እኔ ከመጀሪያውም ነገሩን እረዳው ነበር ግን ብዙዎች ብዙም ትኩረት የሰሰጡት አልመሰለኘም፡፡ አሁን በግልጽ እየታየ ነው፡፡ ወያኔ ትልቅ ጉልበት ያላት ትግራይ ውስጥ ሳይሆን ኦሮነሚያ ውስጥ ነው!!!

የወያኔ ዘመን እንደሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ምን አልባትም ከሌሎችም በከፋ ሁኔታ ግፍ ተቀባይ ኦሮሞ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡የወያኔ የማሰቃያና ማጎሪያ ቤቶች ቋንቋ ኦሮምኛ ነው እስከሚባል ድረስ ከምናውቀው ሌላ ብዙዎች ከሚኖሩበት ቄዬ በጅምላ ተገድለዋል ተፈናቅለዋል እስከአሁንም ወደ ቦታቸው አልተመለሱም፡፡ ብዙ አሳቃቂ ግፎችን ጆሮአችን ሰምቷል፡፡ አይናችን አይቷል፡፡

እነዚያ አስከፊ ጊዜያቶች አልፈው ዛሬ ብዙ ተስፋ ሲታሰብ ይሄው ሰው ከራሱ ተጣልቶ ይገኛል፡፡ ሁሉም ጋር ችግር አለ፡፡ ሆኖም እየቆየ ነገሩ ገብቶት እየተስተካከለ ነው፡፡ በአለፉት 27 ዓመታት እውነቱን እንነጋገር ከተባለ እንደ ኦሮሞ፣ ሱማሌ፣ አማራና ጋምቤላ የተዘመተበት ሕዝብ የለም፡፡ እነዚህ በአንድ ላይ ቢደመሩ የአገሪቱን 80 በመቱ ይሆናሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ እጅግ አሰቃቂ ግፎችን ለፎሮአችን እየሰቀጠጠን እየሰማን ነው፡፡ ከላይ ከጠቀስኳቸው ግን እንደ አሮሞ መጠቀሚያ የሆነ የለም፡፡ ለ27ዓመቱ የግፍ ዘመን ለግፍ አድራጊዎቹ ትልቁ ጉልበት የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ ነበር! ምክነያቱ ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊ ማንነት አወርደውት እንደፈለጋቸው ለሚፈልጉት ዓላማ መጠቀም መቻላቸውና ከሌሎች ጋር በተለይም ከአማራ ጋር ጠላት እንዲሆን ማድረግ መቻላቸው ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ የሆኑት በሴረኞች ወሬ ስለተፈታ ነው፡፡ ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይባላል፡፡ ይህ ነገር እጅግ ይገርማል፡፡ 27 ዓመት አልፎም ያ ሁሉ ሆኖም አሁንም በዛው ስልት መጠቀሚያ ሲሆን ያሳዝናል፡፡ እንግዲህ ይሄ አዚም ነው! ኦሮሞን በባርነት የያዙት ግን ትግሬ ወያኔ እንዳይመስሏችሁ፡፡ ኦሮሞ ወያኔዎች(ኦነጋውያን) እንጂ፡፡ ከጅምሩ እንዲሀ አረጉት

