የዛሬው የክልል አንድ ሰልፍ ህወሀትን ይታደጋልን? የወልቃይት ጠገዴና ራያና ትግል ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል?

በዛሬው እለት በተለያየ የክልል አንድ ክፍሎች ውስጥ ተደረገ በተባለው ሰልፍ ላይ ሁለት ጉዳዮችን ማቅረብ እፈልጋለሁ

በመላ ኢትዮጵያ ለ27 አመት ህወሀት መራሹ መንግስት በጉልበት ባመስፈራራትና በጎቦ ሰልፍ እያሰወጣ “ድግፍ አለኝ” ሲል እንደኖረና የህዝቡን ትግል በሰልፍ ፖሮፓጋንዳ ለማፈን ሲጥር እንደነበረ ሁላችንም እናውቃለን። አበል እየተከፈለው ሰልፍ ስለወጣው ህዝብ ሁላችንም ሰምተናል።

ያ ሁሉ ግር ግር ግን ገዥወችን ጊዜያዊ እፎይታ ከመስጠት የዘለለ ያሰገኘው ውጤት እንደሌለ መታወስ አለበት ።አሁንም ቢሆን ተመሳሳይ እርምጃን በመውሰድ አዲስ ውጤት አገኛለሁ ብሎ መጠበቅ ብዙም ፈቀቅ የሚያደርግ አይመስለንም።

ባለፈው ሰሞን በሰብአዊ መብት ጥሰትና በዝርፊያ የታሰሩት አብዛኛው የህወሀት አባላት ለመሆናቸው ግልጽ ነው። የትግራይ ህዝብ የመብት ረገጣውም ሆነ የዝርፊያው አንዱ ሰለባ እንደሆነ ይታወቀል። ስለዚህም ብዙሀኑ የትግራይ ህዝብ መብት ረጋጮችንና ዘራፊወችን ይደግፋል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።

የፖለቲካ ሂሳቡም ሆነ ተጽእኖው ቀደም ባሉት ጊዜወች ሁሉ ሕወሀት ያካሂዳቸው ከነበሩት ሰልፎች የተለየ አይደለም። ህወሀትን ለመታደግ እንኻንስ ሰልፍ ሌላ ሌላም የያዋጣም ።

ህወሀትን ለመታደግ ከተፈለገ ራሱ ድርጅቱ ማስተካካል ያለበት እጅግ ብዙ ጉዻዮች አሉ። በኔ እይታ የህወሀት ነቅዟል። ካሁን በኻላ ህወሀትን በስልፍ መታደግ አይቻልም። የትግራይ ህዝብም ሆነ የህወሀት ደጋፊወች ድህረ ህወሀት ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚያሰችላቸውን ሌሎች የፖለቲካ አማራጭችን መቃኘት ማተኮር የሚገባቸው ጊዜ አሁን ነው።

ሌላው ጉዳይ በትግራይ ውስጥ በወልቃይት ጠገዴና በራያ ውስጥ የሚታየው ተቃቅሞ በየቦታው ሰልፍ በማሰለፍና በማውገዝ ሊፈታ እንደማይችል መገንዘብ ያሰፈልጋል።

ያካባቢወቹ (የወልቃይትና ራያ) ህዝብ የሚለው ማንናታችን ተረግጦ በግድ ሌላ ማንንት ተጭኖብናል ነው። የኛ ድምጽ አልተሰማም ፣ ታፋኗል፣ ተረግጠናል፣ ስለዚህም መብታችንን ለማስከበር ማንነታችንን ለማስከበር ትግል እያደረግን ነው ነው።

ዛሬ የተደረገው ሰልፍ ለወልቃይት ጠገዴና ራያ ህዝብ “መብታችሁን እናከብራልን” “ ብሶታችሁን እነገነዘባለን፣ መፍትሄ ለመፈለግም ዝግጁ ነን” የሚል ሳይሆን፣ ለትግላቸው እውቅና ያልሰጠ ፣ ስለ ብሶታቸው አንድም ቃል ያልተነገረበት ነው። ታዲያ ይህ እንዴት የራያንና የወልቃይትን ችግር ይፈታል?።የራያና የወልቃይት ተወላጅ ይህን ሲመለከት ምን የስማዋል ?

በኔ አመለካከት የዛሬው ሰልፍ የወልቃይትንም ሆነ የራያን ህዝብ የሚያሰቆጣና የተጀመረውን ትግል እጅግ የሚያጠናክረው ይመስለኛል።

ህወሀት በፕሮፓጋንዳ ስራው ውጤት ሲያጣ የሚፈልገውን በጉልበት ለማግኘት የመሞከር ታሪክ ስላለው ፣ አሁንም የክልል አንድን ሰልፉ ተከትሎ ውጤት እንዳላገኘ ሲገነዘብ ምን የሀይል እርምጃ ይወስድ ይሆን የሚለው ሁላችንንም ሊያሳስበን የሚገባና የምናየው ይሆናል።