
ተሐት (ወያኔ ሐርነት ትግራይ) ህወሓት፣ ማሊሊት ብዙ ስም ነው የነበራት። አላማዋ ግን አንድም ሁለትም የሆነው አንድ እና አንድ ብቻ ነበር። ጸረ ኢትዮጵያ/ጽረ አማራ። በህወሓት አስተሳሰብ ኢትዮጵያ የብሔር ብሄረሰቦች እስር ቤት ናት። “ኢትዮጵያ አማራ ሰራሽ የሆነች እና የአማራ ኮሎኒያሊስቶች በሀይል ጨፍልቀው የሰሯት ሀገር ናት” የኢትዮጵያ ጠላቶችን ከጎኗ ለማሰለፍ ብዙ ተብሏል። ምኞት ቀቢጸ ተስፋ ሆኖ አልቀረም እና የአረብ ፔትሮ ዶላር ለህወሀት ከሰማይ የሚወርድ መና ሆነላት። የጸረ ኢትዮጵያው ዘመቻ በተቀነባበረ፣ በተደራጀ እና ከፍተኛ ወጭ በተደረገለት የህወሓት ሰራዊት ተካሄደ። በዘመቻውም ኢትዮጵያን የሚያሳይ ማንኛውም ምልክት ፈረሰ። የኢትዮጵያ የሦስት ሽህ አመት ታሪክ የመቶአመት የአማራ ታሪክ ሆነ። ጎበና ዳጨ፣ ሀብተጊወርጊስ ዲነግዴ፣ ባልቻ አባ ነፍሶ ወዘተ ሁሉ የሸዋ የአማራ መኳንንት ሆነው ተሳሉ። ፈርሀ እግዚያብሔር የተላበሱት ታላቁ ንጉሠ ነገስት ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ተሰደቡ። ሚኒሊክ 3000 የነጭ ምርኮኛን ከጀኔራል አልቤርቶኒ ጋር ይዞ የሰለጠነ አለም ዛሬ ድረስ የማያደርገውን ምርኮኛን መንከባከብ እና ወደሀገሩ መንግስት መመለስን ያሳየን የ19 ኛው ዘመን ታላቅ መሪ ጡት ቆረጠ ብለው ተሳደቡ፣ ሰደቡን አዋረዱን። የህወሓት ተልእኮ እስከዚያ ነበር። ከታላላቅ የውጭ ጦርነቶች እና ወራሪወች የተረፈችን ሀገር እና ሕዝብ ማዋረድ ያም ተፈጸመ። ዜጎችን እኛ ትግራውያን በሚል መሪ መፈክር ማሰር፣ ማዋረድ፣ እና ዳብዛ ማጥፋት ነበር ሁሉም ተከናወነ። ጠላቶቻችን ፈነደቁ የአሜሪካ የደህንነቱ መስሪያቤት ሰራተኛ የነበረው ፖል ሔንዝ ህወሓት አዲስ አበባ ከመግባቷ በፊት ያደረገላትን አቀባበል እና ቃለምልልስ በመለስ በኩል ማስተዋል ተገቢ ነው። ግዜ ሲኖር አንድ ቀን ያነን የስራ መቅጠሪያ ቃለምልልስ የሚመስለውን እዚሁ በፌስቡክ አስነብባለሁ።
የህወሓት ክብር እና ታሪካዊ ጉዞ እስከዚህ ነበር። ዛሬ 40 የሚሆኑት የዚህች ዘረኛ ድርጅት አባላት ታሰሩ። እነዚህ የሀገር ንብረት የዘረፉ፤ ከእናቶች መቀነት ተፈትቶ ለሀገር ዘላቂ እድገት ይሆናል በሚል የተሰበሰበ በዘመድ አዝማድ እና በቤተሰብ ተሰባስበው ዘረፉ። ጥፍር የነቀሉ፣ አካል ያጎደሉ፣ ንጹሀንን አስረው የወለዱ ልጆቻቸውን ሳያሳድጉ በእስር እድሜአቸውን የጨረሱ። እንዴውም ብዙወች በየእስር ቤቱ የቀሩ ይህን እና በየአደባባዩ ሰላማዊ ዜጋን የረሸኑ፣ ያስረሸኑ። የት መድረሳቸው ያልታወቁ ዜጎች ዘመድ አዝማድ እርም ሳያወጡ ከዛሬ ነገ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ የተሰራው ወንጀል ቤት እና ታሪክ ይቁጠረው እንጅ ይህን ወንጀል የፈጸሙ እና ያስፈጸሙ በጥብቅ ተሀድሶ እንዲህ በቀላል የሚለቀቁ እንደማይሆን ተስፋችን ነው።
