ዶክተር አክሎግ ቢራራ (የዓለም ባንክ አማካሪ የነበሩ)
አሜሪካ
(ይህ ምልልስ ከጋዜጠኛ እድክንድር ነጋ ጋር የተካሄደ ሲሆን፤ በውጭ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንም እንዲያውቁት በሚል መንፈስ ትንተናየ በኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ፤ በራሴ ውሳኔ ያቀረብኩት መሆኑን እገልጻለሁ፤ ጋዤጠኛ እስክንድር ላደረገልኝ ማስተካከያና ትብብር ምስጋናየን አቀርባለሁ፤ በአገር ቤት ሆኖ የሚሰጠውን አገልግሎት አደንቃለሁ)።
“ምሁራን እነማን ናቸው?
መጀመሪያ በትርጉም እንግባባ፡፡ ምሁራን ስንል ምን ማለታችን ነው? በአብዛኛው፣ ምሁራን ተብሎ የሚጠራው ክፍል ስለ አገሩ፣ ሕዝቡ፣ ህብረተሰቡ ማህበረሰባዊ፣ መንፈሳዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች አዕምሮውን፣ እውቀቱንና ችሎታውን በግልና በጋራ ተጠቅሞ ጥልቀት ያለው ጥናትና ምርምር በማድረግ መፍትሄዎችን ጸንሶና አዘጋጅቶ የሚያቀርብ ነው፡፡ ጥናቱና ምርምሩ የሚደረገው ለግል ጥቅም፣ ለዝና፣ ለንግድ፣ ለወገንተኝነት ወይም ለውጭ ኃይል ፍጆታ አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ ምሁራን የሚጫወቱት ሚና ለአገርና ለሕብረተሰብ ገንቢ እንደሆነ ግን ብዙዎችን ያግባባል፡፡
ምሁራን ወይንም ጠበብቶች፣ በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ደረጃዎች ይሰጧቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ የጃፓን ምሁራን ‹‹ታሪክ፣ የጥንት ባህል፣ ቅርሶች፣ ኃይማኖት፣ ልምዶች፣ ትምህርት፣ ቴክኖሎጅ፣ እድገት፣ ቤተሰብ ወዘተ. ተለያይተው አይታዩም፤ የተያያዙ ናቸው›› ይላሉ፡፡ ለዚህ ነው፤ ጃፓን በቴክኖሎጅ የረቀቀች ብትሆንም፣ ባህሏን ያስከበረች አገር ሆና የቆየችው፡፡ በጃፓን ምሁራን የሚከበሩት “ፈረንጅ” ስለሆኑ ሳይሆን፣ ጃፓናዊነታቸውንና፣ ከሌላው አገር ጋር ተወዳዳሪ የሆነ ከፍተኛ ትምህርት፣ ጥናት፣ ምርምር፣ ኢኮኖሚ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ወሳኝ መሆናቸውን ተቀብለው፣ ባህልን ማስከበርና ዘመናዊነትን አብረው ያስኬዷቸው፡፡ በዚህም፣ ምሁሮቻቸው ጃፓንን ጠንካራ ለማድረግ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ሳይታክቱ ያቀርባሉ፡፡ ተቀዳሚ ኃላፊነታቸው ለጃፓንና ለሕዝባቸው ነው፡፡ ጃፓናዊነትና ጃፓን ለድርድር አይቀርቡም፡፡ ይህ አይነቱ የምሁራን ሚና እንደ ደቡብ ኮሪያ፣ ቻይና እና ቬትናም ባሉ ሀገራት ታይቷል፡፡ ሚናቸው የሚዳሰስና ለፍትህ፣ ለሕግ የበላይነት፣ ለሰላም፣ ለእርጋታ፣ ለዘላቂ የሕዝብ እድገትን ማእከል ላደረገ ልማት ወሳኝ መሆኑ ተመስክሮላቸዋል፡፡
እኔ በተደጋጋሚ መነሻውን የማያውቅ ሕዝብ መድረሻውንም አያውቅም እያልኩ ስከራከር የቆየሁት ለዚህ ነው።
እኛ አገር ተከል ቴክኖሎጂን እንንቃለን
የኢትዮጵያ ተመራማሪዎች፣ በተለይ ምሁራን፣ አገር ተከል ሆነው በኢትዮጵያዊያን ተጸንሰው፣ ተሻሽለው፣ ለምርት ኃይሎች፣ ለማህበረሰቡ አገልግሎት፣ ለንግድና ሌላ ስራ ጠቃሚ የሆኑትን ባህሎችና ቅርሶች እውቅና ሰጥተው፤ተንከባክበው፣ አክብረው እንዲሻሻሉ አላደረጉም፡፡ ለምሳሌ፣ የብረታ ብረት፣ የሸክላ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የመስኖና የከብት እርባታ ስራዎችን ሀገርኛ ይዘታቸውን ሳይለቁ እንዲሻሻሉ አልተደረጉም፡፡ ኢትዮጵያ የእርሻ ልምድ ካላቸው አገሮች መካከል አንዷ ብትሆንም፣ ይህን የኢኮኖሚ ክፍል በራሳችን ጥረትና ምርምር ለማሻሻል አልቻልንም፡፡ ላሊበላን የሰራ ሕዝብ፤ ዛሬ ተመጣጣኝ ሕንጻ ለመስራት አልቻለም። ‹‹እኛ ካላሻሻልነው ማን ሊያሻሽልልን ነው?›› ብለን ራሳችን ለመጠየቅም አልደፈርንም፡፡ አገር ተከል ቴክኖሎጂዎችን የናቅናቸው ይመስለኛል፡፡
እንደ ኢትዮጵያ የሴቶች ልብስን ጌጥ አሳምሮ ልዩ ልዩ ጥበቦችን የሚያመርት አገር ያለ አይመስለኝም። ሴቶች በሙሉ እነዚህን መለያዎች አገር አቀፍ በሆነ ደረጃ የዘወትር ልብስ የማያደርጉበት ምክንያት ለኔ ግልጽ አይደለም። ወደ አርእስቴ ልመለስ!!
በነገራችን ላይ፤ እያንዳንዱ ግለሰብ በተወሰነ ደረጃ ምሁር ነው፡፡ ምሁር ከእናቱ፣ ከአባቱ፣ ከጓደኛውና ከሌላው አልተማረም፡፡ በተለምዶ ምሁር የምንለው የሚለየው፣ ለተሰማራበት ሙያ እንዲረዳውና እውቀቱ እንዲጨምር ከፍተኛ ትምህርት ማግኘቱ ነው፡፡ የመጣንበትን ሁኔታ ባንረሳ፣ ህብረተሰቡን በበለጠ ደረጃ በትህትና ለማገልገል እንችላለን፡፡ ሕብረተሰቡ ከእኛ በበለጠ ……. (Read more)