ክመኮነን ተስፋየ የፌስቡክ የተወሰደ

ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ፍሬህይወት ተሰማ ማን ናት????

(ፎቶው ላይ የሚታየው ጀግናዋ ፍሬህይዎት በወጣትነትዋ ዘመንና በአሁኑ ግዜ ከአንዱ ወንድ ልጅዋ ጋር የተነሳችው ነው)

በእስር አብሮ ከነበረና ስሙም መገለጽ ካልፈለገ ጓድ ስለ ፍሬህይወት ተሰማ የተሰጠ የአይን ምስክርነት እንዲህ በማለት ይጀምራል….“ፌሬህይወት የነበራትን አቁዋም ማንም ሊያጎብጠው ያልቻለ ሞትን አሸንፋ እንደገና ለመሞት ራሱዋን ያዘጋጀች እንደነበር እኔም አረጋግጣለሁ እስርቤትም ውስጥ የብዙዎችን ፀጉር መስራት የምትወድና ፍቅርን ሳትሰስት የምትቸር ጓድ ነበረች”……

ከዛም በኋላ ምስክርነቱን እንዲህ በማለት ይቀጥላል…….“ፍሬህይወት ተሰማ ከእናትዋ ከወ/ ሮ አበቤ ጭቅዋላና ከእባትዋ አቶ ተሰማ አንበሴ በደብረዘይት ከተማ በቀበሌ 11 ተወለደች፡፡ ትምህርቷንም በሐረር ሜዳ ሞዴል ትምህርት ቤት ተከታተለች ። በኢሕአፓ ተሳትፎዋም መዋቅር ደረጃ በስኳድነት ተቋም ተመልምላ ስልጠና የወሰደችና በተለያዩ ወሳኝ ሚሽኖች ላይ የተካፈለች ጓድ ነበረች፡፡

የደብረ ዘይት ከተማ የፓርቲው መዋቅር በፍጥነት መመታት ሲጀምር እንጃ የሆነው ተስፋዬ ለገሰ ከታችኛው የመዋቅር ደረጃ ብዙ ጓዶችን እያወቀ የሪጅኑ ሃላፊነት ላይ በመድረሱ በተለይም የስኳዱን ክንፍ ብዘወቹን በማጋለጥ ከፍተኛ ጥፋት አድርሷል፡፡ፍሬህይወትም የዚ እንጃ ሰለባ ነበረች፡፡

ፍሬህይወት በእንጃው ተስፋዬ ለገሰ ተጠቁማ ከፍተኛ ግብረሰይል የተፈፀመባት ሲሆን በመጨረሻም ለመግደል አውጥተው ገደልናት ብለው ጥለዋት ከሄዱ በኋላ እሷም አለመሞቷን አረጋግጣ ቅርብ ወደሆነ የምታውቃቸው ሰዎች ቤት ተነስታ በሰቆቃ ትደርሳለች፡፡እዛም ስትደርስ የሚያስጠጋት አላገኘችም፡፡

ከዝያም በምን ሁኔታ ወደ እስር ቤት ተመልሳ እንደገባች አይታወቅም ሆኖም ለመግደል የተተኮሰባት ጥይት ጉሮሮዋን ጨርፎ ትልቅ የቁስል ጠባሳ እንደነበረባት ይታወቃል ። ፍሬ ህይወት ረዥም ጥብቅ ያለ የሰውነት ቁመና የነበራት ማንም ተመልክቶ የነበራትን ንቁና ቀልጣፋ የስፖርተኛ ትክል ሰውነት አይዘነጋውም፡፡

ስትናገር ድምጿ የዜማ ቅላፃ የነበረው ስለሆነ በሁሉም ሰው ትወደድ ነበር፡፡ በጊዜው ከመንጥር ኮሚቴ ጋር ያላትን አቋም በጥንካሬ ያስረዳችና በአቋሟ ጸንታ አልንበረከክም ብላ የተፈታተነች መሆንዋን ሁሉም አብሯት የታሰረ ያውቃል፡፡ ሞትንም አሸንፋ እንደገና ራሷን ለመሞት ያዘጋጀች እንደነበረች አስመስክራለች

ፍሬህይወት በእሁኑ ግዜ ባለትዳርና የ3 ልጆች እናት ሆና ትኖራለች፡፡

ፍሬህይወት ተሰማ ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ናት !!!!! በጣም እንኮራባታለን!!!!

አንድነት ሃይል ነው !!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!

አንድነት ሃይል ነው !!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!

 

Image may contain: 1 person, closeupImage may contain: 2 people, people standing
Image may contain: 1 person, closeup