======================
ወንጀለኛው የህወሓት አመራር ከወንጀሎቹ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሰራዊት የራሱ መሪወች ተረሽነው ያለመሪ በቀረበት በዚያ አጋጣሚ ከሱዳን የመካናይዝድ ጦር ጋር እና ከሱዳን መንግስት በመተባበር በጦር ሜዳ የማረካቸው የኢሕአፓ መሪወች ወደመቀሌ ወስደው ካሰሯቸው በኋላ እስካሁን መዳረሻቸውን እንዳጠፏቸው እና ይሙቱ ይኑሩን ያላሳወቁ በመሆኑ- ስለነ ጸጋየ ገ/መድህንን የት እንዳደረሱ ይጠየቁ።
አበበ አይነኩሉ፣ አበራሽ በርታ፣ ተስፋየ ታደሰ፣ አባይነህ ሽፈራው እና ሌሎችንም ያደረሱበት አይታወቅም። እነዚህንም እንዲፈቱ ይጠየቁ። ለነዚህ ወንጀለኞች፣ ሀገር ዘራፊወች እና ጥፍር ነቃይ፣ የጠበቃ እና ሌላም መብት ሲከበር ንጹሀን አሁንም በእነርሱ የጉድጓድ እስርቤቶች በስቃይ ይኖራሉ።

ፈሪወች እና ጨካኝ በላያሰቦቹ መሪወች

እንደሚመስለኝ ህወሓቶች ጥንካሬአቸው ሀገር መካድ- ዜጎችን ማዋረድ፣ ማሰር፣ መግደል ዳብዛ ማጥፋት፣ ጥፍር መንቀል የባስ ተብሎ የኢትዮጵያዊ ህሊና የማይቀበለው የማይገባ እና በየትም ዘመን እና ጨቋኝ መንግስት ያልተሞከረ ግብረ ሰዶማዊነት? እጅግ የሚያሳፍር የታሪክ ቆሻሾች-ደግሞ እጃቸው ሲያዝ በሰሜን ወሎ፣ በባህርዳር፣ በጎንደር፣ በአንቦ፣ ሀረር፣ የፈጸሙትን ያህል የሚያንገራግሩ ሳይሆን እንደዓንበሳ የሚያገሱ ሳይሆን እንደፍየል ግልገል የሚጎተቱ ትርትር ፈሪወች ናቸው ነበሩ ለሰሩት ሁሉ የፈሪ ስራ እና ጭካኔ ሊጠየቁ ይገብል