ለጣና ሀይቅ ሁለት ማሽን ተገዛ
ዓለማቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማህበር ሲያካሂድ የነበረውን ጥናት በማጠናቀቅ ሁለት ከፍተኛ አረም ማጨድ የሚያስችሉ ማሽኖች ከነሙሉ መለዋወጫቸው ግዥ ፈጸመ።
$359,490 የአሜሪካን ዶላር (ወይም 10 ሚሊዮን ብር) ወጭ የተደረገባቸው እነዚህ ሁለት H-9 905 የተባሉ ከፍተኛ የአረም ማጨጃ ማሽኖች እያንዳንዳቸው 75 የፈረስ ጉልበት ያላቸው ሲሆን በአንዴ 26.2 ሜትሪክ ኪዩብ አረም ማጨድ የሚያስችሉ ናቸው። ይህም ከዚህ በፊት ከገዛነው ማሽን ጋር ሲነጻጸር በአምስት እጥፍ አረም የመሸከም አቅም ያለው ነው።
ለዚህ ግዥ የሚሆነውም ገንዘብ የተሰባሰበው በዲሲ፤ ዳላስ፤ ቺካጎና ለንደን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ነው። በተጨማሪም ዋሺንግተን ዲሲ የምትገኘው የኢት/ኦ/ተ/ ደብረገነት መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን $70፣000 ዶላር ለዚሁ ተግባር አበርክታለች። ይህ ይሆን ዘንድ ገንዘባችሁን፤ ጉልበታችሁን፤ ጊዜያችሁንና ዕውቀታችሁን ለጣና ድጋፍ ያደረጋችሁ በሙሉ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው። በህብረት በመቆማችን ይህን ታላቅ ስራ ጣናን ለመታደግ መስራት አስችሎናል።
Global Coalition for Lake Tana Restoration