Image may contain: 1 person, beard, sunglasses and closeup

Befekadu MorodaFollow

የዛሬ አሥር ዓመት ሰኔ ወር በኢሕአዴግ ጥይት ያለቁትን ወጣቶች በእጄ የሚገኘዉን የጥቂቶቹን ፎቶ ግራፍ እያየሁ አስታወስኩዋቸዉ፡፡

የዛሬ 17 ዓመት በወያኔ ነፍስ ገዳዮች እቤቱ በራፍ ላይ በስለት ጨፍጭፈዉ የገደሉትን ወንድሜን ተስፋዬ ታደሰን ግን በእምባ አሰብኩት፡፡

ተስፋዬ የሕግ ባለሙያ ፣ጋዜጠኛ፣የሰብአዊ መብት ታጋይ፣…ነበር፡፡በተደጋጋሚ አፍነዉ ለወራት እየሰወሩ ደግሞም ሲፈቱት፣ከሥራዉ (በኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የሕግ ባለሙያ ነበር)ሲያባርሩት፣ሥርዓቱ በሚያዘዉ ፍርድ ቤት ላይ እንኳን ቢሆን መንግሥትን እየከሰሰና እየረታም ወደሥራዉ እንዲመልሱት ያስገድድ የነበረ ጎበዝ ነዉ፡፡‹በመስተዋወት መፅሔት እና ሉባር ጋዜጣ በአዘጋጅነትና አሳታሚነት እንዲሁም በብስልና ስል ሂስ አቅራቢነት ግፈኞችን ሲሟገት የነበረ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡

አፈናዉ፣እስራቱና ማስፈራራቱ ሊመልሰዉ ስላልቻለ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር ጁን 7 ቀን 1998 ማታ ገርጂ በሚገኘዉ ቤቱ በራፍ ላይ በገጀራ ደብድበዉ ገደሉት፡፡ ይህን ሰማዕት የሕዝብ ልጅ አሥራ ሰባተኛ ሙት ዓመቱን በእምባ እያስታወስኩ፣ተስፋዬ የሞተለት እዉነት ይዋል ይደር እንጂ አሸናፊ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ወንድሜ፤ ሌላ ወሬ የማወራበት አቅም የለኝም፤ብቻ እግዜር ነፍስህን ይማር!!!