November 14, 2018

መንበረ ካሳየ

ከ2006 እስከ 2007 ዓ/ም የመሬት መጠቀሚያ ኪራይ አልከፈላችሁም በሚል የወጣ ማስታወቂያ ነው ። የስም ዝርዝሩን ስትመለከቱ የአንድ ብሔር የበላይነት ይታይበታል ። ምናልባት የህወሃት ባለስልጣናት ቤተሰብ እና በጥቅም የተሳሰሩም ጭምር ሊሆኑ ይችላሉ ። የጋንቤላ ህዝብ በገዛ መሬቱ ተፈናቅሏል ተጨፍጭፏልም ።

አዲሱ የጋንቤላ ክልል ፕሬዝደንት ያላግባብ የታሰሩ በርካታ ሰዎችን ከእስር መፍታታቸውን ያለፈው ሳምንት ሰምቼ ነበር። ቀጣዩ ስራ ደግሞ ያላግባብ የተዘረፉ መሬቶችን ለህዝብ እንዲመለሱ የሚሰሩ ቢሆን ጥሩ ይሆናል ።