ሰሞኑን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ችግር በርካታ ተማሪዎች ተጎድተዋል። የአማራ ተማሪዎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት በአሶሳ ብቻ ሳይሆን በሀሮማያም ተከስቶ ነበር። በጎንደር ተመሳሳይ ችግር ተፈጥሮ የነበር ሲሆን ተረጋግቷል። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሁኔታውን ተቃውመው በመውጣት ድንቅ ስራ ሰርተዋል።

በዛሬው ዕለት አሶሳ ላይ የታየው የአማራና ኦሮሞ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ሕዝቡም ላይ ግጭት ለመፍጠር እየተሰራ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ገሬ ወዲ ሴሮ የተባለ የትህነግ/ህወሓት ሰው በሀሰት መታወቂያ ግጭት ሲያስነሳ እንደነበር እየተነገረ ነው።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በትህነግ/ህወሓት ሴራ ውስጥ ተጠልፈው በሌላው ላይ ጥቃት ከማድረስ መቆጠብ አለባቸው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደመሆናቸው የትህነግ/ህወሓት ሴራ ይጠፋቸዋል አይባልም። መጠቀሚያ ከመሆን አልፈው የሚለኩሱት እሳት የት እንደሚደርስ ይጠፋቸዋል አይባልም። የትህነግ/ህወሓት ሰዎች የሚከፍሏቸውም ይሁኑ አጀንዳ የሚጋሩ ጥቂት ተማሪዎች ኢላማ ያደረጉት ላይ ድንጋይና ዱላ አንስቶ ከመዝመት በፊት ሁሌም የትህነግን ሴራ ሊያስታውሱ ይገባል። ይህን ማስታወሱ ብቻ ግን በቂ አይደለም።
በየ ዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች ወኪሎቻቸውን መርጠው የጋራ ኮሚቴ ማዋቀር አለባቸው። ሁለቱን ለማጋጨት የሚገልጉት ሴራ ጠንስሰው ሲመጡ ድንጋይና ዱላ ይዞ በሴራው ውስጥ ሰተት ብሎ ከመግባትና እሳት ከመለኮስ በፊት ጉዳዩን በማጣራትና በመነጋገር የትህነግም ሆነ አጀንዳውን የሚጋሩት ሴራ ማክሸፍ ይገባል።
ትህነግ/ህወሓትም ሆነ ሁለቱን ሕዝብ በማጋጨት የፖለቲካ ጥቅም ማግኘት የሚፈልግ አካል መጠቀሚያ መሆን ማብቃት አለበት። በሀሰት መታወቂያ ሕዝብና ሕዝብን ለማጋጨት ስራዬ ብሎ የያዘ አካልን ሴራ ውስጥ ገብቶ ንፁሃን እንዲቀጠፉ፣ እንዲቆስሉና በሕዝብ መካከል ጥል እንዲፈጠር መጠቀሚያ ከመሆን መቆጠብ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ አስልቶና አውርቶ የሚፈታው ችግር ነው።