ብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚገምት ሀብትና ንብርት የያዘው  ኤፈርት ( EFFORT:   Endowment Fund For Rehabilitation of Tigray) ተብሎ የሚጠራው የብዙ ኩባንያ ባለቤት ህግወጥ በሆነ መልክ በማፊያ  ንግድ ስራ ላይ ተስማርቶ በአገራችን ትልቅ  የኢኮኖሚ ድርሻ በብዙ እጅ ተቆጣጥሯል። ንብርትንቱ   የህወሃት ቁንጮ ባለስልጣኖች  ሲሆን   በቢዝንስ አለም የማይታሰብና የማይገመት አሰራርና ህግ እየጣሰ ባለቤቶቹን  ሃብታም እያደርገ ያለ የንግድ ድርጅት ነው። ህወሃት  ኢትዮጵያውያን ላይ ላድርገውና ለሚያደርገው የጥፍት ስራ ዋና የገንዝብ ምንጭና  ከፋይ ነው።  በአገራችን ካሉ ኩባንያዎች ሁሉ በሃብትና ንብርቱ  ተወዳዳሪ የሌለው በቁጥር ፩ ላይ የሚገኝ የንግድ ድርጅት ነው።

ይሄ የማፍያ  ድርጅት “የደም ገንዝብ” በሚባልም ስም ይጠራል። ገና ሲቋቋም የሃብት ጅማሬ ምንጩ በዝርፊያ የተገኘ የህዝብና የመንግስት  ገንዝብ ነው። በ 1960 መጨረሻዎቹ  ህውሃት ገና በሽፍትነት በትግራይ በርሃ በምትንቀሳቀበት ግዜ  የቀድሞ መሪውን መለሰ ዜናዊን ጨምሮ በአድዋ እና አክሱም ከተማ የነበሩ የ ኢትዮጲያ ንግድ ባንክን  ሰብረው የዘርፉት የሌብነት ገንዝብ ነብር። እንድ ጅብ በምሽት እየመጡ በትግራይ የነብሩ ሃብታም ነጋዴውችን እያስፈራሩ እና እየገደሉ የሚዘርፉት  በትግራይ ውስጥ የነብሩትን የህዝብና የመንግስት ድርጅቶችን ሰብረው የሚገኝውን ገንዝብና ንብርት  ዘርፈው ወደ በርሃ  በሚሮጡበት ስልታቸው ነበር።

ከሁሉም በላይ ግን ትልቅ የገንዘብ ምንጭ የሆነው በማጭበርበር ስራቸው ነበር ። 1977 በሰሜን ኢትዮጲያ በተለይም በትግራይ በተከሰተው አስከፊ ርሃብና ድርቅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ  የትግራይ ኢትዮጲያውያን ህጻናት፣ ሴቶች ፣አርጋውያን በርሃብ ተጎሳቅለው እንደ ቅጠል በሚገርፉበት  ግዜ ለህዝቡ እርዳታ የተለገሰውን ገንዝብ  በማጭበርበር ዘዴያቸው  ገንዝቡን ለራሳቸው ለኤፈርት ማድርጋቸው ነበር ።

ቢቢሲ (BBC) ቲሌቭዥን  ያን ግዜ በአለም ያስርጨው  አሰቃቂ የድርቅና የርሃብ ሰቆቃ   ወገኖቻችን  እንድቅጠል ሲርግፉና የርሃብን ሳል ሲስሉ፣ ከብቶቻቸው አጽም ና የእርሻ መሪት ደርቆ ሲታይ ብዙ  የአለም ህዝብን አሳዝኗል። ይህን የተመለከቱ  ወጣቱ አይርላንዳዊ  ዘፋኝ ቦብ ጌልዶፍ   ና ጋደኞቹ  “ገናን ያውቃሉ ወይ?” የሚል ሙዚቃ በ 1977 አዘጋጅተው ቦኋላም ከሞያ ጉደኞቻቸው ጋ ተባብረው በዛን ወቅት በአለም ታዋቂ የነበሩ ዘፋኞችን ያካተተ “We are the World” የሚል የሙዚቃ ኮንሰርት በተዋቂው ዌንብሌይ ስታደየምና በሌሎች ቦታዎች በአለም ዙሪያ በቴሊቭዥን በቀጥታ በተሰራጨ  ዝግጅት ከ 100 ሚሊዮን ብሪትሽ ፓውንድ በላይ  የተሰብሰበው በድርቅ ለተጠቁት አፍሪካውያን የሚል ሲሆን በዋናነት ግን  ለኢትዮጵያ ነበር።

