እንግዲህ  ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ ለመናገር እየቀፈፈው  የተደረጉ አረመኔያዊ ድርጊቶችን በደምሳሳው ነው፡፡ እርግጥም በምን ቃላት ይገለጻል? በአለፉት 27 ዓመታት ምን ያህል ሰው በእንደዚህ የሰይጣናዊ እምነት ተከታይ የሆኑ አረመኔዎች በሚዘገንን ሁኔታ አሰቃይተው አጥፍተዋል፡፡ በቃ የሆነው ሁሉ ለመናገር ይቀፋል፡፡ እንግዲህ እንዲህ ያሉ አረመኔዎች ኢትዮጵያ ሠላም ከሆነች ምን እንደሚገጥማቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ አውሮፕላን ጠፋ መርከብ ጠፋ፡፡ እንኳን ጠፉ! ከምንሰማቸው አረመኔያዊ ድርጊቶች ጋር በመዘኑ የብናኝ ያህል አደሉም፡፡ ብዙ የጠፋ የሰው ልጅ አለ፡፡ ለአውሬ ከእነ ነፍሱ የተሰጠ ብዙ ነው፡፡ በቃ የቻሉትን ሁሉ አረመኔያዊ ድርጊት ፈጽመዋል፡፡ ሰውን ቶርቸር ማድረግ፣ በጥይት መግደል፣ በድብደባም መግደል ቀላል ሆኖ ይሰማችኋል የተፈጸመውን አውሬያዊ የአረመኔ ድርጊት ስትሰሙ፡፡ ከእንደነዚህና መሠል ወንጀሎች ጀርባ ብዙዎች ተሳትፈዋል፡፡ የለውጡ ኃይል ወደ ሥልጣን መምጣት አብድ ያደረጋቸው ዝም ብሎ ተራ የፖለቲካ አለመስማማት አይምሰላችሁ፡፡ አረመኔያዊ ወንጀላቸው እንዳይጋለጥ ለውጡን መቀልበስ ግድ ይላቸዋል፡፡ ይሄን ሁሉ አረመኔያዊ ድርጊት የፈፀመ የወያኔ አውሬ ቡድንና አጋሮቹ ኢትዮጵያ ሠላም ሆና እነሱ መቀመቅ እንደሚገቡ አሳምረው ያውቁታል፡፡ እዚህ ጋር ከለውጡ ጀርባ ብዙ አስተዋጽኦ ያረጉ አሉ፡፡ የሕዝብ ትግሉ እንዳለ ሆኖ መከላከያው ቁልፍ እንደነበር እንረዳለን፡፡ ብዙዎች መከላከያው በወያኔ አረመኔ አመራሮች ነው የሚታዘዘው ብለው ብዙ ሲሉ ነበር፡፡ እንደተረዳሁት፡፡ በዛ ቀውጢ ወቅት መከላከያው ከእነ ለማ ጋር ባይቆም ኖሮ ዛሬ የምናየውን እስከወዲያኛውም አናይም ነበር ብይ አምናለሁ፡፡ በወቅቱ ከመከላከያው በአረመኔው ድርጊት ተሳታፊ በሆኑት ብዙ እዛም እዚህም ሕዝብን ማሸበርና ሁሉም ነገር በእነሱ ቁጥጥር ሥር እንደሆነ ለማሳየት ሞከረዋል፡፡ ይበልጠው እውነታ ግን መከላከያው ቀድሞውንም ቦታውን ይዞ ነበር፡፡ ለዛም ነው ዛሬ አብይ የተናገረለት መከላከያ የተፈጠረው፡፡ ለዚህ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፡፡ ግን በሕዝብ ዘንድ ይሄ ብዙም አይታወቅም እንዲታወቅም አላስፈለገም፡፡ እነ ሳሞራ እጃቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ሲሰናበቱ ቀድሞውንም ከጥቅም ውጭ ሆነው እንደነበር ብዙ ሰው አልተረዳም፡፡ እንደተባለው ነው ኢትዮጵያ ያለቸው መከላከያው ውስጥ ነው፡፡ ይሄን የምለው አብይ ዛሬ ስለተናገረለት አደለም፡፡ ቀደም ብዬም ይህን እውነት አንስቼ ነበር፡፡ በዛ ቀውጢ ወቅት ወያኔ እንኩትኩቷ እንዲወጣ የሕዝብ ቁርጠኛ ትግል እንዳለ ሆኖ መከላከያው ውስጥ የነበሩ የሕዝብ ልጆች ግን ዋና ተዋናይ ነበሩ፡፡ እስካሁንም መከላከያ ነው አገሪቱን እያረጋጋ ያለው፡፡ በከተማ ከወሮበሎች ጋር ሲሞዳሞድ የቆየው ፖሊስ አስተዋጾኦ ብዙም አደለም፡፡ ይልቁንም የወንጀሎች አቀናባሪና ወንጀለኞችን ሸሻጊ ነው፡፡

