ከላይ የተመለከተዉ የጠቅላይ ሚኒስትር የዶ/ር አብይ አህመድ አባባል በወያኔ  ፋሽስቶች የተሰራዉን ወንጀልና ሌብነት ደፍረዉ እንዳለ ለማቅረብ መቸገራቸዉን የሚያሳይ የጭንቀት  አባባል ነበር ። ጥፍር የነቀሉት፤ የወንድና የሴት ብልት ላይ በአስነዋሪ ሁኔታ የቀለዱት፤ ዜጋን አካለ ጎደሎ ያደረጉት፤የገደሉት፤ ያሳደዱት፤ልጅን ገድለዉ እናትን እሬሳዉ ላይ ያስቀመጡት፤ወጣት ዜጋን ገድለዉ አንበሳ እንደገደሉ ሁሉ አጠገቡ በፎርም ተመቻችተዉ ከአስከሬኑ ጋር ሳይቀፋቸዉ  ፎቶ ስለሚነሱት ፋሺስቶች ሳይሸማቀቁ ገለጻ መስጠት በእነሱ ሞራል ልክ መዉረድን ይጠይቃል።

የሰዎቹ ዘረፋ መጀመሪያ ማስረጃ  የሚሰባሰብበት ሳይሆን እነሱ ተሰብስበዉ ቃልቲ ወርደዉ ማስረጃዉ ሳይደለዝ፤ ሳይፋቅ ሳይጠፋ፤ የዘረፉት ንብረት ባለቤትነቱ  ሳይተላለፍ፤ሀገር ቤት ያለዉ  ገንዘብ በትስስራቸዉ ከሀገር ሳይለቅ፤ሳይታጠብ (money laundry)  ምርመራዉ እንዲደረግ ያሳሰበን ዜጎች አመላክተን ነበር። በመሰረቱ አንድ ትግሬ ብድግ ብሎ ባለ ምናምን ሚሊዮን ብር ቤት ህንጻ ሰራ ሲባል የንግድ ድርጅት ሲያቋቁም ማስረጃ ስላልተገኘ  አትጠየቅም ማለት ትንሽ ፈገግ ያሰኛል። ስድስት ወር እንደ ህወአት በሌብነት  ለተካነ ድርጅት መረጃን ለማጥፋት  ከሚያስፈልገዉ ጊዜ በላይ በመሆኑ ሀገር ተሻግሮ የወጣ የሀገርን ሀብት ማስመለሱ የማይታሰብ ይሆናል።  ለዚህም ነበር ወንጀለኞቹ ቢሊየነሮች ደፍረዉ ገንዘብ የለንም መንግሰት ጠበቃ ያቁምልን ብለዉ ያሾፉት?

ወገኖች በስልጣን ላይ የሚገኝ ዜጋ በከፍተኛ የሞራል ልእልና ላይ መገኘት ያስፈልገዋል። እዚህ ላይ አንድ ነገር መጥቀስ ያስፈልጋል። ታላቋ ብሪታንያ በነበርኩበት ጊዜ  ጀፈሪ ሮቢንሰን  የተባሉ ባለሀብት በጠ/ሚኒስቴር ቶኒ ብሌር በጅሮንድ ሁነዉ ተሹመዉ ነበር። እኝህ ባለሀብት ፒተር ማንድልሰን ለተባለ የካቢኔ አባል  የመንግስትን ሳይሆን የራሳቸዉን ገንዘብ አበድረዉት ፒተር ማንድልሰን መኖሪያ ቤት ይገዛል። ጀፈሪ ሮቢንሰን የራሳቸዉን ብር ማበደራቸዉን መናገሩ  አስፈላገነቱ ስላልታየቸዉ ስራቸዉን በቅንነት እየሰሩ እያለ ጋዜጠኞች ጉዳዩን በማጋለጣቸዉ አበዳሪና ተበዳሪ ስምምነቱን ይፋ አላደረጉም በሚል ክስ  ሁለቱም ከስራቸዉ ተባርረዋል። የሚገርመዉ ጀፈሪ ሮቢንሰን ብድሩን የሰጡት በ1996 ሲሆን እሳቸው ወደ ካቢኔት ለሹመት የተጠሩት በ1997 ነበር ።አለም በዚህ አይነት የሞራል ልእልና ላይ ሲገኝ የእኛ ኪስ አዉላቂ የትግራይ ጭልፊቶች (ዳንኤል ብርሀኔ፤አሉላ ሰለሞን፤ሰናይት መብርሀቱን …..) የመሳሰሉ አቅጣጫ ለማሳት ሲባክኑ ማየት ድካማቸዉ ከምንም በላይ ያደፈ ሞራላቸዉን አጉልቶ ያሳያል።

