።
ጽንፈኛዋ ህወሃት እና አባላቱ ልክ አይጋ ፎረም እንደወጣው አይነት አስተሳሰብ አላቸው። ምኞታቸው ብቻ ሳይሆን እምነታቸውም ኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ አላት ይሉን ነበር ያኔ በጸረ ኢትዮጵያ ትግላቸው ዘመን። ያችም የመቶ አመቷ ባለታሪክ አማራ ሰራሽ ይሏት ነበር። ብዙወቹ የባንዳ ልጆች ስለነበሩ ከምር የሚጠሏት ኢትዮጵያ የባለ ሦስትሽህ ዘመን የእድሜ ባለጸጋ፣ የስልጡን ሕዝብ ሀገር ህብረ ቀለማት የሆነች መሆኗን ፈጽሞ ማመን፣ መስማት አይፈልጉም። የሜዳ የፖለቲካው ሹም መለስ ዜናዊም ስለነበር (አይነታው የባንዳ ልጅ) አጥብቆ ያስተማራቸው ይህን የእውሸት ጸረ ኢትዮጵያ ታሪክ ነበር። ሞኝ የያዘውን እንዲሉ ቂሎች ለመለስ አላማ ታገሉ። ንጹሀን የትግራይ ወጣቶች በማያውቁት የተረት ተረት ጸረ ኢትዮጵያ ታሪክ ተተብትበው ህይወታቸውን ገበሩ። እድሜ የሰጣቸው እና የተረፉት ከስርአቱ ፍርፋሪ ያልደረሳቸው የህወሓትን የመጨረሻ ማየታቸው አይቀሬ ነው። መሪወቹ ግን ዛሬም አቅም ሸሽቷቸው ተቸንፈው መቀሌ ከከተሙ በኋላም ሕዝብ ከሕዝብ ማባላታቸውን ቀጥለዋል። የሚመኙትም የኢትዮጵያን መፍረስ ስለሆነ ሌት ተቀን በማህበራዊ ገጽ እና በከፈቷቸው መገናኛወች ሁሉ ልክ ከላይ እንዳሳየሁት አይነት ትንቢት ሲናገሩ እና ሲጽፉ ይውላሉ። ያ ቀቢጸ ተስፋ ብለነዋል። ኢትዮጵያ የነበረች፣ ያለች ወደፊትም አብባ እና ፈክታ የምትኖር ሀያል ሀገር ናት። ለማሳነስ የሞከሯት ዛሬም እንደአንበሳ አግስታ ተነስታለች።