  1. ከሐበሻ ቅኝ ግዛት እናወጣሀለን ከሚኒሊክ ጀምሮ ሲገዛሕ ከነበረው ሐበሻ አሉት፡፡ ሐበሻ ማን ነው? ለማለት ጊዜ አላገኝም ይህ ዘመቻ የተደረገው በዋናነት የተማርን ኦሮሞ ነን በሚሉ ስለሆነ ያውቃሉ በሚል ተቀበላቸው፡፡ ሐበሻ ከሚለው የኢትዮጵያዊ ጎራ ኦሮሞ ወጣ ሌሎችንም አስወጣ፡፡ ከዛ ይሄው ኦሮሞን የሚነግድበት ኦሮሞ ነኝ የሚለው የተማረውና ብልጣብልጡ ሐበሽነትን ከሰጣቸው አንዱ ትግሬ ከወጡ የሕዝብ ጠላቶች ጋር አብሮ ኦሮሞን እየገበረ ሌላውንም እያስገደለ ኑሮውን መሠረተ፡፡ ኦነጋውያን መሪዎች በቦሌ ወደሚፈልጉበት አውሮፓና አሜሪካ አገራት በልዩ ፓስፖርት ሲሸኙ ኦሮሞ ሁሉ ኦነግ ነህ እየተባለ ታረደ፡፡ ብዙ ግፍ አሳለፈ 27 ዓመት፡፡
  2. ከኢትዮጵያ አውጥተው በገዛ አገሩ ኦሮሚያ ብለው በሰየሙት ምናባዊ አገር ስደተኛ አረጉት፡፡ ከዚያ ብዙ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊቱን ካደ፡፡ በሚሄድባቸው አገራት ሁሉ ከየት ነህ ሲባል ከኦሮሚያ ማለት ጀመረ፡፡ ኦሮሚያ የት ነው ያለው ሲሉት ምስራቅ አፍሪካ ምናምን ብሎ በራሱ ጊዜ መባዘን ጀመረ፡፡ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ብዙ ኦሮሞን ያስደነብረዋል! ኢትዮጵያ! ይገርማል ይህችን አገር የገነቧት እነማን እንደሆኑ እኮ በጆሮው እየሰማ ነው፡፡ የአባቶቹን አገር ካደ! እርግማን ይልሀል ይሄ ነው! ኢትዮጵያን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ብዙ ሞከረ፡፡ ሌላው ቀርቶ ከጅምሩ በታላቁ መጻፍ ቅዱስ በማያሻማ ሁኔታ የተገለጸችውን የሐበሾችን ምድር ኢትዮጵያን የኩሽ በሚል ሊያስተካ ብዙ ሞከረ፡፡ ይህ ሙከራ ከሌሎች ጋር በመሆን ኦሮሞ ነን የሚሉ ያደረጉት ነው፡፡ ኩሽ የካም ልጅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ግን የጊዮን (አባይ) ወንዞች (ገባሮቹን ጨምሮ) የሚፈሱባት የሐበሾች ምድር ናት፡፡ አልተሳሳተም ታላቁ ነብይ ኤርሚያስ ኢትዮጵየዊ መልኩነን(አበበ መልኩን) ነብር ዥንጉርጉርነቱን አለለት፡፡ ይሄ ሁሉ መዝገብ ያለትን አገር ከደ አገር አልባ ሆነ!
  3. የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ አለው አለው አሉት፡፡ ሲጀምር ምን አልባት የአገዛዝ በድል ስለአለ ከጭቆና ነጻ የመውጣት ነው ብሎ ሊታሰብ ይችላል፡፡ ነገሩ እንደዛ አደለም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ምንድነው ብላችሁ ብትጠይቁ መልስ የምታገኙለት አይመስለኝም፡፡ ጥያቄው ከዘረኝነትና ጥላቻ የሚነሳ ስለሆነም በግልጽ ለመናገር ይከብዳል፡፡ ይህ የሕዝብ ጥያቄ ሆኖ ሳይሆን ሴረኞቹ እስካሁንም ሕዝብን ለማወናበድ የሚጠቀሙበት ነው፡፡ እንግዲህ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ እየተባለ ትልቅ የሴረኞች መሳሪያ የሆነው ኦሮሚያን ከን ኦሮሞቲ ሌላው በሙሉ ከኦሮሚያ ይውጣ ነው፡፡ ልብ በሉ ከላይ እንደጠቆምኩት ነው! አገሩ የኦሮሞ አደለም!!! ኦሮሞያ የሚባል የቅዠት ምድር ያቆናጸፉጽ የወያኔና-ኦነግ ጥምር ቡድን ነው! ይህ ጥምር ቡድን ነው እስከዛሬም በተለይ ኦሮሞን መሣሪያ አድርጎ ኦሮሞንም ሌላውንም የሚጫወትበት፡፡ በዚህ ጥያቄው መቼም ነጻ ላይወጣ ነው!!
  4. ኢትዮጵያና ሐበሻ አደለህም በሚል የኢትዮጵያ የሆነውን ሁሉ አስጣሉት፡፡ የሐበሻ ፊደል፣ ሐበሻ አቆጣጠር(ተጀምሮ ነበር) በአጠቃላይ ከኢትዮጵያዊነት ለመራቅ የሚያስችላቸውን ሁሉ፡፡ የሐበሻ የተባለው ግዕዝ በሙሉዕነት ምድር ላይ አሉ ከሚባሉት ፊተላት ሁሉ ብልጫ ቢኖረውም የላቲን ፊደል የኦሮሞም፣ ሌሎች ኩሽ የተባሉ (የሚባል ነገር የለም) ፊደላቸው አደረጉ፡፡ ላቲንን ለኦሮምኛም ሆነ ለሌሎች ለማሰማማት የተደረገውን ያህል ግዕዝ ላይ ቢሰራ የወፍ ቋንቋም ለመጻፍ ባስቻለ ነበር፡፡ ግዕዝ ለኦሮምኛ አይመችም ለሚሉ እስኪ ኦሮምኛ ከግዕዝና ከላቲን ለማ እንደሚቀርብ የቋንቋ ምሁራን ይጠየቁ፡፡ ምን አልባትም በአጋዝያን ዘመን(ግዕዝ ተናጋሪዎች) ሁሉም አንድ ነበሩ፡፡ ሥያሜያቸውም አፍሮ ኤሺያቲክ ነው፡፡ እነዚህ ከሌላው አፍሪካ የሚለዩ ናቸው፡፡ ግዕዝ ከእነዚህ ምድብ ነው! በኋላ የመጡትን ተውት፡፡