በቀደመዉ ጊዜ ባገራችን ኢትዮጵያም ከዚህ በተሻለ የሞራል ማማ  ላይ የነበሩ መሪዎች ነበሩን። ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ በአሜሪካን  ላይበረሪ ኮንገረስ (https://youtube.com/watch?v=VqWQsgJ_CIs)ዲሰኩሩ እንደገለጸዉ ለመጀመሪያ ጊዜ የስእል  ኤግዝቪሺን አዲስ አበባ ሲያሳይ ጎብኝዎቹ አጼ ሐይለስላሴንና ሚኒስተሮቻቸዉን ጨምሮ ነበር። ከጉብኝቱ በሗላ ንጉሱና ሚኒስተሮቻቸዉ ስእል መርጠዉ ይወስዳሉ። በተከታዩ ቀን አፈወርቅ ተክሌ ለትምህርት ወደ እንግሊዝ መምጣት ስለነበረበት አጼ ሐይለስላሴን ለመሰናበት ወደቤተ መንግስት ሲሄድ  ሚኒስተሮቹ ለወሰዱት ሰእል ከፍለዉት እንደሆነ ሲጠይቁት ያለመክፈላቸዉን ሲነግራቸዉ ባስቸኳይ ስልክ ደዉለዉ ወይ ገንዘቡን ወይ ስእሉን ሆቴሉ ድርስ ወስዳችሁ ስጡት ብለዉ ጥብቅ ትእዛዝ ይሰጣሉ። ሚኒስተሮቻችንም ስእሉን ለአፈወርቅ ተክሌ ሆቴሉ ድረስ ወስደዉ ይመልሳሉ። አንባቢ ከዚህ መረዳት የሚችለዉ ሚኒስተሮቻችን  ስእሉን ቢወዱትም በደሞዛቸዉ ብቻ ይተዳደሩ ስለነበርና  ትርፍ ገንዘብ የሌላቸዉ የህዝብ  አገልጋዮች በመሆናቸዉ የሚወዱትን ሰእል ገዝተዉ ለማስቀረት ባለመቻላቸዉ በጸጸት በሀፍረት ለመመለስ ተገደዋል። በዝባዥና ጨቋኝ ተብለዉ በኢትዮጵያ ጠላቶች የተገደሉት መሪዎቻችን እነዚህ ነበሩ።

አጼ ሐይለስላሴም በስደት በነበሩበት ጊዜ በችግር ምክንያት የግል መጠቀሚያ ንብረታቸዉን ይሸጡ እንደነበር የፖላንዱ ጸሀፊ (Ryszard Karuscinski)  The Emperor በሚል መጽሀፉ ገልጾታል።  በፕሮፌሰር መስፍንና በረከት ሐ/ስላሴ ምክር ለሞት የተዳረጉት በሻቢያና ህወአት ቅስቀሳና ነገር ባልገባቸዉ የወቅቱ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እብደት ተደማምሮበት  እንደ አዉሬ የተሳሉት ንጉስና ሚኒስተሮች ይህን ይመስሉ ነበር።