ቦብ ጌልድፍና ጓድኞቹ ከሰበስቡት ገንዝብ 100 ሚሊዮን ዶላር  ያኔ በትግራይ እየረገፉ ላሉት ወገኖቻችን የእህል መግዣ እንዲሆን አስበው ሱዳን ኢትዮጲያ ድንብር ሲወርዱ የህውሃት  ብልጣብልጦች  በብዙ ጆንያ አሸዋ ሞልተው  ከፊት ለፊት ትንሽ ጆንያ ስንዴና ጤፍ አደርገው  አጨበርበርው 100  ሚሊዮን ዶላሩን ተርከበዋል።  ይህ ገንዝብ ለህዝቡ ቢደርስ ኖሮ  በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ ወገⶈቻን ክሞት ይተርፉ ነበር። ወያኔ ግን ለመሳርያ መግዣ ና ያኔ ሊመሰርተው ለነበርው ኮምኒስት ፓርቲ (ማሌሊት) ማስፋፍያና የጥቂቶች የግል ንብርት ለነበርው ኤፈርት ካዝና ኧድርጎታል። ይህ ቆመንለታል ለሚሉት የትግራይን ህዝብ ካፉ ላይ የተሰጠውን እርዳታ ነጠቀው ለሞት ዳርገውት እንሱ አሁን ለሚኩራሩበት የሃብታቸው ምንጭ ለሆነው ኤፈርት አድርገውታል። ለዚህም ነው ይህንን ታሪክ የሚያውቁ ወገኖች ኤፍርትን “የደም ገንዝብ” የሚሉት።

ህወሃት ተጠናክሮ በጦርነት ብዙ  መሬት መያዝና የቀድሞው መንግስት ከተሞችን ለቆ በመውጣቱ  ወያኔ በያዛቸው ከተሞች የሚገኙትን የህዝብ ድርጅት የሆኑ የንግድ ድርጅቶችን፣ የመንግስት መስሪያ ቤት ንብርቶችን ገንዝብን ዘርፎ ለኤፈሪት በብዙ ቢሊዮን የሚገመት ሃብት ወደ  ካዝና ከⶆል። ከትግራይ እስክ አዲስ አበባ እስክሚደርስ የዘርፋቸው የመንግስትና የህዝብ ንብርት ስፍርና ቁጠር የለውም። ሃላፊነት የሚሰማው ፓርቲ ቢሆን ኖሮ ይህን የዘረፈውን የህዝብና የ መንግስት ንብርትና ሃብት ራሱ ለሚቆጣጠርው መንግስት መመልስ ይችል ነበር። ወያኔ ግን መንግስትም ሆኖ ከርሱ ስለማይሞላ አላደረገውም።

1983 የቀድሞው መንግስት መጨረሻ ቀናት ውስጥ “Operation Solomon” በሚባል በሚታወቀው  ዘምቻ ኢትዮጲያውያን ፈላሻዎችን ወደ እስራል ለማጓጓዝ መብት ለነብረው የኢትዮጲያ አየር መንግድ  ካሳ እንዲሆን  ተብሎ የተከፈለው 26 ሚሊዮን ዶላር ኒዎዮርክ ባለው ባንክ የኢትዮጵያ መንግስት ባንክ አካውንት ገብቶ ነበር። ስልጣኑን የተረከበው ወያኔ መራሹ መንግስት በዛን ወቅት የሽግግሩ መንግስት ፕሬዝዳንት መለስ ዜናዊ  ቀጥታ ትዛዝ ገንዝቡ ለመንግስት ወይም ለአየር መንገዱ ገቢ መሆን ሲገባው ለግል ድርጅታቸው ኤፊረት ካዛና እንዳስገቡት በቅርብ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ሚስጥሩን አጋልጠዋል።

በዚ መልክ በዝርፊያ፣ በማጭበርበር፣ በሌብነት እና ስልጣን ብልግና የተከማቸ ገንዝብ (የደም ገንዝብ) የተቋቋመው ኤፈርት ወያኔ መንግስት ከሆነ ቦኋላ  የተራዳኦ ድርጅት ነኝ ብሎ እጅና እግሩን የገንዘብ አካፋ አሲይዞ የአገርን ሃብት ለመዝርፍ በንግድ ድርጅትነት ተመዝግቦ ፡ በመንግስት ቀጥታ ትዛዝና እርዳታ ወደ አኪኖሚው ሜዳ ገብቶ ብዙ ኩባንያዎችን አቑቁሞ ሌሎችን ተፎካክሪ የንግድ ድርጅቶችን ከሜዳ አስወጥቶ በ ሞኖፖል የንግዱን፣ የኮንስትርክሽን ፣የፋብሪካ ውጢቶችን፣ የትራንስፖርት፣ የእርሻ፣ የባንክ፣  የማእድን እንዲሁም በብዙ የኤኮኖሚው መስክ ተሰማርቷል።

ቀድሞ የዘረፉት አልበቃ ብሎቸው መንግስት ከሆኑ ቦኋላ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ቀጥታ ትዛዝ  የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አንዲሁም የኢትዮጲያ ልማት ባንክ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ ብድር እንዲስጣቸው በማደርገ፤ ቦኋላም ባንኮቹ ከግዜ ቦኋላ ገንዝባቸውን ለመሰብስብ ቢጥሩም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዛዝ የተበላሸ ብድር ተብሎ እንዲሰርዝላቸው በማደርግ  ይቅርታ ሊድርግልት የማይገባ የአገርና የህዝብን ትልቅ ገንዘብ ለራሳቸው አውለውታል።  (ስልዚህ ጉዳይ በይበልጥ ለማወቅ  ከፈልጉ የቀድሞ የ መንግስት ዲኤታ ሚኒስቴር የነበርውን ኤርሚያስ ለገሰ የጻፈውን “የመልስ ልቃቂት”የሚለውን መጽሃፍ ያንብቡ)

