አቶ ቢተው በላይ በድብቅ ወደ አፋር ሰመራ መጥተው ከአብዴፓ አመራሮች ጋር መክሯል።
የአፋር ክልል ጉዳይ አሁንም አደገኛ እየሆነ መሆኑ ተዘገበ፣ህወሃቶች በቀጥታ እጅ እያስገቡ ነው።
የአፋር ክልልን የሚመራው የአብዴፓ ፓርቲ በውስጡ በተፈጠረው ሽኩቻ ምክንያት ለሁለት ተከፍሎ በጠቅላይ ሚንስትሩ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ግምገማ ካደረጉ በኃላ ነባር አመራሮች ወርደው ስልጣናቸውን ለአዳድስ ምሁራን ወጣቶች እንደሚያስረከቡ መስማማታቸው ይታወሳል።
ይሁን እንጂ አሁንም የፓርቲው ሊቀመንበር እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት ሀጂ ስዩም በቀጣዩ ጉባኤ ላይ ሌጋሲያቸውን ለማስቀጠል በሚያስችላቸው መንገድ በጎሳና በቤተሰብ ስልጣናቸውን ለማውረስ እያዘጋጁ በመሆኑ ምክንያት በየቦታው ህዝብን አስቆጥቷል።
ህወሀት እንደ ጓሮ አትክልት የሚያየው የአፋር ክልል ላይ ታማኝ አገልጋዮቹን እንዳያጣ ከፍተኛ ትግል ዉስጥ ይገኛል።
ትናንት ከመቀሌ በድብቅ ወደ ሰመራ የመጡት የህወሓት አመራ የሆኑት አቶ ቢተው በላይ ከዶ/ር አብይ በተቀራኒ የአብዴፓ ፓርቲን ለመሸምገል ወይም ለመደለል ሞክሯል።
አቶ ኢስማኢል አሊ ሲሮን፣ ሀጂ ስዩምንና አቶ አሊ አብደላን ያነጋገሩት አቶ ቢተው በላይ የዶ/ር አብይ መንግስት አይዘልቅም፣ የዶ/ር አብይን ምክር ሰምታችሁ መታለል የለባችሁም፣ እኛ ከሃያ ሰባት አመታት በፊት እናንተን የሾምናችሁና እስካሁንም እንድትቀጥሉ ያደርግናችሁ እንደዚህ በቀላሉ እጅ እንድትስጡ አይደለም በማለት ለማሳመን ሞክሯል።
አቶ ቢተው በላይ የዶ/ር አብይ መንግስት አይዘልቅም፣ የዶ/ር አብይን ምተው በላይ የዶ/ር አብይ መንግስት አይዘልቅም፣ የዶ/ር አብይን ምተው በላይ የዶ/ር አብይ መንግስት አይዘልቅም፣ የዶ/ር አብይን ምተው በላይ ከዚህ በተጨማሪም እንዳሉት እኛ እንኳን አፋር ክልል ይቅርና በኦሮሚያም ጭምር ብዙ ለውጥን ለመቀልበስ የሚስችለን አቅም አሁንም አለን፣ ሰለዚህ እናንተ በአንድነት እስከ መጨረሻ ከህወሀት ጎን መቆም አለባችሁ በማለት ለአብዴፓ አመራሮች መናገራቸው ከታማኝ ምንጭ አረጋግጠናል።
አቶ ቢተው በላይ ይህን ካደረጉ በኃላ ብዙ ሳይቆዩ ወደመጡበት መቀሌ ተመልሰው ማደራቸው ነው የተነገረ።
ቢተው በላይ ማለት አሁን አብደፓ የሚባለው ፓርቲ በ1992ዓ.ም ከተለየያዩ ፓርቲዎች ተዋህዶ ወደ አንድ ፓርቲ እንዲመጣ በተደረገው ህደት ዋና መስራች የነበረው። የነበሩ፣ በኃላም ከህወሀት ጋር እየታገል ከጫካ የመጠውን የአዴ ፓርቲ ብቻ ክልሉን እንዲቆጣጠር ያደረጉ ሰው ናቸው።