ምን ይሄ ብቻ የህወሃት ፋሺስቶችን በቅጡ ሳናዉቃቸዉ ፋሺስት ያልነዉ ደርግም  አባላቶች (ደርጎቹ)  የግል ቤት እንደሌላቸዉ ከመገለጹም በላይ ሌብነትና የራስን ጎሳ መጥቀም ቀርቶ የግል ዘመድንም ከስርአት ዉጭ በመርዳት ጭራሽ አይታሙም ነበር። ሌላዉ ቢቀር መንግስቱ ሐ/ማርያም አባቱ ያገኟትን ከሰፈር መጠጥ ቤት ተቃምሰዉ ሲኖሩ እንዳልደገፋቸዉ ስለሁኔታዉ የሚያዉቁ በተደጋጋሚ መስክረዋል ጸሀይ የሞቀም ሀቅ ነበር። ከኩዌት መንግስት በግሉ የተሰጠዉን 20 ሚሊዮን ዶላር ኢትዮጵያ በችግሯ ትጠቀምበት ብሎ በደመቀ ባንጃዉ እንደላከ ሰነዶች ያሳያሉ በተወሰነ ደረጃ ከህወሃት ፋሺስቶች መለየቱን እንጂ መንግስቱ ኃይለማርያምን ቅዱስ ነዉ አለማለቴን አንባቢ ያጥንልኝ። የደርጉ ሁለተኛዉ/ ሶስተኛ ሰዉ የነበረዉ ብርሀኑ ባዬህ የናት ያባቱ ልጂ  ጭማድ በተባለዉ ድርጂት ሰፕላይ (supply) ክፍል ዉስጥ እቃ ስትሸከም ትዉል እንደ ነበር አብረዋት ይሰሩ የነበሩ በአግርሞት ይናገራሉ።

ይህን ሁሉ የደረደርኩት ወያኔዎችን አንባቢ በንጽጽር እንዲመለከታቸዉ በማሰብ ነዉ። ያለፉት ስርአቶች ክፉም በጎም ጎን ሊኖራቸዉ ይችላል እንደ ህወሃቶች ግን በታሪካችን በክፋት ተወዳዳሪ የተገኘለት አገዛዝ  አልተፈጠረም ወደፊትም አይፈጠርም። የእህትን ባል ሁለት አይን አያቶቻቸዉ በጉጠት ማዉጣታቸዉ፤ ደካማን በሻሺ አንቀዉ መግደላቸዉ  ሲያሸማቅቀን  ይህን አሻሺለዉ ህዝብነ ይክሳሉ ስንል የልጅ ልጆቻቸዉ ክፋታቸዉን አሻሺለዉ ሐይ ቴክ (hi tech) አድረገዉት ብቅ ብለዉልናል።

