ሲያስቧቸው የሚያስጨንቁ ምስጢሮች;
ህወሓቶች ሀገር ከተቆጣጠሩ በኋላ ከሱዳን ጋር በመመሳጠር/በመተባበር ከጀርባ ገብተው የማረኳቸውን የኢህአፓ/ሠ አዛዦችና ተዋጊዎች የነበሩትን እነፀጋዬ ገብረመድህንን (ደብተራውን) የት እንዳደረሷቸው ይንገሩን!?ድራሻቸውን ስላጠፏቸው ሌሎች በርካታ የፖለቲካ ሰዎችም ይነገረን!? በህይወት አሉ? ወይስ ተገድለዋል? ወይስ የሆነ ዋሻ ውስጥ ደብቀዋቸዋል? እንደሰው ማሰብና መንቀሳቀስ ይችላሉ? ወይስ የቁም በድን አድርገው አስቀምጠዋቸዋል? የትግራይ ምድር በሆዷ ስንቱን ከባድ ምስጢር አርግዛ; እስከመቼ ታምጣለች? እነዚህና የመሳሰሉትኮ ሊያስቧቸውም የሚያስጨንቁ ምስጢሮች ናቸው። ለሀገርና ለህዝብ ብለው የወጣትነት ዕድሜያቸውን በትግል ስላሳለፉ የህዝብ ልጆች “ፍትህ” ቢቀር መረጃ ይሰጠን!?
የተዳፈኑ የግፍና ጭካኔ ምስጢሮች ይውጡ