ይህ ማፍያ የሆነ የንግድ ድርጅት ባለቤቶቹ  እያንዳዳቸው በቢሊዮን የሚቆጥሩ ገንዝብ ሃብትም ያደርግቸው ሲሆን  ድርጅቱ በስሩ አቅፎ የያዛቸው ብዙ ካምፓኒዎች የሚመሩት በ ትግራይ ተውላጆች ብቻ በሆኑ  ስራ-አስⷋያጆች  ነው። በመላ ኢትዮጲያ የተንስራፋው ይህ የንግድ ድርጅት አብዛኞቹ ተቀጣሪ ሰራትኞች ደሞ ወያኔን የሚደግፉ ትግራውያን ናቸው።  የተራዶኦ ድርጅት ነኝ እያለ እንድሌሎቹ ህጋዊ የንግድ ካምፓኒዎች  በስን ስርአት ተገቢውን ቀረጥ  የማይከፍልና  ለይስሙላ  ኦዲት የሚደርገ  የ ህውሃት የንግድ ድርጅት ነው። ራሳቸው ያወጡት ህገ-መንግስት ራሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በንግድ ስራ እንዳይግቡ ቢያግድም ህውሃት ግን  በ 10 ጣቱ ገብቶበታል። በትግራይ ህዝብ ስም የሚነግድው ይህ የጥቂት የህውሃት ቁንጮ ስዎች ንብርት የሆነው ለአብዘኛው የትግራይ ህዝብ ፋይዳ ያለው ነገር ያልሰራ፤ የትግራይ ህዝብ የተረፈው ከሌላው ኢትዮጲያዊ  ወንድሙና እህቱ የማይገባውን ጥርጣሬና እምንት ማጣትን ነው።

ህወሃት ፖለቲካውን፣ መከላⷋያውን፣የጸጥታ ና መርጃ ስራውን፣ የውጭ-ግንኙንት እንዱሁም ወሳኝ የህብርተስቡን አንቀሳቃሽ ክፍሎች በዋናነት መቆጣጠርና መምራት  መጀመርያ ስልጣን ሲይዝ ያደርገው እቅድና ቦኋላም  ተግባር ያዋለው ነው።  ኤኮኖሚውን እንዲቆጣጠር ደግሞ ኤፈርት ድርሻ ተሰጥቶት ነበር።  ባሁኑ ግዚ ወሳኝ የሆኑ የአገራችንን  የኢኮኖሚ  ድርሻና ተቁሞች ይዧል። በዚህም በህውሃት የተሰጠውን ግብ አሟልቷል።

የህውሃት ስልጣንን ለዘምናት  እንዲቀጥልና የሚገጥሙትን ተቃውሞች ሁሉ ለመደምሰስ የመንግስትን አካላትን  ህግወጥ በሆነ መንግድ በ መጠቀም 27  አመት ሲዘልቅ  በተጨምሪም በድብቅ ህውሃት ለሚሰራው መስሪና አስከፊ ስራው ኤፍረት የገንዝብ ከፋይ ምንጩ ነው።

ባለፉት 7-8  ወራት በአገራችን የሚታየው  የ ፖለቲካ ለውጥ ሂደትን ለማጨናጋፍ እና አገር ለማፈርስ፣ ህዝብን በህዝብ ማጋጨት አፍራሽ ድርጊቶች በመላ አገርችን በቀጥታ ና በድብቅ የሚደርጉ ሁከቶችን ማን እንድሚያስተባብረው  ያደባባይ ሚስጥር ነው። የገንዝብ ምንጩም እንግዲህ ግልጽ ነው። በኢትዮጲያ ውስጥ በሃብቱ ቁጥር አንደኛ የሆነው የማፍያው የንግድ ድርጅት ኤፌርት የባለቤቶቹን ጥቅም ለማስከበር የማያደርገው የለም።

አሁን ያለው በዶ/ር አብይ አህመድ  የሚመራው  የኢትዮጲያ መንግስት ይህን ህገ-ወጥ የማፍያ ካምፓኒ  በዝርፍያ፣ በማጭበርበር ፣ በነጠቃ፣ በደም ገንዝብ የተመሰርትና በባለስልጣኖች እገዛና ጥበቃ  እዚ ደርጃ ላይ የደርሰውን የጥቂት የህውሃት ቁንጮ ባልስልጣኖች ንብረት የሆነውን ኤፈርትን  በህግ በመወርስ የህዝብ  እንዲያደርግ ወይም ማፈራርስ አለበት! ይህንንም በማድርግ ለወንጆለኞቹ የሚፈሰውን የሃብት ምንጭ በማድርቅ በሃገራችን የሚያደርጉትን አደጋ ና እንቅፋት መልክ ለማስያዝና ሰላማዊ የፖለቲካ ለውጡን ምህዳር  ይረዳል። የንግዱም ማሃበረስብ ፍትሃዊ በሆን መንግድ ንግዱን ለማከናውን ይርዳዋል።