የጉራጌ ዞን የክልልነት ጥያቄ አቀረበ
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና Ethiothinkthank ጦማሪ Daniel Mekonnen በፌስቡክ ገፁ ላይ እንደገለፀው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የጉራጌ የክልል ጥያቄን ተቀብሎ ማፅደቁን አስታውቋል፡፡
በደቡብ ክልል ከሚገኙ ዞኖች ውስጥ የሲዳማ ዞን፣ ወላይታ ዞን፣ ከፋ ዞን እና ሃዲያ ዞን የክልልነት ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወቃል፡፡ በዚህ መሠረት በደቡብ ክልል የክልልነት ጥያቄ ቀረቡት ዞኖች አምስት ደርሷል፡፡