ዐቢይንና ለማን የለውጥ ሐዋርያት አድርገው የሚያስቡ ወገኖች “የለውጥ ኃይል የሚባለው ዐቢይ፣ ለማ ብለን ሦስተኛ ሰው መጥራት የማንችልበት ነው!” ሲሉ ይሰማሉ፡፡
እኔ ደግሞ እንዲህ የሚሉ ወገኖችን ልጠይቃቸው “ከዐቢይ እና ለማ ውጭ ያለው ወያኔ/ኢሕአዴግ የለውጥ አደናቃፊ መሆኑን ካወቁ እነኝህ የለውጥ አቀናቃፊዎች እንዴት ዐቢይንና ለማን በሙሉ በሙሉ ድምፅ በመሪነት ሊመርጧቸው ይችላሉ ብለው ሊያምኑ ቻሉ??? ዐቢይንና ለማን በተደጋጋሚ መርጦ መሪ ያደረጋቸው ማን ነው???” ለሚለው ጥያቄ መልስ ይኖራቸዋል ወይ???
መልሱ ሌላ ሳይሆን ነገርየው ትወና በመሆኑ ነው ዐቢይን እና ለማን “የለውጥ አደናቃፊ!” በሚባሉት በሙሉ በሙሉ ድምፅ የክልል ሊቀመንበርና እና የፌዴራል ጠ/ሚ አድርገው ሊመርጧቸው የቻሉት ሌላ ምንም መልስ የለውም፡፡
ካልሆነ በስተቀር እነ ዐቢይ እና የለውጥ አደናቃፊዎች የተባሉት በጠላትነት እስከመፈላለግ የደረሰ ሰፊ የዓላማ ልዩነት እያላቸው የለውጥ አደራቃፊዎች ዐቢይንና ለማን በሙሉ በሙሉ ድምፅ መርጠው መሪ ሊያደርጉ አይችሉም፡፡
ስለሆነም የምናየው ነገር ሁሉ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ሞራሊቲ (ቅስማዊነት) የጎደለው፣ መንግሥት ነኝ ከሚል አካል ፈጽሞ በማይጠበቅ መልኩ ነውረኛነት የተሞላ ትወና፣ ማወናበድና ተራ ሕዝብን የማጭበርበር ተግባር እንጅ ለውጥና የለውጥ ኃይል የሚባል ነገር የለም!!! ይሄንን ጠንቅቃቹህ ልታውቁ ይገባል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
