አነሰም በዛም  ዛሬ ላይ ብዙ ቦታ ላይ ሰው ሰከን እያለና ወደራሱ እየተመለሰ ነው፡፡ ወለጋ ግን በገዛ ፍቃዱ እድሉን ለሚሸጡት ሰጥቶ ይተራመሳል፡፡ ሰሞኑን በወለጋ እነ ጀዋርና በቀለ ገርባ ሲፈነጥዙበት ከርመው አሁን በሰፊው ጸረ-ኢትዮጵያና ሰላም ዘመቻቸውን እያስኬዱት ነው፡፡ በወለጋ ሕዝቡን እየሰበሰቡ ለቀጣይ ገበያቸው ሲያስማሙት ነበር፡፡ የገረመኝ ነገር ግን የእዛ አካባቢ ሕዝብ የሽብር የኦኤምኤንን ወሬ ብቻ ስለሚሰማ ነው መሰለኝ እየሆነ ስላለው ነገር እንኳን ምንም ፊንጭ ያለው አይመስለም፡፡ የሚመስለው ከ1 ዓመት በፊት የነበረው አይነት ነው፡፡ እነጀዋርም ሕዝቡ ስላልነቃ ተደስተዋል፡፡ ያሳዝናል! የኦሮሞ ትግል ይቀጥላል ይላሉ አሁንም፡፡ ሕዝቡን በራሳቸው አስተሳሰብ ባርነት ሥር አድርገው ይፈነጩበታል፡፡ ኦነግ 50 ዓመት በነፃ አውጪ ሥም የቆምራል፡፡  እንኳን 50 ዓመት ይቅርና ባለፉት 8 ወራት እንኳን ብዙ ነገር ሆኖ አልፏል፡፡ 50 ዓመት እኮ አንድ የመንግስቱ አገዛዝ ሁለት 27 ዓመት የወሮበሎች ዘመን አክትሞ ሌላ ምዕራፍ ከተጀመረ 8 ወር አለፈው፡፡ ለመሆኑ ግን የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ እየተባለ እሰካሁንም በሕዝብ የሚነገድበት አስተሳሰብ መቼ ይሆን ጥያቄው ተመልሶ  ኦሮሞ ነጻ የሚወጣው? የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ ዋና ጠያቂ ነን የሚሉት ከጅምሩ ጥያቄውን ስለአበላሹት ኦሮሞ ራሱ ነቅቶ እነዚህን ነጋዴዎች ከላዩ ላይ ከአላሰወገደ መቼም ቢሆን ነጻ የሚወጣ አይመስለኝም፡፡ በአለፉት 27 ዓመትንም ጨምሮ ኦሮሞን በባርነት የያዙት የኦሮሞን ፖለቲካ የሚነግዱበት ኦሮሞ ነን የሚሉት ናቸው፡፡ አሊያማ የወያኔም መጫወቻ ባልሆነ፡፡ እራሱንም ነጻ አድርቶ ለሌሎችም ነጻነት ጉል ድርሻ በኖረው፡፡  ይህ እንዳይሆን ግን ከጅምሩ ኦሮሞን ከራሳቸው አስተሳሰብ ባርነት ሥር እንዳይወጣባቸው ቆርጠው የተነሱ የኦሮሞ ፖለቲካ መሪዎች ናቸው፡፡ ወለጋ ዛሬም እንዲህ ነው የሚደነፋው

