አብዛኛዎቹ ከኦሮሚያ ክልል ሲሆኑ፤ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 1.1 ደርሷል፤ በጎርፍ እና ድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉትን ጨምሮ።
Norwegian Refugee Council
አጭር የምስል መግለጫ አብዛኛዎቹ ከኦሮሚያ ክልል ሲሆኑ፤ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 1.1 ደርሷል፤ በጎርፍ እና ድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉትን ጨምሮ።

ከሐምሌ ወር ጀምሮ ባለው ጊዜ ብቻ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ግጭት በመሸሽ ከሶማሌ ክልል መፈናቀላቸውን የኖርዌይ ተራድዒ ድርጅት ይፋ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ግጭትን በመሸሽ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ የሚያትተው መግለጫው በሁለት ዓመታት ብቻ 700 ሺህ ሰዎች ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለዋል።

አብዛኛዎቹ የተፈናቀሉት ከኦሮሚያ ክልል ሲሆን፤ በጎርፍ እና ድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉትን ጨምሮ 1.1 ሚሊዮን ደርሷል፤።

የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪቃ ተጠሪ ኤቬሊን አየሮ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ቁጥራቸው እጅግ የላቀ ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል ይላሉ።

ጥቂት እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ብቻ በሚገኙበት በዚህ አካባቢ አሁንም የተፈናቃዮች ቁጥር እንዳልቀነሰና የእርዳታ እጥረት እያጋጠመ እንደሆነ ኃላፊው ያክላሉ።

«እርዳታ በጣም ያሻል፤ ከመርፈዱ በፊትተፈናቃዮቹ ሕይወትን የሚታደግ እርዳታ ይሻሉ።» ብለዋል

በሞያሌ በተከሰተ ግጭት የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

ከምስራቅ ኦሮሚያ የተፈናቀሉት አርሶ አደር አብድራህማን ሞአሊም «ልብሳችንን ብቻ ይዘን ነው፤ ቀያችንን ጥለን የወጣነው» ይላሉ።

አብድራህማን ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ሶማሌ ክልል በሚገኘው ኮሎጂ በተሰኘ የመጠለያ ጣብያ የሚገኙ ሲሆን ጣቢያው ሌሎች 65 ሺህ ገደማ ሰዎች ተጠልለውበታል።

«ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር አለ፤ ሕፃናት እየሞቱ ነው። የኩፍኝ እና የቲቢ በሽታ እየተንሰራፋ ነው። 3 ወይም 4 ሰው በቀን ሊሞትብን ይችላል» ይላሉ አብድራህማን።

አዲሱ የሶማሌ ክልል አስተዳደር ለችግሩ መፍትሄ ለማበጀት የእርዳታ ድርጅቶች ወደ ክልሉ ገብተው የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ጥሪ እያቀረበ እንደሆነ የኖርዌይ ተራድዖ ድርጅት በመግለጫው አስታውቋል።

“በኢትዮጵያ 93 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መጸዳጃ ቤት የለውም”

ከተፈናቃዮቹ መሃል 5 ሺህ የሚሆኑትን መልሶ ለማቋቋም እቅድ እንዳደለ ድርጅቱ ይፋ አድርጓል።

ውሃ፣ መጠለያ እና ሌሎች እርዳታዎች ተፈናቃዮቹ በአፋጣኝ የሚሿቸው እንደሆኑ ነው ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ያሳውቀው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለጉዳዩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ብናውቅም አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ ጉዳዩች እንዳሉ ግን አይካድም ይላል የድርጅቱ ማሳሰቢያ።

«ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ብዙ ትኩረት ዘንድ ያገኘ አይደለም፤ መንግሥት ለችግሩ ፖለቲካዊና ሰብዓዊ መፍትሄ ለመስጠት እየጣረ እንዳለው እናውቃለን። እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ግን አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ረደግ ሊሯሯጡ ይገባል» ይላሉ ኃላፊዋ።

ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል?

ምንጭ            –        ቢቢሲ/ አማርኛ