Source: https://mereja.com/amharic/v2/68199
በ50 ቢሊዮን ብር የሚገነባው የለገሃር ሁሉን አቀፍ የተቀናጀ የመንደር ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

በ50 ቢሊዮን ብር የሚገነባው በአዲስ አበባ ለገሃር የተቀናጀ የመኖሪያ አገልግሎት መስጫና የመዝናኛ ስፍራ ልማት ስራውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድ በተገኙበት ይፋ ሆኗል፡፡
በ36 ሄክታር መሬት ላይ የሚያረፈዉ የለገሀር የተቀናጀ የልማት ኘሮጀክት በዉስጡ ከ4 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ግዙፍ የንግድ ማዕከላት ይኖሩታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ፕሮጀክቱ መጋቢና ዋና መንገዶች እና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ይኖሩታል።
ኘሮጀክቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና በዱባዩ ኤግል ሂልስ ትብብር የሚሰራ ሲሆን ነዋሪዎች አሁን ባሉበት ቦታ መኖርያ ቤት ተገንብቶላቸዉ በዘላቂነት በሚያዉቁት ቀዬ እንዲኖሩም ይደረጋል።
ኘሮጀክቱ ለአከባቢዉ ነዋሪዎችም ሆነ ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የበለጠ የማነቃቃት ሰፊ ሚና እንዳለው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ በሚገነባበት ወቅትም በአካባቢው የሚኖሩ 1 ሺህ 600 ዜጎች አካባቢያቸውን ሳይለቁ በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የተሻለ መኖሪያ ቤት እንደሚገነባላቸውም ገልጸዋል።