ለክቡር ዶ/ር አቢይ አህመድ

የኢ...ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የዘለቄታ ጥቅም ቀዳሚ ነው የሚለውን እሳቤ ከግምት በማስገባትና እቅድ በመንደፍ ለሀገርዎ ለኢትዮጵያ ያለዎትን ራዕይ ከሕዝቡ ፣ ዳያስፖራው ን ጨምሮ፣ ለማገናኘት ከተቻለም ለማዋሀድ በመውሰድ ላይ ባሉት ቆራጥ እርምጃ ያልተደነቀና የልተደሰተ ያለ አይመስለንም። ይህ የአርቆ አስተዋይነትና በሥራ የመተርጎም ውሳኔዎና የሚወስዱት እርምጃዎቾ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አዲስ የታሪክ ምእራፍ ከፋች ያደርግዎታል። ይህንን ስለእርስዎ የተሰጠውን አስተያየት ሐቅ መሆኑን ይህ ከመስክረም 23 ቀን እስክ 25 ቀን 2011 .ም በአዋሳ ከተማ በተደረገው 11ኛ ጉባኤ በሙሉ ድምጽ ለሊቀመንበርነት መመረጥዎ ታሪካዊ ምስክር ነው። በሰሜን አሜሪካ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ፊትለፊት ተገናኝቶ በሃገር ጉዳይ ለመወያየትና ለመመካከር በናፍቆት አቅደው በመምጣትዎ የኢትዮጵያ ሰላምና እርቅ ምክር ቤት፣ ይህን ያልተለመደ ተግባር በመፈጸምዎ ጥልቅ የሆነ ምስጋናውን በትህትናና በአክብሮት ያቀርብልዎታል።

የኢትዮጵያ ሰላምና እርቅ ምክር ቤት ሰለደህንነትዎ በጥንቃቄ መጠበቅና ስለጤንነትዎ መሟላት ምንጊዜም ክሚያስብልዎትና ከሚመኙት አድናቂና አክባሪ ወገኖችዎ ውስጥ አንዱ ነው። ካለብዎት ኃለፊነት ጥልቀትና ስፋት ፣ ከሚወስዷቸው ቆራጥና ወሳኝ እርምጃዎች አንጻር በተለይ የደህንነቱ ጉዳይ ምንጊዜም ተሟልቶ መገኘቱ እጅግ በጣም ወሳኝ መሆኑን ለማሳሳብ እንወዳለን።

ይህን የዳያስፖራውን ታሪካዊ ጉዞ አንዱ ልዩ የሚያደርገው ጉዳይ፣ የጉብኝትዎ እቅድና ትኩረት በውጪ መንግሥታት ላይ ሳይሆን፣ ብዙጊዜ በተለይ አዲስ ሥልጣን በያዙ መሪዎች የተለመደው በቅድሚያ ይህን ማድረጉ ስለሆነ፣ እርስዎ ግን በናፍቆት ገስግሰው ለመገናኘት ወደፈለጉት ወደኢትዮጵያውያኑ ላይ ነበረ። ይህ ድርጊትዎ የአሜሪካንን መንግሥት ጭምር ሳያስገርም አይቀርም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ያህል ኩሩና የተለማማጭነት ጠባይ ፈጽሞ እንደሌለው ክቡርነትዎ በተግባር አስመስክረዋል። በዚህ ድርጊትዎ ራስዎንና ኢትዮጵያን አስከብረዋል፣ አኩርተዋልም። አሜሪካ ወደፊት፣ ማለትም ከአርስዎ ጉብኝት በኋላ ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራት ግንኙነት ዞሮዞሮ እንደማንኛውም አገር የራስዋን ጥቅም ለማስጠበቅ ስለሆነ ምንም የሚያሰጋ ነገር አይኖርም።

የሰሜን አሜሪካው ጉብኝትዎ ባስከተለው ውይይትና ምክክር ምክንያት፣ ወደሌላውም ዓለም ወይም አህጉራት በሚኖረው ኢትዮጵያዊ ተስተጋብቶና ጆሮ አግኝቶ ሐገራዊ ስሜቱንና መንፈሱን በማነሳሳት ትኩረቱን ሙሉበሙሉ ወደአገሩ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያደርግ አነቃቅቶታል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣እነዚህ ሀሳብ ለሀሳብ ከመለዋወጥና ከመመካከር፣ ከጥያቄና መልስም በኋላ የተገኙ ፣ ከነበሩም የዳበሩት፣ የፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የማህበራዊና የሰላሙ የአስተሳሰብ አዎንታዊ ለውጥ ሁኔታ በዳያስፖራው ውስጥ እንዲስተጋባ ማድረግ መቻሉ በቀላል የሚገመት አይደለም። በአሁኑ ጊዜ፣ ዶር አቢይ በሚያስተዳድሩበት መንግሥት ስር፣በሚደረገው ያላቋረጠ ዘመቻ ምክንያት፣ በየአህጉሩ የሚገኘው ዳያስፖራው፣

