
ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ-ሚካኤል በቅርቡ በሰጡት መግለጫ «ድብቅ እስር ቤት» የሚባል እንደለሌ አስታዉቀዉ ነበር።አረና ለሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ የተባለዉ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ግን ትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌ ዉስጥ ቢያንስ አንድ የድብቅ እስር ቤት መኖሩን እንደሚያዉቁ ተናግረዋል።
ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ መስተዳድር በተለያዩ አካባቢዎች የድብቅ ወይም ሕገ-ወጥ እስር ቤቶች አሉ መባሉ የተለያዩ ወገኖችን እያወዛገበ ነዉ።ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ-ሚካኤል በቅርቡ በሰጡት መግለጫ «ድብቅ እስር ቤት» የሚባል እንደለሌ አስታዉቀዉ ነበር።አረና ለሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ የተባለዉ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ግን ትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌ ዉስጥ ቢያንስ አንድ የድብቅ እስር ቤት መኖሩን እንደሚያዉቁ ተናግረዋል።በትግራይ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተጠሪ በበኩላቸዉ የድብቅ እስር ቤት ሥለመኖሩ የደረሰን ጥቆማ የለም ባይ ናቸዉ።
ለዝርዝሩ ይህን ይጫኑ , https://m.dw.com/am