ዛሬ የትግሬ ሕዝብ ትግራይ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ከተሞች በነቂስ በመውጣት ሰልፍ አድርጎ የሀገሪቱን ካዝና አራቁተው የዘረፉትን ሌቦችና ወንበዴ ልጆቹ፣ በዜጎች ላይ ለመስማት የሚዘገንን፣ እጅግ ጸያፍ ነውረኛ ሰቆቃ (ቶርቸር) እና አረመኔያዊ ግፍ የፈጸሙ አጋንንት ልጆቹ ለፍርድ መቅረባቸውንና እንዲቀርቡ መጠየቁን በመቃወምና በማውገዝ ሰልፍ ወጥቷል፡፡ የወያኔን አባባል በመጋራትም ሕወሓት ማለትም የትግሬ ሕዝብ ማለት መሆኑን የትግሬ ሕዝብ ማለትም ሕወሓት ማለት መሆኑን በጉልህ አስተጋብቷል፡፡

እንግዲህ ምን እንላለን!” እንዲል መጽሐፉ የትግሬ ሕዝብ ይሄንን ያህል ደንቁሮ፣ በእብሪት ታውሮ፣ በጥጋብ ተደፍኖ ማሰብ ተስኖት በራሱ ላይ ከፈረደ እኛ ምንም ልናደርግለት የምንችለው ነገር የለም!!! ጥቅማቸውን እነሱ ያውቃሉና!!!

እኔ በግሌ እንደምታውቁት እየተወሰደ ያለው የእስር እርምጃ የማስመሰል እንጅ እውነተኛ ነው ብየ የማምን ሰው አይደለሁም፡፡ ይሄንንም በብዙ አመክንዮዎች ለማረጋገጥ ለማሳየት ለማስረዳት ስሞክር ቆይቻለሁ፡፡ አሁን ለጊዜው ግን የእስር እርምጃው እውነት ነው ብለን እንውሰድና ዛሬ የትግሬ ሕዝብ በወንጀለኞች ላይ እየተወሰደ ነው የሚባለውን የእስር እርምጃ በመቃወምና በማውገዝ በተለያዩ ከተሞች ያደረገውን ሰልፍ እንድምታ እንመልከት፡፡

የወያኔ ባለሥልጣናት እራሳቸውን ከተጠያቂነት ነጻ ለማውጣት በማሰብ እስራቱ ፖለቲካዊ ነው፣ የትግራይ ሕዝብን ለማንበርከክ የታሰበ እርምጃ ነው!” እያሉ የወሸከቱትን መናኛና አሳፋሪ ምክንያት የትግሬ ሕዝብ ነቅቶባቸው “””እኛን የትግራይ ሕዝብን እንወክላለን እያላቹህ ይሄንን ሁሉ አድርጋቹህ በእጅጉ ካዋረዳቹህን በኋላ ይሄንን የማለት የሞራል ብቃቱ የላቹህም! ይሄ ጉዳይ የሚታሰባቹህ ከሆነ ይሄንን ማሰብ የነበረባቹህ ድርጊቱን ከመፈጸማቹህ በፊት ነው እንጅ ፈጽማቹህ ካዋረዳቹህን፣ አንገታችንን ካሰበራቹህን በኋላ እንዲህ ማለት የሌባ ዓይነደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ!” እንዲሉ የሌባ ዓይነደረቅነት ነው፡፡ አዎ እውነት ነው ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው፡፡ ፖለቲካዊ የሆነው ግን ለፈጸማቹህት አስነዋሪ፣ አዋራጅ፣ አሸማቃቂ ወንጀላቹህ ተጠያቂ ስትሆኑ ሳይሆን ከጅምሩ ገና የትግራይ ሕዝብን እንወክላለን፣ እኛና የትግራይ ሕዝብ አንድ ነን እያላቹህ ነውረኛ ድርጊቱን ስትፈጽሙ ነው ፖለቲካዊ የሆነው፡፡

የትግራይ ሕዝብን ለማንበርከክ ነው ላላቹህት ግን ማንም ይሁን ማን ሌባና ወንጀለኛ ተጠያቂ መሆኑ፣ የሕግ የበላይነት መረጋገጡ የትግራይን ሕዝብ ያንበረክካል!” ማለት የትግራይ ሕዝብ የቆመው በሌቦችና ወንጀለኞች ነው!” ማለት ስለሆነ እያዋረዳቹህን እያንበረከካቹህን ያላቹህት እናንተው እራሳቹህ እንጅ ሌላ ማንም አይደለምና እውነት የታገላቹህት ለኛ ለትግራይ ሕዝብ ከሆነና የትግራይን ሕዝብ የምትወዱት፣ ከራሳቹህ በላይ አድርጋቹህ የምታዩት ከሆነ እባካቹህ ከጎናቹህ እንድንቆም በማድረግ የወንጀላቹህ ተባባሪ አድርጋቹህ፣ አታዋርዱን፣ የታሪክ ተወቃሽና ተከሳሽ አታድርጉን፣ በስማችን መነገዳቹህን አቁማቹህ ለሕግ እጅ ስጡ!