ይህ ከሰሞኑ የሰማነዉ በጣም ቁንጮዉ ላይ የተቀመጡ ሌቦችን ነዉ። አምባሳደሮቻቸዉ ትልቁ ስራቸዉ ድለላ፤ሎቢስት ማማለልና የኢትዮጵያን ወጣቶች ወደ አረብ አገር ልኮ ኮሚሺን መቀበል ነበር። ሱሌይማን ደደፎ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንደ ህወአት አምባሳደሮች በየግብዣዉ ከመቀላወጥ ከዲፕሎማት ደረጃ ወርዶ ሀገርና ወገንን ከማዋረድ ተቆጥቦ  ትናንሿ የኢትዮጵያ ጉዳይ አሳስቦት ጂቡት ወደብ ላይ ሆን ተብሎ በትግሬ ዘራፊዎች ስለተተወዉ መርከብ ተከታትሎ በመርከቡ ጤንነትና ከወጭዉ አንጻር ሀገር ላይ የሚያደርሰዉን ኪሳራ ተገንዝቦና ተቆርቁሮ ደብደቤ  ለዉጭ ጉዳይ በመጻፉ በረከት ሰምኦንና ቴዎድሮስ አድሀኖም  ጥርስ እንደገባ ኤርምያስ ለገሰ ገልጾታል። ሱሌይማን ደደፎ እዚህ ላይ ሳይቆም ነዉረኞች መሆናቸዉን ተገንዝቦ እንቀስቃሴያቸዉን ስለተከታተለ አሸዋዉን ስኳር ብለዉ ሊሸጡ ሲዘጋጁ እጅ ከፍንጅ መያዙንም አብስሮናል። የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ለዚህ ታላቅ ዲፕሎማት ባለበት ቦታ ኢትዮጵያዊ ክብር ይድረሰዉ ይላል። እንዲህ ያሉ ዲፕሎማቶች  የታላቁ ዜጋ አክሊሉ ሐብተወልድ ካቢኔ ከፈረሰ በሁዋላ ማግኘት እንደ ሉሲ ርቆብናል። ይህ ዲፕሎማት (ሱሌይማን ደደፎ)  የነዚህን ባለጌዎች የሀገርና የባንዲራ ጥላቻቸዉን አስመልክቶ በቁጭት የሰጠዉ ቃለመጠይቅ ለሀገር፤ ለወገን፤ ለባንዲራ ክብር ያለዉ ዜጋ መሆኑን በግልጽ አሳይቷል። ሐይለ ማርያም ደሳለኝ/አባዱላ ገመዳ/ነጋሶ ጊዳዳ  ያንተ አይነት ሞራል ቢኖራቸዉ እንዲህ ስብእናቸዉን ሺጠዉ አገር ባላዋረዱ ነበር።

አየር መንገድን የመሰለ ትልቅ  ተቋም የቅጥር፤ ምልመላና ስልጠናዉን ነገር ለጊዜዉ ትተነዉ  ከምድር በታቻ የማሰቃያ ክፍል ከመኖሩም በላይ የቴክኖሎጂ ክፍሉ (IT ) ትልቁ ስራዉ ፓልቶክና ፌስ ቡክ ላይ አክራሪ ትግሬዎችን ወዝፎ ወገንን ከወገን ማባላት መሆኑን ሰሞኑን ከዉስጥ ምንጮች በተላለፈዉ መረጃ ከመመልታችንም ባሻገር  ሾልከዉ ለበረራ በደረሱ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚያደረሰዉን አሳዛኝና አሰቃቂ ስራ ባለፈዉ ተመልክተን ልባችን በሀዘን ተሰብሯል። የኢትዮጵያ አምላክም ፍርዱን ያሳያል እንላለን አንድን ፓይለት ምን ያህል ቢያማርሩት ነዉ ቆፍሬ ልብላ የሚል ዉሳኔ ላይ የደረሰዉ? ይህ ሰሞኑን የተጀመረዉ ሌባን አድኖ መያዝና የመንግስትን ስልጣን ባግባቡ ያለመጠቀም በአየር መንገዱም እስከ ታችኛዉ እርከን ይቀጥላል ብለን እንገምታለን ወንጀለኞቹ ከሀገር ካላመለጡ።

እንግዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦርነቱ አብሪ ጥይት ተተኩሷል ምናልባትም ዶ/ር አብይ ይህን ያህል ጊዜ የጠበቀዉ ሸምቀቆዉን ሲያጠብቅ ይመስላል። ዛሬ ነገሮች ለኢትዮጵያ ጠላቶች የተመቹ አይደሉም ወደ ሀገር የገቡት ተቃዋሚዎችም ፍጥነታቸዉ ከኢትዮጵያዊነት ጋር እኩል መሄድ ስላልቻለና ንግግራቸዉም ስለተሰለቸ  ሾለክ ሾለክ እያሉ መሆኑ ይነገራል። አረጋዉያኑ ኦነጋዉያኑና የህወአት መስራቾቹ ግን እድሜም አቅምም  ባለመኖሩ በዉጭም በሀገር ዉስጥም ሊያበረክቱት የሚችሉት ነገር ስለሌለ አማራጫቸዉ ወክለነዋል በሚሉት የጎሳ ድርጅት ተጠልለዉ ወጣቱን እያምታቱ መኖርን ነዉ።

