11/30/2018
ግልጽ ደብዳቢ ለመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ በያላችሁበት ወሰኔ ይፍሩ [ፕሮፌሰር]
የተከበራችሁ ወገኖቼ ሆይ
በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።
ክፍል አራት
ስለ ኢትዮጵያ ነፃ ምርጫ ለውይይት የቀረበ አጀንዳ
ክፍል ሶስት ላይ እንደተጠቀሰው በቅደም ተከተል ይቀርባል እንደተባለው ስለ ነፃ ምርጫ ቦርድ፣ ስለ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ስለ ጎሳ፣ ስለ የፖለቲካ ፓርቲ አመሰራረት፣ ስለ ነፃ ፍርድ ቤት በዚህ ክፍል ላይ በዝርዝር ይቀርባል። ሌላው እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው የምንለው ነገር ቢኖር ምርጫው በምን አይነት “ሁኔታ” ይካሄዳል በሚለው ጉዳይ ላይ ነው። ይህንን በተመለከተ በዚህ በመጨረሻው ውይይታችን ላይ በዝርዝር ይቀርባል፤ ይኸውም ዲያስፖራው ምን ሊረዳ እንደሚችል፤ የምርጫ ሳጥን [Eletronic Machine] ከተለያዩ አገሮች በእርዳታ የምናገኝበትን “ሁኔታ” ማመቻቸት፤ ሕዝብ የተስማማበት ከሶወስት ወይም ከአራት የማይበልጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በስምምነት የሚመሰረትበትን “ሁኔታ”፤ ለምሳሌ የገበሪዎች፤ የወጣቶች፤ የሴቶች፤ የሰራተኞች፤ ሕዝቡ በየቀበሌው፤ በየወረዳው፤ እንዴት ተደራጅቶ የምክር ቤቱን አባል እንዴት እንደሚመርጥ [A blue print and a road map for genuine democracy] እነዚህን ሁሉ ለማከናወን የሚወስደው ግዜ ተሰልቶ እንዲስተካከል ማሳሰብ፤ የምርጫው ቦርድ በምን አይነት “ሁኔታ” እንደሚመሰረት፤ ነፃ ፍርድ ቤት በሕገ መንግሥቱ ተደንግጎ ስራ ላይ እንዲውል ማድረግና ወንጀለኞች ወደ ፍርድ የሚቀርቡበት፣ የተዘረፉትና ወደ አንድ ክልል ቦታ ተወሰደው የተከማቹት የእንዱስትሪ ማምረቻዎች የሚመለሱበት “ሁኔታ” ማመቻቸት፤ በሕገ ወጥ መንገድ ተዘርፈው በውጭ አገር ባንኮች የተቀመጡ ገንዘብ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት አማካይነት የሚመለሱበትን “ሁኔታ” መወያየት አስፈላጊ ነው። እነዚህ ሁሉ በቅጡ ተጠንቶ በዚህ ክፍል ላይ ይቀርባል። ግን እዚህ ላይ በጥንቃቄ ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያለብን የለውጡን ሂደት ለማሰናከል ወይም ደግሞ በመደመር መልክ እንደገና የለውጡ ደጋፊዎች ነን በማለት ወደስልጣን ለመመለስ የሚያደርጉትን ጥረት አጥብቀን መከላከል ይኖርብናል። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕደግ)ን ጠግነው ቢመለሱ የሚያመጣው የተለመድውን እልቂት እንጂ ለውጥን አይደለም። የ27 ዓመቱ አብዮትዌ ዲሞክራሲ፤ የብሒር ክልል መንግሥት፤ የብሒር ብሒረሰቦች እኩልነት ያመጣው አብዮታዌ ግርግርን ነው፤ የክልል ፌደራሊዝም ያመጣው ዘር ማጥፋትን፤ መፈናቀልንና ዝርፌያን ነው፤ ወያኔ አሁን የሚጮኸው በግርግር የሚሰርቀውንና የሚዘርፈውን ሃብት ስለቆመበት ነው። ሊያቀው የሚገባ ነገር ቢኖር ሁለተኛ የማሰር፤ የመግደል፤ ዘር የማጥፋት፤ በሕገ ወጥ መንገድ በቢሊዮን የሚቆጠር የአገር ሃብት ወደ ውጭ ማሸሽ ያለመቻሉን ነው፤ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት ይጠየቃል፤ [Money Laundering, Illicit funds and Stolen Money , according to US Department of Justice and FBI is illegal; public corruption, no matter where it occurs, is a threat to a fair and competitive global economy. The FBI is committed to working with foreign and domestic partners to identify and return these stolen assets to their legitimate owners]. በቻይና፤ በሲንጋፎር፤ በመካከለኛው ምስራቅ፤ በካናዳ ባንኮች ውስጥ የተቀመጡ ገንዘብና ንብረቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት ማስመልሰ ግዲታ ስለሆነ አጥብቀን በስራ እንዲውል ማድረግ ነው። በተጨማሪ ወያኔ ለዉጡን ለማወናበድ ያልሆነ ታሪክ አለ እያለ የሚያወራዉን ፕሮፓጋንዳ ለሕዝብ ማሳወቅ ታሪካዌ ግዲታ ስለሆነ ጎሳ፤ ብሒር፤ የብሒር ብሒረሰብ እኩልነት፤ አብዮታዌ ዲምክራሲ፤ ዲሞክራሲ ምን ማለት እንደሆነና ታሪካዌ ሂደታቸውን እያመሳከርን እንወያያለን፤ ነገር ግን የምርጫውን ሂደትና ሕገ መንግሥቱን ሕዝብ በየቀበሊው ውይይት ተደርጎ ስምምነት ላይ ሳይደርስ ወደ ምርጫ መሂድ ታጥቦ ጭቃ መሆኑን በቅድሚያ ማወቅ ይኖርብናል። መልካም ንባብ።
ለማንበብ ከዚህ ላይ ይጫኑ ===> ግልጽ ደብዳቢ ለመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ በያላችሁበት ክፍል አራት, pdf
—————
ክፍል ሶስት ለማንበብ ከዚህ ላይ ይጫኑ
ክፍል አንድ እና ሁለትን ለማንበብ ከዚህ ላይ ይጫኑ