https://www.facebook.com/nikeey1/videos/2021879734546071/

በአለፉት 27 ዓመት ከወያኔ ዳረጎት እየተቀበሉ ኦሮሞን ሲያሳርዱ ምንም አቅም እንዳይኖረው ሽባ ሲያደርጉ የኖሩ አሁንም እነሱው ዋና ሆነው ነጻ እናወጣሀለን በሚል ከእነሱ ሥር እንዳይወጣባቸው እየተሯሯጡ ነው፡፡ ችግሩ እኮ ነጻ ከማይወጣበት የዘረኝነትና ጥላቻ ባርነት ሥር ያዋሉት መሪዎቹ ናቸው፡፡ ይሄንኑ አስተሳሰብ ዛሬ ላይ ወደሌሎችም በስፋት እየተሰራጨ ነው፡፡ በአንጻሩ እንደውም ብዙ የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ላይ ነገሩ እየገባው ነው እንደወለጋ ያሉ ቦታዎች ከእነጭርሱም ባይረዱትም፤፡ በአማራ እንደ አዲስ እየተስፋፋ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ የእነጀዋር ኦነጋውያን የንግድ ቡድን ኦሮሞን እንደ ቋሚ መደበቂያ በማድረግ ለመኖር ነው፡፡ በ27ዓመቱ የግፍ ዘመን የኦሮሞን ሕዝብ ለወያኔ በመነገድ የኖሩበት ኑሮአቸው ሚስጢሩ ሊወጣ ጫፍ ላይ ስላለ እንደነ ጀዋር የመሳሰሉት እብድ ሆነዋል፡፡ እነ በቀለ ገርባ ወደፊት ኦሮሞን ለንግድ በማቅረብ አስበው ነው እንጂ እስከዛሬ ከወያኔ ብዙም ተጠቃሚ አልነበሩም፡፡ በእርግጥም ጫፍ ጫፉ እየደረሳቸው ነው፡፡ በቀለ ገርባ ፍጹም ዘረኛና በጥላቻ የተመረዘ ሰው መሆኑን በይፋ አይተናል፡፡ ግን ኦሮሞ ውስጥ በመደበቅ ትልቅ ፖለቲከኛ አልፎም ምሁር ሆኗል፡፡  የተማረው ያንሰዋል አደለም፡፡ ሆኖም ለተማረው ትምህርት ቦታ ያልሰጠ መሆኑ ነው እንጂ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በመምሕርነት እንደተቀላቀለ ነግሮናለ፡፡ እንደ እውነቱ ለዚህ ያበቃው ከኦሮሞነቱ ውጪ ሌላ ምንም ሆኖ አላየውም፡፡ ጀዋር ቀድሜም ተናገሬ ነበር፡፡ ሳሙኤል ዘሚካኤልን ማስታወስ ጥሩ ነው፡፡ ሆኖም የሁለቱ ልዩነት ጀዋር በብዙ ቁማር ወንጀል ከሰሩ ጋረ በሚስጢር ተቀጣሪ ሲሆን ሳሙኤል ሙሉ በሙሉ በግሉ መሆኑ ነው፡፡ ጀዋርን ከጅምሩ ወደ ሲንጋበፖር የላከው ማን ነበር? ስኮላፕ የሰጠው ወያኔ ወይስ ሌላ አካል? ብዙ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ያልተማሩትን ትምህርትና የሌላቸውን እውቀት በድፍረት አለን በሚል ይታወቃሉ፡፡ ፕሮፌሰር ነኝ የሚለው ሕዝቅኤልን ጨምሮ፡፡ የሠሩት ሳይንሳዊ ሥራ ግን ብንፈልግ አናገኘውም፡፡  ጀዋር በሰታን ፎርድ ግቢ ገብቶ ትንሽ ኮርስ ቢጤ ወስዶ ሳይሆን አይቀርም በድፍረት ፖለቲካል ሳይንስ የሚለው፡፡ ኧረ እንደውም ፒ.ኤችዲም ጀምሬ ዘብጬው ትቸው ነው እያለን ያለው፡፡ ሲጀምር በልዩ ሁኔታ ከአልሆን ፒኤች ዲ በቀጥታ ከባችለር የማይመስል ነው፡፡ ልብ በሉ ሲንጋበፖር ተማርኩበት የሚለው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንጂ ዲግሪ አይሰጥም፡፡ እንግዲህ ዲግሪው ሰታንፎርድ መሆኑ ነው፡፡ ከዛ ለእሱ ምን ይሳነዋል ፒኤች ዲውን ጀመረ፡፡ ጥያቄው ግን ከእነጭርሱ ባችለሩስ አለው ወይ ነው፡፡

