የደብረጽዮን እና የሞንጆሪኖ ሕወሓት ለምን ጌታቸው አሰፋን አሳልፈው አይሰጡም? የሚለውን መረጃ ላቀርብላችሁ ስዘጋጅ
የሕወሓቱ ሦስተኛ ሰው ጌታቸው ረዳ በኤል ሊቲቭ ላይ ወጥቶ ቃለምልልስ ሰጥቷል:: ቃለምልልሱን የተመለከተ አንድ ጋዜጠኛ ጌታቸው ረዳ “አራጁን ጌታቸው አሰፋ መናኝ እስኪመስል ዋሸን! የሚጠበቅ ነው!” ብሎታል::
ይህን ያለው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ሲሆን እርሱ በቃለምልልሱ ላይ የጻፈውን አስተያየት ላስቀድምና ቀጠል አድርጌ “ሕወሓት ጌታቸው አሰፋን አሳልፎ ከማይሰጥበት ምክንያት አንዱn” bemil በራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር አቶ ደጀኔ አሰፋ የተሰናዳውን አቀርባለሁ አብረን እንቆይ::
–
“ጌታቸው አሰፋ ከእስር ቤቶች ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም” አለ ጌታቸው ረዳ። ህወሓትና ጌታቸው ላይ ያለው ውሸት ሲደጋገም እውነት እየመሰለ መሆኑ ራሱ እየደጋገመ ዋሽቶ ሊያሳምን ጥሯል።
መጀመርያ ነገር ሰዎችን የሚያፍነው ደሕንነት ነው። ንፁሃንን አይኑን አፍኖ ኮተቤና ጦር ኃይሎች ያሉት ጨለማ ቤቶች የሚያስገባው ደሕንነት ነው። ከተማው ውስጥ ያሉ ቪላቤቶች ውስጥ፣ የፌደራል ፖሊስ ስር፣ 22ና ቄራ የሚገኝ ሕንፃ ስር አሉ በሚባሉት ድቅድቅ ቤቶች እየታፈኑ የሚታሰሩት ንፁሃን የፍርድ ቤት ማዘዢያ ወጥቶባቸው አይደለም። በደህንነት አፈና ነው። አዛዡ ደግሞ ጌታቸው አሰፋ ነው።
ማዕከላዊ መርማሪ ፖሊሶችን አስወጥተው ሌሊት ሲደበድቡ ከሚያድሩት መካከል ብዙዎቹ ደሕንነቶች ናቸው። በየድብቅ እስር ቤት ወጣቶችን የሚደፍሩት ነውረኞች ደሕንነቶች ናቸው።
እስር ቤቶቹ ከብሔራዊ ደሕንነት ጋር የሚያገናኙ ደሕንነቶች አሉት። የጥበቃና ደሕንነት ውስጥ የሚሰሩት ከፖሊስ ይልቅ ለደሕንነት መስርያ ቤቱ የሚሰሩ ናቸው። ሌላው ቀርቶ የደሕንነት መስርያ ቤቱ ፖሊስን ስለማያምን አንዳንድ እስረኞችን የራሱን ሰው አስቀምጦ ፍርድ ቤት ይወስድ ነበር። በቃጠሎው የተከሰሱትን እየነጠሉ ያደርሱ የነበሩት ደሕንነቶችም ነበሩ።
ደሕንነት መስርያ ቤቱ በእስር ቤት ውስጥ እንደማያዝ ሊነግረን የሚሞክረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ያህል ሞኝ ቢመስለው ነው? እስር ቤቱ ውስጥ ማስመሰያ ክስ ተሰጥቷቸው እስረኞችን የሚሰልሉ፣ እብድ መስለው እየዘላበዱ እየዋሉ የእስረኛውን መረጃ ለደሕንነት መስርያ ቤቱ የሚሰጡትን የሚያውቅ ያለ አይመስለውም?
ሌላው ቀርቶ ፍርድ ቤቱ ፈትቸዋለሁ እያለ እስር ቤት የሚከርሙት እስረኞችን ማን ነበር የሚያቆያቸው? አቶ ጌታቸው ረዳ አንድ እስረኛ ሊፈታ ሲል እንኳ ብሔራዊ ደሕንነት ሰው ልኮ እንደሚያናዘው ሊያውቅ የሚችለው ወይ ሲቀምሳት ነው አሊያም መሸምጠጥ አመል ሆኖባቸዋል። የእስር ቤት ኃላፊዎች በላይ ጌታቸው አሰፋ የላካቸው ደሕንነቶች በእስረኛ ጉዳይ ላይ እንደሚወስን ብዙ ሰው የሚያውቅና የገጠመው አይመስለውም። የደሕንነት መስርያ ቤቱን ብቻ ሳይሆን ያን አረመኔ ጌታቸው አሰፋ ከሰው አይን የራቀው አራጅ ስለሆነ ሳይሆን የመነነ መነኩሴ አስመስሎ ዋሸብንኮ! አይ ክፉ አመል። አይ ክፉ ባህል! አይ ክፉነት! የውሸት አባቶች!