እንግዲህ እንዲህ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ አረመኔያዊ ድርጊቶች በኢትዮጵያውያን ላይ ሲፈጸም የአረመኔውን ቡድን በገንዘብም ሆነ በስነልቦና ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርጉለት የነበሩ መንግስታት ሳይቀሩ ነበሩ፡፡ ከጅምሩ ይህን የሰማናቸውን አይነት አረመኔያዊ ድርጊት የሚፈጽም ወሮበላ አውሬ ቡድን ኢትዮጵያን እንዳይመራ ሲሉ ብዙዎች ግልጽ ተናግረው ነበር፡፡ አውሬው ቡድን እኮ ከመጀመሪያውም ይታወቅ ነበር፡፡ ገና ከጅምሩ ብዙዎችን ሲያርድ የመጣ ነው፡፡ የመጀመሪያው ሰለባ የትግራይ ሕዝብ ነበር፡፡ ሕዝብ ከሚቆጣጠራቸው ወረዳዎች እንዳይወጣ በማድረግ በረሐብ እንዲያልቁ ከማድረጉም በላይ ይሄንኑ የሕዝብ የረሀብ ሰቆቃ ፊልም ሰርቶ እርዳታ የተቀበለና መሳሪያ የገዛ አረመኔ ቡድን ነበር፡፡ በተለያየ ጊዜም ብዙዎችን ባዶ 6 በሚባለው ኦሺዊትስ በምን ዓይነት ሁኔታ ያጠፋቸው እንደነበር ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ሐውዜንን ሆን ብሎ በአውሮፕላን እንድትደበደብ ያገውም ይሄው አውሬ ቡድን ነው፡፡ ይሄን ሁሉ አድርጎ እየታወቅ ምን አይኔን ግንባር ያርገው ማለትን ስለሚችልና ከዛም በላይ ስለሚያስወራ እውነተኛ መረጃዎች ለሕዝብም ሆነ ለሌሎች መንግስታት ግልጽ  አልነበሩም፡፡ በአለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነውን ማውራት ይከብዳል፡፡ ሰዎች ደርግን አረመኔ ያደረጉታል፡፡ እስካሁንም ከደርግ ወያኔ ይሻላል ይሉናል፡፡ አዝናለሁ! ወደፉት ይሄን መሥማት አልፈልግም እስከምንል ድረስ ጉዱን እንሰማለን፡፡ በቁጥረም በግፉ ሰቅጣጭነትም ወያኔን ምድር ላይ ያለ የተኛውም አረመኔ ቡድን አይተካከለውም፡፡ ወያኔ ይሄን እያደረገ ትልልቅ ሚዲያዎችንና የደርጅት መሪዎችን ሳይቀር በገንዘብ እየገዛ ታላቅነቱን ሲያወራልን ነበር፡፡ ኢትዮጵያ የገዳዮቿን ተባባሪዎችም ኪስ ማደለቢያ ነበረች፡፡ ምን አልባት ከኢትዮጵያ ትልቅ የፈረንጅ ባለስልጣን ገንዘብ አይቀበልም ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ እውነታው የምትሰሙት ነው፡፡ በሚሊየን ሳይሆን በቢሊየን ሳይቀር አስላጊ ሲሆን የወያኔ ወሮበላ ቡድን ይከፍል ነበር፡፡ እና ይሄን የሚያሕል ቁጥር ያለው ገንዘብ በየትኛው አገር ለመደለያነት ይሰጣል?

