ከሜቴክ የሚበልጥ ከዚህ አለ።!!!!!!!
ሰው ከገንዘብም ከተቋምም በላይ ነው ።ምንም ድሀ ብሆንም ይህን ሀቅ አንክደውም።
ሰው ስንል እራሳችን የመጣንበትና የተገኘንበት መንገድ ማለት ነው።ወይም እኔ እኛ የሚለው አቅራቢ ቃላትን መጠቀም ነው።ገንዘብ በሰው የሚሰራ ነው። ሰው ግን ሰሪውም ሆነ አስገኙ ከሰው በላይ ነው።በሰው መገኘት የሰው ድርሻ ፈቃዱን ወይም ጊዜው ፍላጎቱን መፈጸም ነው።
ይህ ከሆነ ሰው የአስገኙ እንጅ የአጋጣሚ ጉዴይ አይደለም ሊሆንም አይችልም።
ሰሞኑን ቁጭትና ንዴት በህዝቦች መካከል ገኖ ወጥቴል። ምክንያቱ ደግሞ የሀገር ገንዘብ ጠፍቶ ነው ወይም ተዘርፎ ነው።ሀገርን የሚያስጠራው ክቡር ፍጥረት አልጠፋም እንዴ? ምነው ቸል ተባለ ? ያውም ሊቅ ለትውልድ የሚተርፍ እውቀት ያለው ስንል እኛም ትዝብታችን ከትበናል ።
የሀገራችን እንቆቅልሽ ተነግሮም ተጽፎም አያልቅም።ሲያስቡትም ያደክማል።
የታላቁ ሊቅ እንደስራቸውን የእስር እንቆቅልሽን መፍታት አቅቶን ያገር ያለህ ካልን ወራት ተቆጥሯል።ሊቁን መነሻ እድርግን እንጅ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እንደ ወጡ የቀሩ ሰዎች በርካታ ናቸው።
ሊቁ እንደሥራቸው ለሥራ ወጥቶ ከሥራ ሲመለስ ታፍኖ ከአዲ ረመጽ እስከ ሽሬሮ ባሉ የምድር ውስጥ እስርቤት መኖር ከጀመረ 25 አመታትን አስቆጥሯል።በዚህ አካባቢ መታሰሩ የታወቀው ከሁለት ዓመት በፊት ኑው።
የመልስ ፋውንዴሽ ምክትል ዳሪክተር የሆነ ሰው የዶክትሬት ድግሪውን ማሟያ የጥናት ጽሁፍ ለማቅርብ በተዘጋጀበት ወቅት የጥናቱ ሥራና የአከናዎነበትን ቦታ ለማስጎብኘት አማካሪው /አድባይዙሩ /የነበሩ አንድ ህንዳዊ መምህርና ሌላ ኢትዮጵያዊ መምህርን ወደጥናት ቦታው ወስዶ ሲያስጎበኝ፤ የኢትዮጵያዊዩ መምህር የትውልድ መንደርና አብሮ አደግ ፤አንድ የተበሳቆለ ሰው መጥቶ እኔ እንደሥራቸው ነኝ አንተ እከሌ አይደለህም ብሎ ይጠይቀዋል። በሁኔታው ግራ የተጋባውና በአየው ሰው የተረበሸው መምህርም መሆኑን አምኖ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ለቤተሰብእ መልክት ለማድረስ ተስማምተው ይለያያሉ።
በወቅቱ ከአሜሪካን ሂደውና ሲቢል ስርቢስ ኮሌጅ የሚያስተምረው መምህር ወደ ትውልድ መንደራቸው አቅንተው ሁኔታውን ለመግለጽ ቢሞክር አባት ናት ከአለም ተለይተዋል። የእንደሥራቸው ልጆችና ሚስትም በቤት ችግር ከቀበሌ ቀበሌ በመዛወራቸው ሳይሳካ ቀረ። ይሁን እንጅ ወሬው ተሰራጭቶ ከሁለት ዓመት በኋላ ሚዲያ ላይ ዋለ። እኔም ድሮ ስለሊቁ የሰማሁ በመሆኔ በግንባር ያገኘውን ሰው በማገኘት ስለሁኔታው ለማወቅ በቃሁ። በሰማሁት ነገር እጅግ ከአዘንኩባቸው ቀኖች አንዱ ነበር። ሰው ሳይሞት እንደሞተ መሬት ውስጥ ሩብ ምእት ዓመት መኖሩን ሳስብ ዛሬ እረበሻለሁ።
ጉዳዩን በከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ለማድረስ ከዳንኤል ክብረት ጋር መረጃ ተለዋወጥን።ዳንኤልም በሁኔታው ገፍቶበት ነበር።በአካል ያገኘው ሰው ምንጊዜም የትም ቦታ ሁኔታውን ለማስረዴት ዝግጁ ነኝ አለ። የመንግሥት ባለሥልጣናት ትግራይ ውስጥ ችግር ስለአለ ታገሱን አሉ ተባለ።ቆይቶም ቦታው የት ነው አሉን የሚል ወሬ መጣ። መንግሥት ግዛቱንና ወሰኑ በግዛቱ ውስጥ ያለው እስርቤት እንዴት አያውቅም ከማለት ይልቅ የለውጥ ሃይሉ መረጃ ላይኖረው ይችላል በሚል በበጎ ጎኑ ተቀበልነው።
የሄዱት ሰዎች እንግዶች ናቸው።በጎንደር ሆመራ መንገድ መሄዳቸውንና ከሽራሮ አለማለፋቸውን ብቻ እንደሚያውቁ ትግራይ ውስጥ መሆኑን አስረግጠው ከእነ አካባቢው ነገሩን።በአካባቢው ሦስት የምድር ውስጥ እስርቤቶች እንዳሉ ሌሎች አካባቢውን የሚያውቁ ለጨማሪ ማስረጃ አነጋግረን አረጋገጡልን።
እንደሥራቸው በታሰረበት የመሬት ውስጥ እስር ቤት መልካቸው የወየበ፤የጽሐይ ብርሃን የናፈቃቸው ከሁለት ሺህ በላይ እስረኞች እንዳሉ ከስር ቤቱ ገብተው ይወጡት ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ከሜቴክ ሰው ይበልጣል ።ሰባዊነት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።ሞቱ ተብለው አልቅሰው ያልቀበሯቸው ቤተሰቦች ከነገ ዛሬ ይመጣሉ እያሉ ይጠብቃሉ። ይህ በእኔ ቤተሰብእ ቢሆን በሎ ማሰብ ያስፈልጋል። በሕይዎት መኖሩን የሰሙ ቤተሰቦች እንደ እስረኛ እንኳን እንዴት መጠየቅ አይችሉም?። መንግሥት ሆይ አቅም እየጠነከር ከሄደ፤ ከጠፋ ገንዘብ ይልቅ ክቡር የሆነው የሰው ሕይዎት ይበልጣልና።ብጫዋ ሄሊኮፍተር ሁመራ ከደረስች የሚታሰሩት ብቻ ሳሆን መሬት ውስጥ የታሰሩትም ታምጣ ።እነዚያ የምድር ውስጥ እስርቤቶች ለሚዲያ ክፍት ይሁኑ። መቼም ሰምተን ማዕዘን ነው።እባካቹሁ ሁሉንም በእወነተኛ መንገድና በጊዜው ንገሩን።
መረጃው የfredemis ነው።
Daniel Kibret
Zemedkun Bekele B
Getachew Shiferaw
Amhara Democratic Party /ADP/ CC office
ANRS Communication Affairs OfficeJustice