ህወሓት በተወለደች በ44 አመቷ ማለት ነው ወደመቃብር ሄደች። ከኢሕአፓ ጋር የነበራት ልዩነት ሰፊ እና በኢትዮጵያ እና በህወሓት መሀል ያለው ቅራኔ ነበር። ለዘመናት የታገሉ ያታገሉ መሪወችን በአገኘችው ግዚይዊ ድል እና በደጋፊ ተባባሪ የውጭ እና የውስጥ ጠላቶች ድጋፍ ኢሕአፓ/ኢሕአሰን አዳከመች። መሪ ታጋይወቹን ዳብዛቸውን አጠፋች። ግን እርሷ ወደታሪክ ቆሻሻነት ስትቀየር የተሰው በህይወት ያሉ የኢሕአፓ ታጋዮች ከሕዝብ ጋር አብረው ታዘቡ። የአገር አጥፊዋ ህወሓት ታሪክም ትቢያ ሲሆን፣ የኢሓፓወች አላማ እና ገድል ግን ህያው ነው። አገር ለማፍረስ የተደራጀችው ህወሓት የማፍረሱን የቤት ስራ እና የዘረፋ ወንጀሉን በሌላ ወገን አጦዘችው።፡አይቀሬው ውድቀቷ ያውም አይን እያየ ጀሮ እየሰማ ውግዝ ከማሪወስን አጣጥማ እየሟሸሸች ትርኢቱን ተከታተለችው። መቸም ህወሓትን ማመን ቀብሮ ነው እንል ነበር። ወዳጅ ያለችውን ቀን ጠብቃ ታጠፋዋለች እና ነው። ኢሳያስንም በአሳቻ ግዜ አግኝታ እንዳይሆን አድርጋው ነበር። የሰራላትን ውለታ ሁሉ ገድል ከታ አጠፋቸው። አፈር ልሶ የተነሳው ኢሳያስ ጎንደር ላይ ቀለደባት። አስመራ ላይ Game over no more TPLF አለ። የታላቁን፣ እና እሩህሩህ ይቅርባዩን አማራን ታላቅነቱን እና የተደረገው ታናሽ ስራን ተናገረው።፡የህወሓት አልህዋ ምላሽ የቆየ ህልም ቀቢጸተስፋ እንዲሉ ጎረቤታችን ጎንደር አማራ ነው አለ። በአይናችን እየሟሟች ያለችው ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ከወገኑ ነጥላ ለማስቀረት እና ዳግም ሌላ ጦርነት እንዲገባም በራያ፣ በወልቃይት፣ በፀለምት የምታካሂደውን ሽብር እና ዘር የማጥፋት ተግባር ቀጥላበታለች። ይህ ዋና አላማዋ ስለሆነ ማለት ነው።
መሰረታዊ ጠላቴ አማራ ነው ብላ ነበር። ከኢሕአፓም ጋር የተለያዩበት አንዱ እና ዋነኛው ይህ ነበር። ወልቃይት ላይ 1971 ግዚያዊ ድል እንበለው አግኝታ ነበር። ከ13 ቀናት ውጊያ በኋላ ኢሕአፓን አስለቅቃ ወልቃይትን በይፋ ወደትግራይ ጠቀለለች። ከዚያ በኋላ የሆነውን ሁሉ የፈሰሰው የወልቃይት፣ የፀለምት ደም ይጮሀል።