ኤኦኖሚው 11 በመቶ እየተመነደገ ነው ሲሉ አዎ ልክ ነው ኢትዮጵያ የአፍሪካን ኢኮኖሚ እየመራች ነው ሲሉን የነበሩት እንማን እንደነበሩ አስታውሱ፡፡ አይ ኤም ኤፍና የአለም ባንክ ሳይቀሩ ይሄን ይሉን ነበር፡፡ አገሪቱ ግን እንዲህ ባዶዋን እስክትቀር እየተመዘበረች መሆኑን አሳምረው ያውቁ ነበር፡፡ አዝናለሁ! የአሜሪካ መሪዎች ሳይቀሩ በኢትዮጵያውያን የአረመኔዎች ግፍና መከራ እጃቸው አለ፡፡ የአሜሪካ ግብር ከፋዩ ሕዝብ ሊጠይቃቸው ይገባል፡፡ ኦባማ ኢትዮጵያ ሄዶ ሲደንስብን ነበር፡፡ የኦባማ ሴክሬተሪ ጀነራል የነበረችው ራይዝ መቶ በመቶ ወያኔ አሸነፈ እንዴት ይሆናል ስትባል ገለፈጠችብን!! ከአንድ የአሜሪካ ጀነራል ሴክሬተሪ የማይጠበቅ ሕዝብን የመናቅና ለኢትዮጵያ ከዚህ በላይ አያስፈልጋትም ማለት ነበር፡፡ የወያኔ ቀንደኛ ወዳጅ ነበረች፡፡ አሜሪካ ዋነኛ የወያኔ የገንዘብ ምንጭ መሆኗ እንዳለ ሆኖ መሪዎቿ እንዲህ በአለ ሁኔታ ነበር ሲሳለቁብን የነበረው፡፡ እኛ እናልቃለን እነሱ እነሱ በእኛ እልቂት ይገለፍጣሉ! https://www.youtube.com/watch?v=IXFXl4avLVw ፡፡

አሁን የማየው ነገር የሚገርም ነው፡፡ ከዛሬ 27 ዓመት በፊት በደርግ ጊዜ ወደመጨረሻው ከደርግ የባሰ አረመኔ መንግስት ይመጣል ከዛ ቀጥሎ ለኢትዮጵያ ቀን ይወጣል ተብሎ ሲነገር ሰምቼ ነበር፡፡ ይሄ ብቻም አደለም ዛሬ እየተለቃቀሙ ያሉት ሁሉ እንደ ጉም በነው እንደሚጠፉ ሲነገር ነበር፡፡ ይሄን የሚሉት እንደዘመኑ የወሮበላው ነብይ ነን እንደሚሉት እንነ ኢዩ ጩፋ ያሉ የአውሬው አገልጋዮች አደሉም፡፡ እነዚህ ከአገሮቻቸው ጋር ይለቀማሉ፡፡ ይህ አሁን እየሆነ ያለው እውነት ሂደቱን ሁሉ ይገርመኛል፡፡ ለዚህ አስተዋጾ እየደረግን ያለን ካለን የራሳችን ሥራ እንዳይመስለን፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞውንም ግፉ እንዲመጣብን ፍላጎቱ አደለም ወደን ያመጣነው አረመኔያዊነት ነው፡፡ የ60ዎቹ ከሀዲ ትውልድ የጠነሰሰው ጥንስስ ነው ዛሬ ላይ አድጎ የምናየው፡፡ ይሄም ሆኖ አግዚአብሔር ስለብዙዎች ጩኸት ተመለከተ! በሥውር የተፈጸሙ አረመኔያዊ ድርጊቶችን እግዚአብሔር ቆጠረ፡፡ የድኆች ደም እስከመቼ ትታገሳለህ ብሎ ጮኸ፡፡ እግዚአብሔርም ሰማ! የሆነው ይሄ ነው፡፡ አሁን በአለቀ ሰዓት ከአረመነው ቡድን ጋር በማወቅም ባአለማወቅም እየተባበራችሁ ላላችሁ ለራሳችሁ ስትሉ ተጠንቀቁ፡፡ ላደረጋችሁት ንስሀ ግቡ፡፡ በልጅነቴ 6 ጓደኛሞች አንድ በምን እንደሆነ ባላውቅም (ልጅ ስለነበርኩ) በጓደኛቸው ቀንተው