የኤርትሪያው ፕ/ት ኢሣያስ አፈወርቂ በቅርቡ የጎንደር ቆይታቸው ላይ ‘ሰላምን ለማፅናት ከተፈለገ ወያኔ ሙሉ ለሙሉ መወገድ አለበት’ ብለው ነበር:: አልተሣሳቱም:: በሁለት ምክንያቶች እስማማለሁ::
1. ከማንኛውም የስርቆት ወይም የዝርፊያና የግድያ ወንጀል ጀርባ ህወሃት-ወያኔ አለ:: ማርዮ ፑዞ ‘የክርስትና አባት (Godfather) በተሰኘ መፅሃፉ “ከማንኛውም ሐብት ጀርባ ወንጀል አለ” እንደሚለው::
2. ማንኛውም የስርቆት ወይም የዝርፊያና የግድያ ወንጀል በህወሃት የንግድ ድርጅቶች ወይም አባላት ማንም ይሁን ማን ይፈፅመው የህወሃት አዎንታና ድጋፍ ውጪ አይተገበርም:: እነ ክንፈ ዳኘው የዝርፊያው ወንጀል መልዕክተኛ ሲሆኑ የመልዕክቱ ባለቤትና መልዕክተኞቹን የሚያሰማራው ህወሃት ነው:: መጠየቅ ያለባቸው መልአክተኞቹ ብቻ ሳይሆኑ ‘የክርስትና አባታቸው’ ህወሃትም ጭምር ነው::
ነብሰ ገዳይ የሲሲሊያን ማፊያ ቅጂዎቹ የሆኑት ወያኔዎች ቁንጮ የሆኑት ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ትላንት የዘራፊዎቹን እስር ሲያወድሱ ቆይተው ዛሬ በህወሃት ዘራፊዎች ላይ የሚደረገውን እስር እንደሚቃወሙ በመግለፅ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው አይገርመኝም:: እስስትም በዚህ ፍጥነት ቀለሟን አትቀይርም:: እናቱ ላይ ሊወጣ እንደሚሞክር ባለጌ ጥጃ ኢትዮጵያ ላይ የተንጠላጠሉ ቀን ተንሸራተው እንደሚወድቁ ማወቅ ነበረባቸው:: የተዘረጋላቸውን ‘የፍቅርና የሠላም እጅ’ ለመንከስና እንደውጫሌ ውል ለማጭበርበር ዳርዳር እያሉም ነው:: ምክንያቱም ማታለል (deceit)፣ ማጭበርበር (deception) እና የለየለት ቆሻሻ ውሸት (dirty liar) እንዲሁም መንታ ምላስና ሃሣብ (doublethink) መለያቸውና ከጣሊያን የወረሱት ቅርስ ነው:: ከሃዲ ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው:: ምክንያቱም ይህ የወዳጆቻችሁ ጣሊያኖች ምሣሌያዊ አነጋገር (Italian proverb) ወያኔን እንዴት ማስተናገድ እንዳለብን ይመክራል:: “ሠው አንዴ ካታለለኝ የእርሱ ጥፋት ነው:: ሁለቴ ካታለለኝ ግን የኔ ስህተት ነው” :: (“When a man deceives or hurt me once, it is his fault; when twice, it is mine”).
ደብረፅዮን የተማመኑት ለክፉ ቀን ብለው በሞጫጨሩት ወያኔ ሠራሹ ‘ሕገ-አራዊቱ’ አንቀፅ 39ን ነው:: በሬ ሆይ ሣሩን አይተህ ገደሉን ሣታይ’ እንደሚባለው እኝሁ “የክብር ዶክተር” የዘነጉት ን.አ. 4 ክፍል በ ‘መ’ ላይ ‘የፌደራል መንግስት መገንጠል ለጠየቀው አካል ስልጣን አስረካቢ’ መሆኑን እና በ ‘ሠ’ ላይ ‘በሕግ የሚወሰን የንብረት ክፍፍል’ መኖሩን ነው:: ወያኔውች “ለመገንጠል” የዘረፉትን ሐገራዊ ሃብት እንደሚመልሱ የሚደነግገውን የራሣቸውን ‘ሕገ-አራዊት’ እንኳን በውል አያውቁትም:: የዘረፉትም ንብረትና ገንዘብ ብቻ ሣይሆን የወልቃይት: የራያ እንዲሁም የፀለምት ጠፍ መሬትና ግዛት በቅድሚያ መመለስ ግድታቸው መሆኑን እረስተዋል:: የጨዋታው ሕግ ‘የመርዙን ለመርዙ መሆኑን ማስታወስ ተስኗቸዋል:: ለነገሩ ውሸታምና ዘራፊ መዋሸቱንና መዝረፉን እንጂ መዘዙን አይረዳም:: ጆን ዮርምዝ “ድምፅህ እውነታንና ሐቅን መፃረር ሲጀምር መፈናፈኛ ለማግኘት የምታደርገው እውነታንና ሐቅን ማጣጣል ነው” ይላል:: (“When your voice contradicts reality & truth the only way to creat space for it is to discredit reality & truth”. John Yarmuth)
የሽኝት ሙሾ ለወያኔዎች!
‘ረሐቡንም ችለን ብንታገሣችሁ፣
ጥጋቡንም መቻል ጭራሽ አቃታችሁ፣
ለዘግናኙ ወንጀል ለፈፀማችሁት ዝም ብንላችሁ፣
እንዳንገነጠል ሆኖ ጨዋታችሁ::
የልጅ ማስፈራሪያ አትስጡን ባካችሁ፣
እንደ ሐምሌ ክረምት ፈቀድን ልንሸኛችሁ፣
የጣሊያንን ጫማ ያን የምታውቁትን አቀረብንላችሁ::
ስለአቡነ አረጋዊ ፍጠኑ እባካችሁ፣
የደደቢት መንገድ ጨርቅም ያርግላችሁ፣
የክብር ዶክተሮች” ደህና ሁኑ አልናችሁ፣
ዳግም እንዳታዩን እኛም አናያችሁ::’
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በህወሃት በትር አይደማም!
ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ክብር ነው!