አሁን ላለንበት ዘርና ጎሳ እየለየ የመጋጨት ቀውስ መንስኤ የጎሳ ፌዴራሊዝሙ (የራስ ገዙ) ሥርዓት እንደሆነ ከማናችንም የተሰወረ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡

ዐቢይና ለማም ይሄንን በመረዳት ነፍስ ብሔር የላትም ዘር እየለየን ከምናደርገው መናቆር መውጣት አለብን!” እያሉ ጣፋጭ ዜማን እያዜሙ የጎሳ ፌዴራሊዝምን (የራስ ገዝን) ሥርዓት መሠረታዊ አስተሳሰብ እየናዱ፣ እየኮነኑ፣ እያወገዙ ሲመጡ ጊዜ ሕዝቡ በከፍተኛ ፍቅርና አክብሮት ተቀበላቸው፡፡ እኔን የመሰሉ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ያላመንናቸው ቢንኖርም ቅሉ፡፡ ሕዝቡ ግን የተናገሩትን መሬት ላይ ያወርዳሉ ብሎም ሲጠብቅ ቆየ፡፡

ለካ ያ ሁሉ ድለላ ወያኔ/ኢሕአዴግን ከገባበት አጣብቂኝ ለማወጣት ለማስመለጥ የተፈጠረ መላ ኖሮ የተናገሩትን መሬት ላይ ያሳርፋሉ ተብሎ ሲጠበቅ በአደባባይ ሌላ እየተናገሩ በተግባር ግን የዚህን ተቃራኒ ሥራ ሲሠሩ ቆዩ፡፡

ዐቢይ አሜሪካን በጎበኘ ጊዜ ምሁራን ከተባሉ ወገኖች ጋር በነበረው ውይይት ላይ የጎሳ ፌዴራሊዝሙ ያለበትን ችግርና ከችግሩ መውጫ መፍትሔን የሚያጠና ክፍል ይቋቋማል!” ሲል ተናግሮ ነበር፡፡ ያኔ ዐቢይ ይሄንን ሲል ሁሉም ሰው የተረዳው የነበረው የጎሳ ፌዴራሊዝሙ ለሀገር ሰላምና ህልውና፣ ለሕዝቡ አንድነት ጠንቅ መሆኑ በግልጽ ስለታወቀ ይህ የሚቋቋመው አካል የጎሳ ፌዴራሊዝሙ የፈጠረብንን ሳንክ ተረድቶ የጎሳ ፌደራሊዝሙ እንዲያከትም ምክረ ሐሳብ የሚያቀርብና ሀገሪቱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከጎሳ ፌዴራሊዝም (የራስ ገዝ) ሥርዓት ጋር እንደምትለያይ አድርጎ ነበር የተረዳው፡፡ በመሆኑም ተስፋ ሰነቀ፡፡

ይሁንና ዐቢይ በአዋሳው የኢሕአዴግ ጉባኤ ላይ እንደ ኢትዮጵያ ላለችና ፈርጀ ብዙ ብዝኃነትን ለተላበሰች ሀገር ፌዴራሊዝም የተሻለ የአሥተዳደር ሥርዓት ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥት አወቃቀር ደግሞ የሀገሪቱን ታሪካዊና ነባራዊ ሁኔታ ማገናዘብ ይኖርበታል፡፡ ክልላዊ አሥተዳደርን ከብሔር ማንነት ጋር ሳናምታታ ማስተናገድ ከቻልን እንደኛ ሀገር ላለ ነባራዊ ሁኔታ ፌዴራሊዝም ተመራጭ የአሥተዳደር ሥርዓት መሆኑ አያጠያይቅም!” በማለት ቃሉን ማጠፉንና ከጎሳ ፌዴራሊዝም ጋር የመፋታት እሳቤ እንደሌለ ጠቆመ፡፡

ዛሬ ደግሞ ጎንደር ከሀገር ሽማግሌዎችና ከወልቃይት ራያ የአማራ ማንነት ተወካዮች ጋር ባደረገው ውይይት ምን አለ መሰላቹህ ይሄ ጥያቄያቹህ የክልል ወሰኖችን ችግሮች አጥንቶ መፍትሔ የሚሰጥ የድንበር ኮሚሽን ስለሚቋቋም ያነሣቹህት ችግር በዚህ የሚፈታ ይሆናል!” በማለት አገዛዙ ከጎሳ ፌዴራሊዝም ጋር መቁረቡንና መለያየት የማይፈልግ መሆኑን እንቅጩን ተናግሯል፡፡

አያሳዝንም??? እንግዲህ በዚሁ የጎሳ ፌዴራሊዝም ሳቢያ በድንበር ወሰን ይገባኛል ጥያቄ ግጭት እየፈጠርን መፋጀታችንና በየቦታው ሕዝብ መፈናቀሉ በመላ ሀገሪቱም በየትኛውም አቅጣጫ እሳት መንደዱ መቀጠሉ ነው ማለት ነው፡፡

እኔስ ከዝንብ ማር፣ ከእባብ እንቁላል እርግብ ጠብቃቹህ ለዐቢይ ዘመኑ የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ላገበገባቹህ ላፎደፎዳቹህ የዋሃን ወገኖቸ በእጅጉ አፈርኩላቹህ!!!

እኔ የምለው ሕዝብን መዋሸት፣ ማወናበድ፣ ማታለል፣ ማጭበርበር፣ ማበል እንዴት ነው ለነ ዐቢይ የዚህን ያህል ቀሎ ሊታያቸው የቻለው ግን??? ያንን ሁሉ እያሉ ሕዝብን ሲደልሉ፣ ሲያታልሉ፣ ሲያጭበረብሩ እንደመክረማቸው እንዴት እፍረትና ይሉኝታ አይሰማቸውም??? ሕዝብን አይደለም ግለሰብን እንኳ መዋሸት፣ ማጭበርበር፣ ማወናበድ አያሸማቅቅም??? ሰው እንዴት በመሪ ደረጃ ተቀምጦ የዚህን ያህል የወረደ ሰብእና ሊኖረው ይችላል??? ይሄ እግዚኦ አያሰኝም??? ለመሆኑ ምን ዓይነት ቤተሰብና ምን ዓይነት ማኅበረሰብ ነው ወልዶ ያሳደጋቸው??? ግን እርግጠኞች ናቹህ እነኝህ አሳዳጊ አሰዳቢዎች እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ተወልደው ያደጉት???

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አር