በግፍ ይገድሉታል፡፡ እሱን ቢቻ ሳይሆን ነብሰጡር የሆነች ሚስቱን ጭምር፡፡ ትዝ ይለኛል ሕዝብ ሁሉ በአረመኔነታቸው እግዚኦ ነበር ያለው፡፡ ሰዎቹ በግልጽ ስለሚታወቁ ለፍርድ ቀርበው ግን ሰው ስለነበራቸው ከሰባት ዓመት ብቻ በኋላ ይለቀቃሉ፡፡ የሚደንቀው ነገር ስድስቱም በተለያየ ቦታ አገር በሰው ተገደሉ፡፡ ገዳዮቻቸው ይያዙ አይያዙ አላውቅም፡፡ አንዱ ግን የተገደለው እዛው ስለነበር ገዳዮቹ አልታወቁም፡፡ አለመታወቅ ብቻም ሳይሆን አሟሟቱ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ያያል፡፡

የ45 ዓመት የአረመኔ ቡድን ምዕራፍ እየተዘጋ ነው፡፡ አረመኔ ፈሪ መሆኑ ነው አረመኔ የሚያደርገው፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዲሀ በአሉ አረመኔያዊ ደርጊቶች እያስፈራራ ነው የኖረው፡፡ ሕዝብን በዘር መከፋፈል ትልቅ ጉልበቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የወያኔ የሆኑን ነገሮች ሁሉ አራግፋ የራሷ የሆኑትን እንድትመለስ እንድታስተካክል ግድ ይላታል፡፡ የዘር ፖለቲካን ሙጥኝ የሚሉ ለምንና እነማን ናቸው? ዘር ውስጥ እየተደበቁ እንዲህ ያለ አረመኔያዊ ድርጊት ለመፈጸም፣ ለመዝረፍ እንዲመቻቸው ነው፡፡ በመሆኑም ለእነ አብይ እላለሁ

  1. በየትም አገር ይሁን የት በሕዝብና አገር ላይ ግፍ ሲፈጽሙ የነበሩ በዓለም አቀፍ አሰሳ (ኢንተር ፖል) ተለቅመው እንዲያዙ፡፡ ያደረሱት አረመኔያዊ ድርጊት የተባበሩትን መንግስታት ሳይቀር ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል ነው፡፡ ምክነያቱ እንደነዚህ ያሉ አረመኔያዊ ድርጊት የሚፈፅም ቡድን አባላትን ሳይቀር የደርጅቱ አባልና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾሟል
  2. ኢትዮጵያ በአስቸኳይ የቴድሮስ አድሀኖምን በአረመኔያዊው ቡድን አባልነት የነበረውን ተሳትፎ አጣርታ በየትኛውም ድርጊት ተሳታፊ ሆኖ ከነበር ለተባበሩት መንግስታት ከሥልጣኑ እንዲነሳና ድርጊቱ በሚያስጠይቀው ሁኔታ ለሕግ እንዲቀርብ፡፡ እኔ ቴድሮስን ከደገፍኩት ነኝ ግን አሁን የምንሰማቸው አረመኔያዊ ድርጊቶች ሲፈጸሙ አንዱ ተባባሪ እንደነበር የሚያሳዩ ፍንጮች እየወጡ ነው፡፡
  3. በአረመነኔው ቡድን መሪዎችና በዘመዶቻቸው ስም ያለ በየትም አገር ቢሆን ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ማገድ፡፡ ብዙዎች ዘመዶቻቸውን በሌሎች አገሮች ባለሀብት አድርገው እያኖሩ ነው፡፡ ለምሳሌ በአውስትራሊያ በአሜሪካ