ይህም ሁሉ ቀርቶ ደሕንነት መስርያ ቤቱ ብቻ ሳይሆን ትህነግ/ህወሓት ገራፊና አስገራፊ መሆኑ ከሕዝብ የተደበቀ ይመስለዋል። ራሱ ጌታቸው ረዳ ከዚህ ወንጀል ነፃ ነው የሚለው ይመስለዋል። እውነታው ሌላ ነው። ጌታቸው አሰፋ ቀርቶ ጌታቸው ረዳ ለተፈፀመው ጭካኔ ተጠያቂ ነው። በመላው ኢትዮጵያ ከተፈፀመው ባሻገር የተወለደበት ራያ ላይ የፈፀመውንና ያስፈፀመውን ማን የሚረሳ መስሎት ይሆን? ግልፅ የሆነው ውሸት ከተጠያቂነት እንደማያተርፍ ከጓደኞቹ ያልተማረ መሆኑን ብቻ ነው።
—
አሁን ሕወሓት ጌታቸው አሰፋን አሳልፎ ከማይሰጥበት ምክንያት አንዱን ላስቀጥል::
ጌታቸው አሰፋን አሳልፎ ከማይሰጥበት ምክንያት አንዱ!!
==========
ዋናው ምክንያት ብላክ ሜይል ስለሚያደርጋቸው ነው። የእያንዳንዱን የትህነግ ባለስልጣን ወንጀል ጌታቸው አሰፋ መረጃና ማስረጃ አለው። ይህንን መረጃ ደግሞ ከራሱ በተጨማሪ የሚያምናቸው ሰዎች ጋር በውጭ ሃገር አስቀምጧል። ድንገት ቢያዝ እነዚህ ሰዎች መረጃውን ያወጡታል ተብሎ ይነገራል። በነገራችን ላይ የዋነኞቹ የትህነግ ባለስልጣናት ዝርፊያ ካላቸው ቤትና የቤተ ዘመድ እንቅስቃሴ አንፃር በወፍ በረር እነሆ
1ኛ) ጌታቸው አሰፋ – መቀሌ ፣ አዲስ አበባና #ብራስልስ ገራሚ ቤቶች ያሉት ሲሆን ሚስቱ ደግሞ እጅግ ቅንጡ እና ዘመናዊ ሴት በመሆኗ ሾፕ የምታደርገው ዱባይ ለንደን እና ዲሲ ነው። ሴትየዋ የጌታቸው ሚስት በመሆኗ #ሾፕ የምታደርገው እነ አንጀሊና ጆሊ ደንበኛ የሆኑባቸው እጅግ ውድ ቦታዎች ናቸው። በሾፒንጉ የአላሙዲን መኪኖች እና ጋርዶች ያጅቧታል!!! የሴትየዋ ታናሽ ወንድም የስቶክሆልም ባር እና ላውንጅ ባለቤት እንደሆነ ይታወቃል።
ጌታቸው አሰፋ በጣም #አስቀያሚ ስብዕና ያለው ሲሆን መሳሪያ የታጠቁ የኤርፖርት ወታደሮችን በጥፊ የሚማታና ብሎም የቀድሞው ጠ/ሚ ሃማደ የፕሮቶኮል ሹምን በጥፊ የመታ ሰው ጭምር ነው። ማለትም ከሚፈፅማቸው የታወቁት ወንጀሎቹ በተጨማሪ ስርዓት አልበኛና ጋጠወጥ ነው ለማለት ነው!! ጌታቸው ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን ለማስገደል ላውንቸር ይተኮስበት ያለና ሰፈሩ ሁሉ እንዲጋይ ትዕዛዝ የሰጠ አረመኔ ሲሆን ኮለኔል ደመቀ ግን ምላሹ ምን እንደነበር አይዘነጋም!!
ጌታቸው ሰውን እጅግ ተጠራጣሪ ከመሆኑ የተነሳ የትም ቦታ ሄዶ ምግብም ሆነ ዉሃ አይጠቀምም። ምግብ ከቤቱ ይዞ ይወጣል ፣ ዉሃ ከመኪና ወርዶ ራሱ ይገዛል ፣ አንድ ሱቅ ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ አይጠቀምም። በአንፃሩ መሳቅ ይወዳል። የሚያስቁትን ያሿማል ፤ አጫዋቾቹም ይሆናሉ። እሱ በውሃ እነሱ በአልኮል ሲያጫውቱት ያመሻሉ። ካላጫወቱት የሚከተላቸውን እነሱም ያውቁታል። ከነዚህ ውስጥ የምናውቃቸውም አይጠፉም!!!
ይህ ሰው ጠ/ሚ ዶ/ር አብይን ለማስገደል የሰኔ 16ቱን ሴራ የጠነሰሰና ትዕዛዝ የሰጠ መሆኑ ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ትህነግ ደግሞ በማዕከላዊ ኮሚቴነት መርጦ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባልም አድርጎታል። መልዕክቱ ግልፅ ነው!!!