ተማሩ አልተማሩ የራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡ ግን ሕዝብን በምሁርነት ሥም የንግድ እቃ ማድረጋቸው ላይ ነው፡፡ ኦነጋውያን በሐሳብ እንደማያሸንፉ አሳምረው ያውቁታል፡፡ ለዛም ነው የመንጋ ፖለቲካ ዋነኛ ስልት ያደረጉት፡፡ ሕዝብ ከነቃ የመንጋውን ፖለቲካም ያጡታል፡፡ ያም ብቻ አደለም ለዘመናት ሲሰሩት የኖሩትም ይጋለጣል፡፡ አስበውት የተነሱት የኦሮሞን ሕዝብ በመጠቀም ወያኔን ለማዳን ነበር፡፡ አልሳካ አለ እንጂ፡፡ እስካሁን የሆነውን አስተውሉ፡፡ አሁን ምርጫ ሽግግር መንግስት ምናምን የሚሉትም ግርግር ለሌባ ያመቻል እንደሚባለው አስበው ነው፡፡ በእነሱ ሂሳብ እስከ ምርጫ ድረስ እንዲሁ በግርግር ለመቆየትና ምርጫ ሲደርስ አጋጣሚውን በመጠቀም ትልቅ ትርምስ ለመፍጠር ነው፡፡ ያ ግን እየተሳካላቸው አደለም፡፡ ምርጫው ከመድረሱ በፊት ጠንካራ የሆነ የመንግስት አደረጃጀት እየተሰራ ይመስላል፡፡ ለዛም ነው አሁን የሽግግር መንግስት በሚል ሌላ ውዥንበር ለመፍጠር የሚጥሩት፡፡ በመንጋ እንጂ በሐሳብ ምርጫም ቢመጣ እንደማያሸንፉ አውቀዋል፡፡ የመረራ ኦፌኮ ራሱን እያስበላ ይመስለኛል፡፡ ዛሬ  ኦነግ ወለጋን ታቅፈፎ እየቀረ ነው፡፡ በጀዋር በኩል ባሌንና ሐረርን ወደራሱ ንብረትነት ቢሞክርም የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ ወለጋ ለብዙ ኦሮሞዎች አደጋ ነው፡፡ለሐረር ከወለጋ ሱማሌ ምን አለው፡፡ ለባሌስ፡፡ በእርግጥም ከአጎራባቹ በሠላም መኖሩ ነው ዋናው፡፡ የወለጋዎቹ ኦነጎች የሱማሌንና ኦሮሚሮሞን ሕዝብ በአብዲ ኢሌ ሽፋን ብዙ መከራ አድርሰውበታል፡፡ በኦሮሞነት ሲያቅታቸው በሐይማኖት ይሞክራሉ፡፡

በአብይና ለማ ላይ ግን አሁንም ትልቅ ቅሬታ አለኝ፡፡ እነ ጀዋር እንደልባቸው እንዲፈነጩ አድርገው የሠላሙን መምጫ እያዘገዩት ነው፡፡ ጀዋር በዜግነትም ኢትዮጵያዊ መሆኑ አጠያያቂ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ በምን ሒሳብ በኢትዮጵያ ምድር ሕዝብ እየሰበሰበ ይደራደራል የሚለውን ጥያቄ ደጋግሜ አንስቼ ነበር፡፡ አሁንም እነ አብይ ቸል ሊሉት ፈልገዋል፡፡ ቄሮን ቄሮ ያደረገው ለማ ነው፡፡ እነጀዋርማ ለራሳቸው ሊጠቀሙበት ነበር፡፡ አሁን ቄሮ እነለማን ቸል ማለት ሲጀምር ተመልሶ እዛው የባርነት አስተሳሰብ ውስጥ ገብቷል፡፡ ለመሆኑ ከማን ነው ነጻ የሚወጣው፡፡ አልተመለሰም የሚባለው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄስ ምንድነው? ኦሮሚያን ከን ኦሮሞቲ የሚለውና ሌሎችን የመጥላትና የዘረኝነት ጥያቄ ከሆን መቼም አይመለሰም! ስለዚህ ከዚህ አስተሳሰብ መውጣት እስካልቻለ ድረስ መቼም ነጻ አይወጣም፡፡ ሁሉም ራሱን ከራሱ አስተሳሰብ ነጻ ያውጣ! በኦሮሞነት አገኘዋለሁ የሚል አስተሳሰብ ይዞ መቼም ነጻ መሆን አይቻልም፡፡ ማንም እንደፈለገ የሚዘውረው ሕዝብ አይኑር፡፡ መንግስት የሠላም ሚኒስቴር እስከመቋቋም ደርሻለሁ ከአለ ዜጎች በሚገባ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡ ማንም በመንጋ ፖለቲካ ሕዝብን የንግድ እቃ ማድረጉን ማቆም አለበት፡፡ ይሄን ደግሞ መንግስት ስርዓት ሊበጅለት ያስፈልጋል፡፡ ሕዝብን ሰብስቦ ለማነጋገርም ሆነ ለመደራደር መጀመሪያ በኃላፊነት ሊወስድ የሚችል ቡድን ሊሆን ይገባል፡፡ የፖለቲካ ቡድን ነን የሚሉትን ጨምሮ ከሕግና ሥርዓት ውጭ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሊገደብ ይገባል፡፡ ከሁሉም በፊት የዜጎች ደህንነት ይቅደም፡፡

አመሰግናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