በትግራይ የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ (ምንሊክ ሳልሳዊ )
በትግራይ ክልላዊ መስተዳደር በሕወሓት ካድሬዎች የሚመሩ በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መካሔዳቸውን ለመረጃ ኮም የደረሱ መርጃዎች ጠቁመዋል። ከተንቤን እስከ አድዋ ከመቀሌ እስከ ሑመራ ሰልፎች መካሄዳቸው ታውቋል።ሰልፎቹ የፌዴራል መንግስቱ በቅርቡ በዘራፊዎችና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ በተሳተፉ ባለስልጣናት ላይ የወሰደውን እርምጃ ለማውገዝ የተደረጉ ናቸው።
በሰልፎቹ ላይ የመንግስት ሚዲያዎችን ጨምሮ የግል ሚዲያዎች የተወገዙ ሲሆኑ በቅርቡ በቁጥጥር ስር የዋሉ በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የታሰሩ የሕወሓት ሰዎችን በመደገፍ ፌዴራል መንግስቱ እንዲፈታ የሚጠይቁ መፈክሮች ተሰምተዋል። እንዲሁም የሕወሓት መሪ ዶክተር ደብረጺሆን በቅርቡ አስሩ ትግራይን ለማዳከም ነው ብለስ የሰጡትን መግለጫ በመንተራስ በሕወሃት ዘራፊዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ ዘርን ተገን ያደረገ ነው በማለ ፌዴራል መንግስቱን ሰልፈኞቹ ወቅሰውታል።
ሰልፉን ታዝበናል የሚሉ የትግራይ ተወላጆች በሰጡት አስተያየት ሰልፉ ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ጉያ ለመወሸቅ የምታደርገው ሩጫ ነው ካሉ በኋላ ይሄ ሰልፍ ዘራፊን የመደገፍ ሰልፍ ነው፣ይሄ ሰልፍ የሰብዐዊ መብት ጥሰትን የመደገፍ ሰልፍ ነው ፤ ይሄ ሰልፍ ግብረሰዶማዊነትን የመደገፍ ሰልፍ ነው ፤ይሄ ሰልፍ ሀገር ያፈረሱትን የመደገፍ ሰልፍ ነው ብለዋል።
ሕወሓት በዘረፈው ገንዘብ ገና ብዙ ወንጀሎችን በመፈጸም ሀገሪቷን ቅርቃር ውስጥ ሳይከታት በፊት መንግስት ከዓለምአቀፉ ማህብረሰብ ጋር በመሆን ሴራውን ቀድሞ ማክሸፍ አለበት ብለዋል።(ምንሊክ ሳልሳዊ )