) ጥናትና ምርምርን ባዘለ ሃሳብ ፣

) ለልማት በሚጠቅም የምርት መሳሪያነት፣ ለኢትዮጵያ፣ የማያቋርጥ ምንጭ ለመሆን በናፍቆት የተዘጋጀ መሆኑ እየታየ ነው።ይህን የመሰለ፣ በኢኮኖሚውና በማህበራዊው ዘርፎች ዙሪያ የበሰለ ምንጭ ሆኖ የመገኘትን ሁኔታ ያለማመንታት እቅድ አዘጋጅቶ ከስራ ጋር ማጣመድና ማቀናበር እጅግ በጣም ይጠቅማል።

በተለይ የዳያስፖራውን ተሳትፎ በተመለከተ፣ እንደዚህ እንደእርስዎ፣ በጉጉትና በቆራጥነት፣ በፍቅርና በቅን መንፈስ ለወደፊት ኢትየጵያን ለሚያስተዳድር መሪ መሰረት ጥለውለታል። ይህን በአጭር ጊዜ ውስጥ በተለያዩ አህጉራት የሚገኙትን ኢትዮጵያኖች ጭምር በመንፈስና በስጋ ያካተተ ታረካዊ ጉዞና ጉብኝት በመፈጸምዎ፣ ተራርቆ የነበረውን ሕብረተሰብ፣ ለመሳሌ በሚኖሶታ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ መጥቀስ ይቻላል፣ በሚያስደንቅ ሁኔታ በማቀራረብዎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከልብ እንደ ሚያመሰግንዎት፣ የኢትዮጵያ ሰላምና እርቅ ምክር ቤት በእርግጠኛነት መመስክር ይችላል።

ከቡርነትዎ እዚህ አሜረካ በነበሩበት ጊዜ፣ ዳያስፖራው ከእርስዎ ጋር ካደረገው ውይይትና ምክክር በመነሳት፤

) በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በማህበራዊውና በሰላሙ መስኮች ላይና ዙሪያ ባተኮሩ ምክክሮችና ውይይቶች፣ በተሰነዘሩ ጥያቄዎችና በተገኙ አጥጋቢ መልሶች ላይ በመመርኮዝ፣

) ቀንተቀን በግንባር ቀደምትነት፣ በቆራጥነት፣ በትእግስትና በዘዴ፣ ለሕይወትዎ ሳይሳሱ ተጋፍጠው በወሰዷቸው ና በሚወስዷቸው እርምጃዎች ላይ በመመርኮዝ፣ ይህችን የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን የመምራት ችሎታና ብቃት እንዳለዎት ዳያስፖራው ያለምንም ጥርጣሬ አምኖበታል። ፊቱን ወደእናት አገሩ ወደ ኢትዮጵያ የማዞር ስሜቱን በከፍተኛ ደረጃ ቀስቅሶታል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ዛሬ ፣ በሚያስደንቅ ሁኔታ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ጭምር ሳያስደንቅ አልቀረም፣ በኢኮኖሚው ዘርፍ፣ በፖለቲካው ዘርፍ፣ በማህበራዊውና በሰላሙ ዘርፍ የሚካሄደው ሰፊና ሕብረተሰቡን በሙ ሉ አሳታፊ የሆነ የለውጥ እንቅስቃሴ ሲደረግ ይታያል። ይህ እንቅስቃሴ እየዳበርእየዳበረ እንዲሄድና አስተማማኝ ዘለቄታን የጨበጠ፣ ፈር የማይለቅ ሆኖ እንዲገኝ፣ የኢትዮጵያ ሰላመና እርቅ ምክር ቤት የሚከተሉትን ሃሳቦች በትህትናና በአክብሮት ያቀርባል፣

ሕሳቤ አንድአስትዳደርን በሚመለከት

) በኢኮኖመው፣ በፖለቲካው፣ በማአሕበራዊውና በሰላሙ ዘርፎች በሚካሄደው፣ ጥርጊያ ጎዳናውን ተከትሎ በመጓዝ ላይ ያለን ሁለገብና ሰፊ እንቅስቃሴ፣ በየቀኑ እየተከታተለ የሚኮተኩትና ሲያስፈልግም ውሃ የሚያጠጣ አስተዳደርዎ ውስጥ እንደሚያስፈልግዎት በግልጽ እየታየ ነው። የልማትና የአንድነት እንቅስቃሴዎቹ የኔም ጭም ር ናቸው ብሎ በባለቤትነቱ የሚያምን ረዳት ያስፈልግዎታል።በእርስዎ ዓይን የሚያይ፣ በእርስዎ ጆሮ የሚያዳምጥ፣ የእርስዎን ስሜት የሚጋሩና የርስዎን ራዕይ ሥራ ላይ የሚያውሉ በየእርከኑ ኃላፊዎችን ባስቸኳይ መመደቡ በጣም ይጠቅማል፣ሽክምዎንም ያቃልልዎታል የሚል ሃሳብ በትህትናና በአክብሮት ለማካፈል እንፈልጋላን።

