አሜሪካ የሚገኘው የብአዴን አመራሮች ጉብኝት አዘጋጅ ኮሚቴ (ደርግ) የብአዴን አመራሮች አሜሪካንን የሚጎበኙበትን ምክንያትና ታላሚ እድምተኛ (Target audience) ግልጽ እንዲያደርጉ ተጨቅጭቀው በግድ ሲመልሱ ከአማራ ክልል ተወላጆችና የክልሉ ሕዝብ ጉዳይ ያገባናል ከሚሉ አካላት ጋር በለውጡ፣ በልማትና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ለመምከር!” እንደሆነ ገልጸው ነበር፡፡

አቶ ንጉሡ ጥላሁን ደግሞ ከዚህ ራቅ አደረጉትና ምንአሉ

የጉዞው ዓላማ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአማራ ልማት ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል እና የክልሉ መንግሥት ለውጡን ተከትሎ ያለውን አቋም ውይይት በማድረግ በቀጣይ ሥራዎች ላይ አብሮ ለመሥራት ያለውን መልካም አጋጣሚ ለማሳወቅ ነው

ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ አሜሪካ ሲያቀኑ እንደገለፁት::

የአማራ ብሔራዊ ክልል ልዑካን ቡድን ወደ አሜሪካ አቅንቷል :: ጉዞውም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸውያላቸውን አንድነት በማጠናከር ታላቅነቷን በጋራ ማስቀጠል ዓላማ የያዘ ነው ::

ቡድኑም በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ ሲሆን ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ አቶ ምግባሩ ከበደ እና አቶ መላኩ አለበል ተካተውበታል!” ሲል በፌስቡክ አካውንቱ (በመጽሐፈ ገጽ መዝገቡ) አስታውቋል፡፡

የብአዴን አመራሮች ጉብኝት ዓላማ ይሄ አቶ ንጉሡ የገለጹት ከሆነ ከጉዞው በፊት በቅድሚያ ራሱን ከክልል ፓርቲነት (የእምነተ አሥተዳደር ድርጅትነት) ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት መቀየር ነበረበት፡፡

ይሄንን ሳያደርግ ሀገር አቀፍ የሆነ ሥራን መሥራት አይችልም፡፡ የፌዴራሉ መንግሥት (የማዕከላዊው መንግሥት) ሕገመንግሥና የየክልሉ ሕገመንግሥት ይከለክለዋልና፡፡ ሀገር አቀፍ ፖለቲካዊ ሥራን መሥራት የሚችለው የፌዴራሉ (ማዕከላዊው) መንግሥት ነው፡፡ እሱም ቢሆን ብዙ ገደቦች አሉበት፡፡

የበድኑ ብአዴን አመራሮች ሕጋቸው በሚፈቅድላቸው፣ ማንዴታቸው (ኃላፊነታቸው) በሚያሠራቸው፣ ይዘናል የሚሉት ጎሳ ተኮር ርዕዮተዓለማቸው ወይም ፖለቲካዊ መርሖዋቸው በሚያዛቸው መሠረት በእነሱ አማርኛ የአማራ ክልል ተወላጆችን በልማትና በፖለቲካዊ (በእምነተ አሥተዳደራዊ) ጉዳዮች ለማነጋገር ነው የመጣነው!” እንዳይሉ ከአሁን በኋላ ከሕወሓት ዘበኝነትና ባርነት ነጻ ወጥተን፣ ተለውጠን ለክልሉ ሕዝብ ጥቅምና መብት ቆመናል!” ካሉም በኋላ ወያኔ የአማራን ሕዝብ ቀፍድዶ ለመያዝና የሚፈልገውን የጥፋት ዓላማ በአማራ ሕዝብ ላይ ለመፈጸም እንዲችል እራስን በራስ የማሥተዳደር መብትን ለአማራ ሕዝብ ነፍጎ ወይም ከልክሎ ወይም ሕጉን በመተላለፍ ከቀበሌ እስከ ክልል አሥተዳደር ድረስ የሰገሰጋቸውን ትግሮች ብአዴን አሁንም ተለውጨ ከወያኔ ባርነት ነጻ ወጥቸ ለአማራ ሕዝብ ቆሜያለለሁ!” ካለ በኋላም ይዞ በመቀጠሉ በዚህ የክህደት፣ የሸፍጥ፣ የቅጥረኝነትና የባንዳነት ተግባሩ ምክንያት ተለውጫለሁ!” የሚለው ነገር ሐሰት መሆኑን የአማራ ሕዝብ ማወቁን ብአዴን ስለሚያውቅ ከአማሮች ወይም ከአማራ ክልል ተወላጆች ጋር ስለ ለውጡ፣ ስለልማትና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ለመምከር ነው የመጣነው!” ለማለት የሞራል (የቅስም) ብቃት ስላጡ ነው ያለማንዴታቸው (ያለኃላፊነትታቸው) እና ያለመብታቸው እንደ ሀገር አቀፍ ፓርቲ “…ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለሀገራቸው ያላቸውን አንድነት በማጠናከር ታላቅነቷን በጋራ ለማስቀጠል!” ምንንትስ እያሉ የሚቀባጥሩት፡፡

አየ እነበድኖ ማጣፊያው አጠራቸው እኮ!!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com