የሸገር ኤፍ ኤም ዘገባ
በሃገራችን የተለያዩ ክፍሎች የሚደርሰን ወሬ የግጭትና የሁከት እየሆነ ነው፡፡ በየአካባቢው ዘርን በለየ ግጭት ዜጎች እየሞቱ ነው፤ ንብረት እየጠፋ ነው፤ ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ ነው፡፡
ይህ ሁከት መሻሻል ሳያሳይ ከዩኒቨርስቲዎች የሚሰማው ወሬ ተመሳሳይ እየሆነ አሳዛኝ ሆኗል፡፡ የእውቀት ምንጭ በሆኑት ዩኒቨርስቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች፣ የተሻለ አስተሳሰብ ኖሯቸው የሃገርና የህዝብን እድገት ያስገኛሉ ተብሎ ሲታመንባቸው እዚያው የጎሳ ቅራኔ ውስጥ ይዘፈቃሉ ?
ግን በአንድ ሃገር ተዛምዶና ተወዳጅቶ የኖረ ህዝብ፣ ድንገት ወንዝ በማይለየው የትውልድ ሐረግ ልዩነት እንዴት በጥላቻ ተዘፈቀ ? ኧረ ምን ቢሆን ነው እንደሰው እንደአብሮ ነዋሪ እንኳ ለመተያየት የሚጠላላው ? በዚህ ጉዳይ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰጣሉ፡፡
ንጋቱ ረጋሣ ከክልል አወቃቀር ሥርዓት አኳያስ የሚሰጠውን አስተያየት ተከታትሏል…