ይህ ዛሬ ኢህአደግ የተባለዉ ድርጅትና መመሪያዉ በኦነግና በሀወአት የተቀረጸ ከመሆኑም ባሻገር ህወአት በሰራዉ በማንኛዉም ጸረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ፤ ዘረፋና ማሰቃየት፤መግደለን ጨምሮ  የኦነግ አሻራ እንዳለበት በድፍረት ሊነገር ይገባል። እነሱም በዶ/ር አብይ መንግስት ለፍርድ ይቀርባሉ የሚል እምነት አለን። ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል መንግስት ለኦነጋዉያን የሚያደረገዉ እሽሩሩ ኦነጋዉያኑን ሲያስደስት አብዛኛዉን ህዝብ ማሳዘኑን ቲም ለማ መገንዘብ ይኖርበታል። 25፣000 የኦሮሞን ወጣት ለፋሺስት ትግሬ አስረክቦ ዛሬም ነጻ አዉጭ ሁኖ መቅረብ ያስተሳሰብን ችግር ከማመላከቱም በላይ አቅምን ያለማወቅና ከጊዜዉ ጋር መራመድ ያለመቻልን ያሳያል።  ኦነጋዉያን  በድርጅታቸዉም ከድርጅታቸዉ ዉጭም ሰዉ ገድለዋል፤ ዘርፈዋል፤ አሰቃይተዋል የነሱ ተጠቂ ፍትህ እንደሚያስፈልገዉ አብይና ለማ መገንዘብ ይገባቸዋል ኦነግ በንጹህ ዜጎች ላይ ባደረሰዉ በደል ከተጠያቂነት አያመልጥም።

የኢትዮጵያን መከላከያ ሀይል በተመለከት ሻቢያን ለማጥፋት በሚል ዘመቻ ትግሬዎች ሊጠቀሙበት ከሚችሉት በላይ በነ ሰይ አብረሃና መለስ ዘራዊ አማካይነት ዘርፈዉ ወደ ትግራይ ወስደዋል። ይህ የመከላከያ ሀብት  ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሆነ ኢትዮጵያ አደጋ በገጠማት ጊዜ ፈጣን ምላሺ መስጠት በሚችልበት ቦታ መቀመጥ ያስፈለግዋል።  አንድ ድርጅት የኢትዮጵያን ሀብት ቀምቶ ዝም የሚባልበት አሰራር አግባብ ስላልሆነ ባስቸኳይ ቆጠራ ተደርጎ የመከላለከያ መሳሪያዎቹ  ለባለቤቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲመለሱ ማድረግ የማእከላዊዉ መንግስት ተቀዳሚ ስራዉ መሆን አለበት። ትግሬዎች የኢትዮጵያን የጦር መሳሪያ ቀምተዉ ጎረቤቶቻቸዉን የሚያስፈራሩበትና የሚያሸብሩበት ከህግ አንጻር ተቀባይነት አይኖረዉም። ዶ/ር አብይ ከሚፈተንበት አንዱ እነዚህን ዉድ መሳሪያዎች ሊጠቅሙ በሚችሉበት ቦታ ማስቀመጥ ይጠበቅበታል።