) በየመስኩ፣ ከመንግስት መሥሪያ ቤት ውጭ በማገልገ ላይ ያሉትን የምሁራን ስም ዝርዝር የያዘ፣ በጥናት ላይ የተመሰረተ፣ብቃት፣ልምድ፣ እውቀትና የምርምርና የጥናት ችሎታ ያላቸውን ግለሰቦች የሚይዝ ባንክ ማዘጋጀት። በሚያስፈልግበት ጊዜ ከተዘጋጀው የስም ዝርዝር ባንክ አውጥቶ ሥራና ሠራተኛውን በማገናኘት መተካት በትከሻዎ ላይ የተጫነውን ከባድ ሸክም ሊያቃልልዎ ይችላል።

) በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካውና በሰላሙ ፣ በየዝቅተኛ እርከኖች ሊሰየሙ የሚችሉ ባለሙያዎችን ማሰልጠኛ ማእከል ማዘጋጀት። እነኝህ በጥራትና በጥልቀት ከሰለጠኑ በሗላ እስከ ቀበሌ ድረስ በመድረስ ሕብረተሰቡን ለአንድነት፣ ለኢኮኖሚ ው ግንባታ፣ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ወሳኝ በሆኑ መስኮችና ጉዳዮች ላይ ሕብረተሰቡ እንዲዘጋጅበት፣ እንዲሳተፍትበትና ነቅቶ እንዲጠብቅ ያሰለጥኑታል፣ ያግባቡታልም።ይህንን እየተከታተለ የሚቆጣጠር ቢሮ መክፈት ደግሞ ሥራውን የበለጠ ያጠናክረዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሥራ ሂደትዎ እንደሚታየው ከተለመደው የሥራ ባህል ውጭ አዳዲስ የሥራ ባህሎችን በመፍጠር ስለሆነ ነው ይህን ያልተለመደ አይነት የሥራ ዘዴ ለአስተዳደሩ ይጠቅማል በሚል ነው ያቀረብነው።

ሕሳቤ ሁለትሁሉን አቀፍ ድርድር ማካሔድ የጊዜው ወሳኝ ጉዳይ ነው

ይህ ገዢውን ፓርቲ ያካተተ ሂደት፣ ግልጽና ስርነቀል ፖለቲካዊ ድርድር ላይ የሚ መሰረት፣ ምርጫን ብቻ ያለመ ሂደት ስለሚሆን ዘላቂና ቋሚ መፍትሔ ይሰጣል የሚል ሙሉ አምነት አለን። ይህ የመፍትሔ ሃሳብ በሥራ በሚተረጎምበት ጊዜ በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በማህበራዊውና በሰላሙ ዘርፎች እንቅስቃሴዎች በሚካሄዱበት ጊዜ የሚከሰቱ ችግሮች ሁሉ ለዘለቄታው ኃላፊነቱን ወስዶ በሥራ የሚተረጉም ባለቤት ተሰየመላቸው ማለት ነው ።ይህ ዘላቂ መፍትሄም የሚረጋገጠው ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫውን አካሂዶ የሥልጣኑ ባለቤት መሆኑ በሚረጋገጥበት ጊዜ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤትነት ተረጋገጠ ማለት በድርድሩ ሂደት ውስጥ ተሳትፈው የዘለቁትና በምርጫው ተወዳድረው በኢትዮጵያ ሕዝብ የተመረጡት ፓርቲዎች ማለትም የመፍትሔ ሰጪ ባለቤቶች ተሰየሙ ማለት ነው። በዚህ አኳሗን የፖለቲካው ችግር መፈታት በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትን፣ ማህበረዊና ባሕላዊ ግንባታን እያፈጠነ እንደሚያስኬድ ምንም ጥርጥር የለንም። እነኚህ ለምርጫ የሚቀርቡ የፖለቲካ ሀይሎች፣

) ሕብረተሰቡ ውስጥ በጥልቀትና በስፋት ገብተው ቅስቀሳ ለማካሔድ በቂ ጊዜ እንዲኖራቸው

) መንግሥትም ዝግጅቱን በተሟላ ሁኔታ ለማቀነባበር እንዲችል፣ የምርጫውን ጊዜ ማራዘሙ ወሳኝ ጉዳይ ስለሆነ በጥብቅ እንዲታሰብበት በትህትና ሀሳብ እናቀርባለን።

አክብሮት ከተሞላበት ሰላምታ ጋር፣

ማንከልክሎት ኃይለሥላሴ (/)

የኢትዮጵያ ሰላምና እርቅ ምክር ቤት

ሊቀመንበር

ጥቅምት 4 ቀን 2011 ዓም

October 14, 2018