ጉዳዩ ፖለቲካዊ እንዳይሆን ከፈለጋቹህ የፈጸምነው ወንጀል የሚመለከተው እኛን ወንጀለኞቹን እንጅ የትግራይ ሕዝብን አይደለም!” ብላቹህ ለሕግ አካል እጃቹህን ስጡ! ያኔ ጉዳዩ የፖለቲካ መሆኑ ቀርቶ የፍትሕ ጉዳይ ይሆንና እዚያ ላይ ያልቃል፡፡ ወንጀላቹህን እንደያዛቹህ፣ በግፍ እንደተጨማለቃቹህ እኛን የትግራይን ሕዝብ ከጎናቹህ እንድንቆም ማድረግ ግን የትግራይን ሕዝብ የወንጀላቹህ ተባባሪ በማድረግ ማዋረድ ስለሆነ እባካቹህ ከዚህ ፈጽሞ ኃላፊነት ከጎደለውና የደነቆረ ተግባራቹህ ታቀቡልን??? መንግሥት አላፊ፣ ጠፊና ተቀያያሪ ነው፡፡ ሕዝብ ግን ዘለዓለማዊ ነውና ለእናንተ ለምታልፉት ለምትጠፉት ዘለዓለማዊ ላልሆናቹህት ለወንጀለኞቹ ጥቅም ብላቹህ የማያልፈውን፣ የማይጠፋውንና ምድር እስካለች ጊዜ ድረስ ዘለዓለማዊ የሆነውን ሕዝብን በማሳሳት ለዘለዓለሙ የታሪክ ተወቃሽና ተከሳሽ ሆኖ ቆስሙ እንዲሰበር፣ ተዋርዶ እንዲቀር አታድርጉ???””” በማለት ፈርጠም ብሎ ይናገራቸዋል ብየ ጠብቄ ነበር፡፡

ነገር ግን ችግሩ ያለው፣ የችግሩ ሰንኮፍ ተሸካሚ ከሆነው፣ ወያኔን ከወለደው ማሕፀን ከትግሬ ሕዝብ እንጅ ከውላጁ ከወያኔ ባለመሆኑ የትግሬ ሕዝብ እንዲህ ከላይ እንደገለጽኩላቹህ አስተዋይነት፣ ብስለትና አርቆ ማሰብ የተሞላበትን አስተሳሰብ ፈጽሞ ሊያስብ አልቻለም፡፡

እጅግ በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ተግባር ነው የትግሬ ሕዝብ እየፈጸመ ያለው፡፡ እኔ አንድ ሕዝብ በዚህ ደረጃ ደንቁሮ፣ አብሮ ለመጥፋት ቋምጦ፣ እጣፋንታውንና ዕድል ተርታውን ከአላፊና ጠፊ የጥፋት ቡድን ጋር አቆራኝቶ አስተሳስሮ በማጫፈር ታላቅ ስሕተት እየፈጸመ እንዴት ሊዘቅጥ እንደሚችል ባስበው ባስበው ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም፡፡

የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግሬ ሕዝብን እጅግ ከሚገባው በላይ መታገሱ ይታወቃል፡፡ የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግሬ ሕዝብ ወያኔን ወልዶ፣ ለወያኔ ኃይል ጉልበት ጥላ ከለላ ዋሻ ሆኖ የፈጸመውን ስሕተት ይቅር ብሎለት እስከአሁንም ድረስ ከጎኑ ተሰልፎ በጋራ ጠላታችን በወያኔ ላይ እንዲነሣና ሀገራችንን ከጥፋት ታድገን ሰላምና ዕኩልነት የሰፈነባት፣ የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት የተረጋገጠባት፣ ዲሞክራሲያዊት (መስፍነ ሕዝባዊት) የሆነች፣ ሁሉንም ዜጋ ዕኩል ተጠቃሚ የምታደርግ ሀገርን እንድንገነባ ቢጋብዝም የምን ሥጋ ከአልጋ ሲሉት ከመሬት!” ሆነና ነገሩ ግብዣው እንደምታዩት እስከዚህች ሰዓት ድረስ በትግሬ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ የትግሬ ሕዝብ ወያኔን የሚያጠፋ መቅሰፍት እኔንም ያጥፋ! ከወያኔ ጋር ልሙት!” ብሎ ወስኗል፡፡

እኛም እንግዲህ የትግሬን ሕዝብ በል እንዳልክ ይሁን! መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ!” ብለናል፡፡ በእርግጠኝነት የምንነግርህ ግን በቆፈሩት ጉድጓድ መግባት፣ በሰፈሩት ቁና መሰፈር፣ በፈረዱበት ፍርድ መፈረድ ነባራዊ ሐቅ ነውና፣ ያለ የነበረና የሚኖር እውነታ ነውና መጨረሻህ ይሄው ነው!!!

የእግዚአብሔር ቃልም ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል!” ገላ. 67 ይላልና እንዲህ እንደወንዝ ድንጋይ ልብህን ያደነደነው ስትዘራው የኖርከውን ሁሉ ያንኑ ሊያሳጭድህ ፈርዶብህ ነውና በል እንግዲህ ቀንህን ጠብቅ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com