አብዲ ኢሌ በክልላዊ ህገመንግስት ሺፋን ኢሰብአዊ ወንጀሉን እንዲቀጥል አልተፈቀደለትም። ይህ እርምጃ በሱማሌ ሳይገደብ  የትግሬ ወንጀለኞችን ደብረ ጽዮንና ቡድኑን አድኖ ለመያዝ በተመሳሳይ መልኩ መተግበር ይገባዋል እንላለን። ያለመከሰስ  ሺፋን ትግሬዎች ወንጀለኛዉን ጌታቸዉ አሰፋን ለማእከላዊ ኮሚቴ በመምረጣቸዉ ድርጅታቸዉን  ህገወጥ በማድረጋቸዉ የህግ ሺፋናቸዉን አንስተዉታል (persona non granta) ወንጀለኛን አድኖ ለመያዝ አለም አቀፍ ህግ ስለሚፈቅድ የጎረቤት አገሮችም ኤርትራን ጨምሮ ትብብር ይሰጣሉ የሚል እምነት አለ።

ሰሞኑን ከተወሰደወ እርምጃ ባሻገር የማእከላዊ መንግስት ለትግሬዎች የሚሰጣቸዉ በጀት ቢሸመቀቅ የትግራይ ህዝብ  ወንጀለኞቹን አሳልፎ ለመስጠትና የተዘረፈዉን የኢትዮጵያ ሀብት ለባለቤቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማስመለስ ይተባበራል የሚል እምነት ይኖራል። በዚህ መልካም እርምጃም ትግራይ ክፍለ ሀገር ከወከባ ድኖ የሰላም አየር ሊተነፍስ ይችላል።

እንደሚገባኝ ተቆርቋሪ ወገኖች ጌታቸዉ ረዳ(ኢትዮ ሰማይ) አቶ ገ/መድህን አርአያ የሚጽፏቸዉን እና ጭንቀታቸዉን ትግሬዎች ሳይገነዘቡ የቀሩ አይመስልም ታድያ አረጋዊ በርሄ፤አብረሀ ደስታ፤የራያዉ  ጌታቸዉ ረዳ፤ገብሩ አስራት፤ግደይ ዘራጽዮን፤ስብሀት ነጋ፤አባይ ጸሀዬ፤ብስራት አማረ፤ቴዎድሮስ አድሀኖም፤አርከበ እቁባይ፤ሰየ አብረሀ፤ ስዩም መስፍን፤ገብረ ኪዳን ደስታ፤ጌታቸዉ አሰፋን………. የመሳሰሉ ነብሰ በላዎች የሚያጎርሷቸዉን  ሳያላምጡ ከመዋጥ በተደጋጋሚ ከመጣዉ እልቂት ያዳናቸዉን የኢትዮጵያን ህዝብ አክብረዉ ቢይዙ ለትግሬዎች አስተዋይነት የተሞላበት ዉሳኔ ይሆናል የሚል እምነት አለን ምርጫዉ ግን የነሱ ነዉ። እኛ ለነሱ መምረጥ አንችልም ካሁን በሗላ ግን በትግሬነት የሚገኝ ጥቅም ማብቃቱን መገንዘብ ይገባቸዋል።

ኢትዮጵያ ብቻዋን የምትኖር ደሴት አይደለችም ከሌላዉ ሀገር ልምድ መቅሰም ያስፈልጋታል ባለፈዉ ቻይና ሚኒስተሯ ጉቦ በላ ተብሎ በእሩምታ ተኩስ ተደብድቧል። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አገርን ለገደለ የሞት ቅጣት ይበይን አይበይን የማዉቀዉ የለም። ነገር ግን መለስ ዘራዊ ሰየ አብረሀን ለማሰር ህግ እንደለወጠ ሁሉ ደረቅ ወንጀለኛን፤ ሌባን፤ ዜጋንና ሀገርን የገደለ  በፍርድ ስርአት ለማዋል ህጉ  የማይሻሻልበት ሁነታ አይኖርም።ስለዚህ  በኢህአደግ ስም ተቧድነዉ የአገርን አጥንት የጋጡ መርከብ ሙሉ ቡና ሰርቀዉ ጠፋ ብለዉ የነገሩን እነሱ በሚፈልጉት መንገድ ሳይሆን ህግ በሚያዘዉ መሰረት ተሰንገዉ እንዲነግሩን የዶ/ር አብይ መንግስት ሸምቀቆዉን ይበልጥ እንዲያጠብቀዉ በኢትዮጵያዊነት ስም እንጠይቃለን።