በሚቀጥለው ስለ ደብረጽዮን እና የሆንግኮንግ ቤቱ ትንሽ እናወራለን።
2ኛ) ዶ/ር ደብረፅዮን – መቀሌ ፣ አዲስ አበባና ሆንግኮንግ ቅንጡ ቤቶች አሉት። በተለይ የሆንግኮንጉ ቤቱ በጣም የሚወደውና እንደ ዋና ቤቱ የሚመለከተው ነው! በምርጫ ደረጃም ከአዲስ አበባ ይልቅ ሆንግኮንግ የሚመርጥ ሲሆን በህክምናም ሆነ በሌሎች ሰበቦች እዚያው ሄዶ ማሳለፍን ና መዝናናትን ይመርጣል። ቤቱ ዘመናዊ ከመሆኑ ባሻገር ሙሉ የሴኩሪቲ እና የመዝናኛ መሰረተ ልማቶች የተሟሉሉት ነው ተብሏል። ደፂ እና ሆንግኮንግ ልዩ ፍቅር አላቸው።
ዶ/ር ደብረጽዮን የውሳኔ ሰው አለመሆኑን (Indecisive) መሆኑ በማዕከላዊ ኮሚቴው ዘንድ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ያለውን ነገ እንደማይደግምና የሚናገረው ነገር ስለመተግበር አለመተግበሩ የሚጨነቅ ሰው አይደለም! ውድ ባለቤቱ የዛሬ 8 ወር ገደማ ቦሌ አካባቢ እጅግ ውድ የሆኑ ልብሶች እና ጌጣ ጌጦች የሚሸጡበት ሱቅ የከፈተች ሲሆን ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት #ጀርመን ነው።
3ኛ) ዓለም ገ/ዋህድ – የትህነግ ፅ/ቤት ሃላፊ ሲሆን እንደ ደብረፅዮን እሱም በመቀሌ ፣ አዲስ አበባ እና ሆንግኮንግ ቤት አለው። ሴት ልጁን ስዊድን ሃገር ያስተምራል።
4ኛ) አዲስ አለም ባሌማ – በመቀሌ ፣ አዲስ አበባና ዲሲ በጣም ዘመናዊ ቤቶች ያሉት ሲሆን ሚስቱም የአርከበ እቁባይ እህት ናት። ሚስቱ በከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ ጨረታዎች (የ200 – 300 ሚሊየን ብር) ያለ ብዙ ተቀናቃኝ የምታሸንፍ ሴት ናት። ከሰሞኑም በሴትየዋ ላይ መረጃዎች እንደወጡ ልብ ይሏል።
5ኛ) ጌታቸው ረዳ – የትህነግ ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ እና የትግራይ ምሁራን እና ሚዲያ ዘርፍ ሃላፊ ሲሆን በመቀሌ በአዲስ አበባ እና በአሜሪካ ዲሲ ቆንጆ ቤት አለው! ብዙውን ጊዜ በዲሲ የሚያሳልፍ ሲሆን ወጭው ከፍተኛ እንደሆነና የጌታቸው አሰፋ ጥብቅ ወዳጅ እንደሆነም ይነገራል።
ከዚህ ቀደም እንደተገለፀው የራያን እና የወልቃይትን አጠቃላይ ጉዳይ የሚመሩት ጌታቸው ረዳና ጌታቸው አሰፋ ሲሆኑ በጥምረት ልዩ ሃይሉን በቀጥታ ያዛሉ!!! የጌታቸው አሰፋን የእስር ማዘዣ ተከትሎ የራያን ጉዳይ ጌታቸው ረዳ ሙሉ ለሙሉ ይይዘዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለአብዛኞቹ የራያ ሽማግሌዎች እስር የሁለቱ እጅ ዋነኛ ነው ተብሏል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የምሁራን እና ሚዲያ ዘርፍን ፎርማሊ የሚመራው ጌታቸው ረዳ ቢሆንም ዘርዓይ አስገዶም ደግሞ ኢንፎርማሊ የሚያስተባብር ነው። በዚህም አዲስ አበባ ያለውን ኮሚቴ በረንዳ አዳሪዎች ወዘተ ብሎ ረዳኢ ሃለፎም እንዲሳደብ ኦሬንቴሽን የሰጡት ሁለቱ ሲሆኑ በራያ ጉዳይ የሚሰሩ የሚዲያ ዘገባዎች እና የምሁራን ውይይት ብሎም ኬሪያ ኢብራሒም መቼ ፣ ምን እና እንዴት መናገር እንዳለባት ጭምር አቅጣጫ የሚሰጡት ጌታቸው ረዳ እና ዘርዓይ አስገዶም ናቸው። ስለ ዘርዓይና ሌሎቹ እመለስበታለሁ።