፡ይህ ደግሞ ሌላው ከኢሕአፓ ያዋጋው ሁለተኛው የህወሓት አላማ ነበር። ብዙ ከማሀል ሀገር የሄዱ የኢሕአፓ ታጋዮችም በዚያ ውጊያ ተሰውተዋል። ሌላው ከኢሕአፓ ያለያያት እና እስከወዲያኛው በጠላትነት ያፈራረጃት ኢትዮጵያ የብሄረሰቦች እስርቤት ናት አለች። ኢሕአፓ ሀሰት ነው ሁሉም ዜጋ በመደብ እና በገቢ ልዩነት እንጅ ጨቋኝ እና ተጨቋኝ ዘር ኢትዮጵያ ውስጥ የለም ግን ጨቋኝ ገዥወች ሁሉንም በእኩል ጨቁነዋል አለ።፡ይህ የጸና የኢሕአፓ አላማ ከሁሉም የዘር ድርጅቶች አይን እና አፈር አደረገው። ከኦሮሞ ነጻ አውጭ፣ እስከ የምእራብ ሶማሌ ድረስ ያሉት ትምክህተኛ ብለው ፈረጁት። ኢትዮጵያን ከድህነት፣ ከኋላ ቀርነት፣ አውጥተን ማህበራዊ ፍትህ እና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ሀገር ብናደርግ ሀገራችን ከማንም በላይ ሀያል ናት በማለቱ ተረባርበው ትምክህት ብለው ኮነኑት። የዘር ድርጅቶች የጸረ ኢትዮጵያ ኀይሎች ሁሉ ውግዝ ከማርዮስ ብለው እንዳይደርስባቸው ተማማሉ። ሎንደን ላይ በሄርማን ኮህን ሲሰየሙ ኢሕአፓ የተባለ የታላቋ ኢትዮጵያ ህልመኛ ትምክህተኛ ነው እንዳይደርስብን አሉ። የሽግግር መንግስት ሲመሰርቱ ግዜው የነሱ ሆነና ባሻቸው ዶልተው የፈረደበትን አማራ እና ኢሕአፓን ከካርታ የመፋቅ ያክል አስወገዱ።
ያሁሉ አልፎ ከእሩብ ምእተ አመት በኋላ ህወሓት ወደትቢያ ጎዳናዋን አፋጥናለች። ስለኢትዮጵያ ያለመው ኢሕአፓ እና መሰል ሀይሎች የብሩህ እና ፍጹማዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ተንሳኤን በጉጉት እየጠበቁ ነው። ታሪክ ግን አይቆምም፤ ታሪክ ደግሞ ክፉ ነው ደግነት የለውም። እውነቱን ስለሚይዝ እና ስለሚከተል ትቢያወችን ትቢያነታቸውን ለመጭው ተከታታይ ትውልዶች ያስረክባል። ዛሬም እንደወዲያኛው ዘመን ተደጋግሞ እንደታየው በታሪክም እንደተመዘገበው ኢትዮጵያ ጠላትቿን አቸንፋ ትነሳለች። የጠላቶቿን መርበትበትም እያየን ነው። ስሟን የተጠየፉት ዛሬ እንደሳት የምትፋጅ ትሆንባቸዋለች። የተሰውት ሰማእታቱ፣ የገደሏቸው፣ ዳብዛቸውን ያጠፉት ጀግኖች ግን ህያው ታሪክ ተመዝግቧል። ታሪክ ለነዚያ ለዚህች ሀገር፣ እና ለዚህ ደግ ሕዝብ ሲሉ ለወደቁ መልካም ቦታ አዘጋጅታለች። ይብላን ለህወሓት አይኗ እያየ በፊቷ የታሪክ ስላቅ ለምታየው። እርኩስ መሪዋ “ባለ እራዕይ” ብላ ለቀለደችብን የኢትዮጵያ ዋና ጠላት። ድንቄም። በፊታቸው ከያደባባዩ ፎቶው ሲነቀል። የሰይጣን ምስልነቱ ሲነገር ዘረኛዋ የትግራይ ጽንፈኛዋ እያየች ነው። Adios TPLF!