  4. ከአረመኔው ቡድን ጋር የሚንቀሳቀሱ ሌሎች አጋር ቡድኖችን መመርመርና ለሕግ ማቅረብ ቀሪዎቹም አደብ እንዲገዙ ቁርጠኛ ማስጠንቀቂያ መስጠት፡፡
  5. በአረመኔያዊው ቡድን በሚሰጣቸው ገንዘብ የሚንቀሳቀሱ በየአገራቱ ያሉ ሚዲያዎች በየአገራቱ መንግስታት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማስደረግ፡፡ ይሄ የፕሬስ ነጻነት ከሚባለው ጋር እንዳይምታታ፡፡ የአረመኔውን ቡድን ፕሮፓጋንዳ መንዛት ወንጀለኝነት እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ በሰው ልጅ ላይ ይደረጋል ተብሎ የማይታሰብ አረመኔያዊ ድርጊት የሚፈጽምን ቡድን ፕሮፓጋንዳ የሚነዛ የሰው ዘር ጠላት ነው!

ሌሎችም ወሳኝ እርምጃዎችን በመውሰድ እግረ መንገድንም ሕዝብን ወደ ኢትዮጵያዊነት ስነልቦናና ባሕል እሴቶች መመለስ ግድ ይላል፡፡ ዛሬ ብዙ ትውልድ ከማንነት ጠፍቶ ማንም እንደፈለገው የሚዘውረው ነው፡፡ ፑቲን ከየልሲን ሥልጣን ሲቀበል ከሰራቸው ነገሮች አንዱ በዱርየነት እየበዛ የመጣውን የራሺያን ወጣት በራሺያ አገር ወዳድ ስነልቦናና በራሺያ እሴቶች መገንባት ነበር፡፡ እነ የልሲን ስንፍና እንጂ አገር አጥፊነት መንፈስ አልነበራቸውም፡፡ 27 ዓመት ኢትዮጵያን ዋሻ ያደረገው አረመኔው ቡድን ግን ኢትዮጵያዊ የሆኑ ማሕበራዊም ሆነ ስነልቦናዊ እሴቶችን ሙሉ በሙሉ በማውደም ላይ ነበር ትኩረት አድርጎ ሲሰራ የነበረው፡፡  ዛሬ የሥልጣን እድል የገጠማችሁ ይሔን እድል እንድትጠቀሙበት ነው፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ዛሬ ከተያዘው የአረመኔው ቡድን አባል ጋር ሌላው የኢንሳ ዳይሬክተር የሚባለው፣ ሳይገደል እንዳልቀረ ይነገራል፡፡ እርግጠኛ አደለሁም እኔ! ሰዎቹ ሲያዙ ዝም ብለው እጅ የሰጡ አልመሰለኝም በኋላ ያየንው ፊልም አይነት አይመስልም፡፡ ሰውዬው መቀሌ ገብቶ ሲፎክር ነበር፡፡ ለማንኛውም ከሞተም እሱ የሞተው በጥየት ነው ብዙዎችን ግን ለጆሮ በሚሰቀጥጥ ሁኔታ እንያልቁ ከአደረጉት ነው፡፡  አንዳንዶች በመረጃ እኔ ነኝ እኔ ነኝ የምትሉ ብትታቀቡ ጥሩ ነው፡፡ ያደረጋችሁት ነገር ከአለ ግዴታችሁ ነበር እንጂ ለመታወቅ ከሆነ ባታደርጉት በነበረ መልካም ነው!

ኃያሉ አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርከ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