ሌሎች ብዙ በርካታ ነገሮች ተደረጉ ብዙ ኦሮሞን በአመለካከት የቅኝ ተገዥ፣ አገር አልባ፣ ታሪክ አልባ አደረጉት! ዛሬ ያን ሁሉ ግፍ አድርሰውበት እንኳን ኦሮሞን እንደፈለጉት ለመጠቀም አልከበዳቸውም፡፡ ኦሮሞ አገር አልባ፣ ቅጭ ተገዥ፣ ሌላም የሆነው በአመለካከት እንጂ እውን በሆነ ታሪክ አደለም! ቅኝ ተገዝቻለሁ ብሎ ያመነን ታሪኩ ግልጽ ሆኖ እያለ በምን ያድኑታል! ኢትዮጵያ አገሬ አደለችም ብሎ ከአመነ እውነቱን እያወቀው ከካደ በምን ያድኑታል፡፡ ይሄን ማዳን ይከብዳል፡፡ ኢትዮጵያዊነታቸውንና ታሪካቸውን የጠበቁ ኦሮሞዎች ቦታውን ሙሉ በሙሉ ተክተው ከአልያዙት ከባድ ነው፡፡ ማንም ሕዝብ ዛሬ ላይ ቢጠየቅ እንዲህ ብሎ አያስብም፡፡ ምሁሮቻቸውም ግንዛቤ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት እየደረጉ ነው፡፡ በኦሮሞ በኩል ያለው ግን የሴረኞቹ ተባባሪው ቡድን ኃይል ስለሚያይል የተደረገው ጥረት ሁሉ እዛው ታጥቦ ጭቃ እየሆነ ነው፡፡ ዛሬ መቀሌ ላይ የምናየው ነገር ከምን ድፍረት እደመጣ ሁሉም ያስተውል፡፡ ኦሮሞ ሲደመር ትግሬ እኩል ይሆናል ኢትዮጵያ! እዛ ላይ ስላቁ ራሳቸውን ትግሬ ብለው መፈክሩን የያዙት በራሱ ትግሬ ሳይሆኑ ወያኔ ናቸው! የለበሱትም ዓርማ የወያኔን ነው፡፡ ወያኔ ከትግራይ መቄሌን ዋና ግዛቱ ስላደረገ መቀሌ የግል ንብረቱ ነው፡፡ ግን ተንቤን ቢሄድ ምን እንደሚል ሕዝብ እናውቃለን! እና ኦሮሞም ትግሬም የተባሉት ሁሉቱም ወያኔዎች እንጂ ኦሮሞም የኦሮሞን ሕዝብ አደለም! ትግሬም የትግሬን ሕዝብ አደለም! ወያኔዎቹ የሕወሐት-ኦነግ ጥምር ቡድን እንዲህ የሕዝብን ሥም በመጠቀም ይሳለቁብናል፡፡ ይሄን ሁሉ ድፍረት ያገኙት የኦሮሞን ሥነልቦና በሚፈልጉት መልኩ እንዳዘጋጁት ስለሚያምኑ ነው! አዝናለሁ! እውነት ግን አደለም! ብዙ ስነልቦናው የተወሰደ ቢኖርም ይበልጠው አደለም! የወያኔ-ኦነግ ጥምር ቡድን ብዙ ሴራ እያሴረ ነው፡፡ ሰሞኑን የቅማንትና አማራ ጉዳይ ዋና አቀንቃኝ የኦሮሞ ሚዲያ ነን የሚሉት ሆነዋል! አማራ ላይ የሆነ ነገር ደረሰ ሲባ ከወያኔ ይልቅ እጅግ የሚፈነጥዙት እነዚሁ የኦሮሞ ነን የሚሉት ናቸው! ጥልቁ ስጋታቸው የኦሮሞና-አማራ ጥምረት ነው! እነ ለማ በመፈጠሩት የእነዚህ ሁለት ሕዝብ ጥምረት ምን ያህል ስኬት በምን ያህል ፍጥነት እንዳመጣ አይተዋል፡፡ አሁን አሮሞን ውዥንበር ውስጥ ከተው ወደኋላ መመለስ ባይችሉ ሁሉምን ነገር አልቆ ዛሬ እያዳንዳቸው ቂሊንጦ በተገኙ ነበር!

አዝናለሁ! ሰሞኑን የቀድሞው አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ውስጣችንን ስላወቁ ነው እንደፈለጋቸው የሚዘውሩን የሚል መልክት አስተላልፈዋል፡፡ አያይዘውም አሁን ያለውን የኦሮሞን ፖለቲካ ከእግዚአብሔር ቁጣ እንዳያመጣ አስጠንቅቀዋል፡፡ ምክነያቱም ከ1 ዓመት በፊት የነበረውን አስታውሶ ተመስገን ዛሬ ላይ ያደረስከኝ ማለትን ሳይሆን ለጠላቶቹ በፍቃዱ የተገዛ መሆኑ ታዝበውና ነው! የዩኒቨርሲቲው ነገር የዚሁ ውጤት ነው!

አዝናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