እንደዉ የጠፋዉ ቡና ከተነሳ አይቀር አዲሷ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሺ ታያቸዉ  ገና ከጂምራቸዉ ወደ ጣልያን ተጉዘዉ የፋሺን እቃዎችን ሺቶና መጫሚያ ከመግዛት ይልቀ መቄዶኒያ ድርጅት ወርደዉ ለአካለ ስንኩላን መጓጓዣ ሲሰጡ የኢትዮጵያን ሀብት በጥልፍልፍ ሲዘርፉ ብዙ ቶን ቡና በምትሀት ከዲፖዉ  ሲያሰርቁ የከረሙት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ምን ተሰምቷቸዉ ይሆን? እንደዉ በዘመነ ፈላጭ ቆራጭነታቸዉ እንዲህ ያለ ሰብአዊ ነገር ሞካክሯቸዉ ይሆን? አይ ስብእና አይ ኢትዮጵያዊነት አይ ስነምግባር። ክብር ለወ/ሮ ዝናሺ ይቀጥሉበት ሀብትዎ ጥሩ ስራና የኢትዮጵያ ህዝብ ነዉ የስራ ዘመኖን ሲጨርሱ ያች ሌባ መጣች ሳይባሉ ሰዉ በደረሱበት በፍቅር ያስተናግዶታል  ከዚህ በላይ ምን ሀብት አለ? ልጆቹም የሌባ የነብሰ ገዳይ ልጆች አይባሉም አሁን ባለዉ ከተቀጠለ።

ነገሩን ለመሸከፍ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ቅድሚያ ተሰጥቷቸዉ የዶ/ር አብይ መንግስት እርምጃ ሊወስድባቸዉ የሚገባ መሆኑን እንደ ዜጋ ማመላከት እወዳለሁ፡

  1. የኢትዮጵያ መከላከያ መሳሪያዎች ከትግሬ ክልል ተለቅመዉ ኢትዮጵያ በችግር ጊዜ ባፋጣኝ ልትጠቀምባቸዉ ቀጠናዎች ማጓጓዝ
  2. ትግራይን ለማልማት በኢትዮጵያ ስም የተበደሩት ገንዘብ ክለሳ እንዲደረግበት ባለሃብቱና ከፋዩም እነሱ ስላልሆኑ እንደ መሳሪያዉ ሁሉ ይህንንም የዶ/ር አብይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዉ ዉሳኔ እንዲወስድበት
  3. የትግሬ ክልል ተከዜን አልፎ ያለመሄዱን የዮሀንስ የልጅ ልጅ ስለነገሩን የባንዳ ልጆችን ተረት ታምኖ ወረራን ህጋዊ ማድረጉ ተቀባይነት ስለማይኖረዉ ትግሬ ወደ ቀድሞ ግዛቱ ተከዜን አልፎ እንዲሄድ ማድረግ
  4. የተጀመረዉ የሌብነትና የወንጀል ተጠያቂነት ያለምንም መታከት እስከ ታችኛዉ እርከን ተኪዶ ምርመራዉን መቀጠል
  5. በትግሬ እስር ቤት ያለምመንም ጥፋት የሚንገላቱ ሲቪል እና የጦሩ አባላት ኢትዮጵያዉያን ባስቸኳይ ተፈትተዉ የህክምናና የካሳ አገልግሎት እንዲሰጣቸዉ ማድረግ የዶር አብይ ፈጣን የስራ ክንዋኔ ይሆናል ብለን እናምናለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ሰመረ አለሙ semere.alemu@yahoo.com