ወያኔ በሚሠራው የአሳሪ ታሳሪ ድራማ (ትውንተ ሁነት) ከውሸት ወይም ከማስመሰል ተጠያቂነት ከታች አቶ ደብረጽዮን ባሉት መልኩ ለማምለጥ አስቧል፡፡ ይመስለኛል ወያኔ በኋላ ሕዝብን ለማሳመን ለማታለል ብየ በገዛእጀ ተለቃቅሜ ወኅኒ ብገባ ያልታሰበ ነገር ተፈጥሮ ጉድ ብሆንስ?” ብሎ የፈራ ይመስላል፡፡ እራሱ የደረሰውን፣ የሚመራውንና የሚተውን የሚያስተውነውን ድራማ እንኳ ማመን አልቻለም፡፡

ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ይሄንን ብሏል “የኢትዮጵያ መንግሥት በሙስና እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ስም የጀመረው እንቅስቃሴ አቅጣጫውን ስቶ የትግራይ ሕዝብን ለማንበርከክ የሚደረግ ጥረት ስለሆነ አንቀበለውም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ጣልቃ ገብነት አለው ብለን እናምናለን!” በማለት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

እነ ደብረጽዮን ሆይ! ምን እያላቹህ እንደሆነ ይገባቹሃል ወይ??? “የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ዝርፊያ ስርቆት የፈጸመ ሌባና ግፍ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸመ ወንጀለኛ ነው!” እያላቹህ እኮነው ያላቹህት ይገባቹሃል ግን ለመሆኑ???

እንደምትሉት የታገላቹህትና የምትታገሉተት ለትግራይ ሕዝብ ከሆነ እራሳቹህን ከተጠያቂነት ነጻ ለማውጣት ስትሉ የትግሬን ሕዝብ በዚህ ደረጃ ማዋረድና መጠቀሚያ ማድረግ እንዴት ሊከብዳቹህና ሊቀፋቹህ አልቻለም???

ለትግሬ ሕዝብ ክብር፣ ስምና ታሪክ ጨርሶ አታስቡም ወይ??? ከመጀመሪያው ጀምሮ ተግባራቹህ ሥራቹህ እያሳየ ያለው እኮ ለትግሬ ሕዝብ መታገላቹህን ሳይሆን የትግሬን ሕዝብ የእናንተ መጠቀሚያ መገልገያ መሣሪያ ዕቃ ማድረጋቹህን እኮነው!!!

ካልሆነ በስተቀር ወንጀለኞችን ተጠያቂ ማድረግ፣ ለሕግ አሳልፎ መስጠት የትግሬን ሕዝብ ማጥቃት ወይም ለማንበርከክ ማሰብ የሚሆነው እንዴት ሆኖ ነው???

ወንጀለኞችን ለሕግ አሳልፎ በመስጠት በቦታቸው ወንጀል ያልፈጸሙ ሰዎችን መተካት እየቻላቹህ እንዴት ሆኖ ነው ወንጀለኞችን በወንጀል ስም በቁጥጥር ስር ለማዋል ማሰብ የትግራይን ሕዝብ ለማንበርከክ ማሴር የሚሆነው??? ነው ወይስ የትግራይ ሕዝብ ከወንጀል ነጻ የሆነ ሰው የለውም!” ነው እያላቹህን ያላቹህት???

ወንጀለኛ እንዴት ሕዝብን ይወክላል??? “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ!” ሆኖ ነው እንጅ ሕዝብን በወንጀለኞች መወከል ያንን ሕዝብ ማዋረድና የሕግ የበላይነትን አለመቀበል እንደሆነ እነ ደብረጽዮን እንዴት ይጠፋቸዋል??? በዓለማችን ምንም ዓይነት ምክንያት ቢሆን ከሕግ በላይ ለመሆን ወይም የሕግ የበላይነት ለመሻር እንደማያስችል ደንቆሮዎቹ እነደብረጽዮን ሊረዱት ይገባል፡፡

አንድ የሕዝብ ተወካይ የወንጀል ተግባር በፈጸመ ቅጽበት ወዲያውኑ የሕዝብ ተወካይነቱ ቀርቷል፡፡ ስለሆነም ክሱና የሚከተለው ቅጣቱ የሚመለከተው እሱን እራሱን ብቻ እንጅ የወከለውን ሕዝብ አይደለም፡፡ ወንጀል እየፈጸመም ሕዝብን እወክላለሁ!” ማለት እወክለዋለሁ የሚለውን ሕዝብ ወንጀለኛ ማድረግ መዝለፍ ማዋረድ ነው፡፡ በዚህ ወንጀለኛ የተወከለው ሕዝብም ፈጽሞ ይሄንን ስድብ፣ ዘለፋና ማዋረድ በትዕግሥት ማሳለፍ የለበትም፡፡

የትግሬ ሕዝብ እነኝህን ወንጀለኞች ወንጀለኛ ቢሆኑም ወንጀል ከፈጸሙም በኋላ ይወክሉኛል፣ የኔ ተወላጆች ስለሆኑ ምንም ይፈጽሙ ምን መጠየቅ የለባቸውም፣ የሕግ የበላይነት ብሎ ነገር አይገባኝም አልቀበልም!” ካላለ በስተቀር በወንጀለኞች ዓይን መታየት አይኖርበትም፡፡ አለማለቱን ግን ወንጀለኞችን አሳልፎ በመስጠት ወይም ባዋረዱት ወንጀለኞች ላይ እርምጃ በመውሰድ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል!!!

የትግሬ ሕዝብ ይሄንን ማድረግ ካልፈለገ እነሱ ማለት እኔ ነኝ እኔ ማለት እነሱ ናቸው!” ብሎ ተማምሏል ማለት ነው፡፡ በዚህም ተግባሩ የትግሬ ሕዝብ እራሱን ማንነቱን ህልውናውን ከሚያልፉ ከሚጠፉ ወንጀለኛ ግፈኛ የአንድ ዘመን የአገዛዝ ጭፍሮች ጋር በማቆራኘት በማስተሳሰርና እነሱን የሚበላ መቅሰፍት እኔንም ይብላኝ!” በማለት በዓለማችን የመጀመሪያው ደንቆሮ ሕዝብ መሆኑን ያስመሰክራል ያረጋግጣል ማለት ነው፡፡

እንግዲህ ምርጫው የትግሬ ሕዝብ ነው፡፡ በእርግጥ የትግሬ ሕዝብ ይሄንን ከላይ የተጠቀሰውን አስከፊ ምርጫ እንደመረጠ የሚጠቁሙ ሕዝባዊ ሰልፎችን ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ያደረገና ያረጋገጠ ቢሆንም ይሄንን የደነቆረ አርቆ ማሰብና ማመዛዘን ጨርሶ የተለየውን ውሳኔ መልሶ እንዲያጤነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም ዕድሉን ይሰጣልና የትግሬ ሕዝብ ሆይ! ከዚህ የተሳሳተና ከደነቆረ የጥፋት አስተሳሰብህ ወጥተህ እንደ ሕዝብ መቀመጥ ባለብህ ቦታ ላይ በመቀመጥ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመሰለፍ መውሰድ ያለብህን እርምጃ በወያኔ ላይ ትወስድ ዘንድ ለመጨረሻ ጊዜ ትጠየቃለህ???

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com