
#በሰሜን_ወሎ_ጋዞ_እስታይሽ_ወረዳ የነዳጅ ክምችት እንዳለ ታውቆል።
“ነዳጅ ከክልላችን አይወጣም” በሚባልባት ኢትዮጵያ ” ከደጃፋችን አውጡና በጋራ እንልማ እያልን ሰሚ አጣን
እጅግ ለበርካታ ዘመናት #በዋድላ_ደላንታ አውራጃና በዋድላ ወረዳ በመቄት ወረዳ ይተዳደሩ ከነበሩት 8 ቀበሌዎች ጋር እስታይሽ ከተማን ማዕከል በማድረግ አንድ የተመቸ ወረዳ የመመስረት ዕድል ገጠማቸው፡ ጥቅምት 26 ቀን 2009 ዓ.ም ታሪካዊ የወንዙ ስያሜ #ጋዞ በመውሰድ የአዲሱ ወረዳ ስያሜ አድርጎ አጸደቀው፡፡ በአሁኑ ስዓት በሰሜን ወሎ ዞን ካሉት 11 የገጠር ወረዳዎች መካከል ጋዞ ወረዳ በሚል ስያሜ የሚጠራ በሰሜን የተከዜ እና በደቡብ የአባይ ተፋሰሶችን ያካተተ፣ በአቀማመጡ ምቹ፣ በባህሉና በወጉ ጨዋና ምስጉን ህዝብ የያዘ፣ በቅቤና ጮማ አምራችነቱ ምንጊዜም የማይነጥፍ ወረዳ ነው።
############
#ከአቶ_ገብረ_ህይወት_ሙላቱ የቀድሞው የመቄት ወረዳ አስተዳዳሪ ጋር በነዳጁ ዙሪያ #በላይ_በሁሉ ያደረገው ቃለምልልስ ይሄን ይመስላ
ጥያቄ:- እስታይሽ ከተማ ላይ ተገኘ ስለሚባለው የነዳጅ ማዕድን እርስዎ በጊዜው አስተዳዳሪ ስለነበሩ ያለወት እውቅና እስከምን ነበር ተገኝቷል የሚባለውስ እውነት ነው??
አቶ ገብረ ህይወት :- በ2008 መጨረሻ 2009ዓ.ም መጀመሪያ ከፌደራል የማዕድን ሚኒስቴር የተውጣጡ 1 አቶ መሰረት 2 አቶ ሶሪ የሚባሉ ሰዎች መጥተው በወረዳችን ነዳጅ ምልክት መገኘቱን እና በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉም እንዲሁ መገኘቱን ገለፁልን። ቀጥለውም እስታይሽ ላይ ያለው የነዳጅ መጠን የተሻለ ነው ከአስፖልቱ እስከ ነዳጁ የተገኘበት መሬት 1.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ብቻ ይገኛል። ለወደብም ቅርብ ነው በለው ጉጉታችንን አሳደጉት ከዛም #ሳልኮም ፔትሮሊየም ኩባንያ የሚባል ድርጅት ከአንድ አረብ ጋር መጥቶ ጥናቱን ጀመረ። ከኩባንያው ጋር አብረው facilitate ሲያደርጊ የነበሩት #abedellah የአባታቸውን ስም ረሳሁት እሳቸው ናቸው። ኢትዮጵያዊ ናቸው።
ከአረቡ ጋር እየተመላለሱ ፕሮጀክቱን ሲጎበኙ ነበር ዙሪያውን አጥር ለማጠር socioeconomic data ለመሰብሰብ process ላይ ነበሩ። የነዳጅ መቆፈሪያ ማሽኑ ከቻይና እተጓጓዘ እንደሆነ ሲነግሩንና በተስፋ ሲሞሉን ነበር።
ከዛም የመቄትና የዋድላ ወረዳ ደንበር ስለነበር የኔ ይገባኛል ጭቅጭቅ ሲነሳ እሱ ይቆይና ለአካባቢው የሚጠቅም ነገር በትምህርት በጤና በውሃ እንደግፋለን አሉን በትምህርት እንዲደግፉንና ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ እንዲሰራ ጠይቀን 2000000 ሁለት ሚሊዮን ብር ተበጅቶ 1.8 ሚሊዮን አክባቢ ብር በመቄት ወረዳ አካውንት ገቢ ተደርጎ ትምህርት ቤቱን አስገንብተዋል።
ጥያቄ:- ይሄ ሁሉ ነገር ሲደረግ የክልሉ መንግስት እውቅና ነበረው?
አቶ ገብረ ህይወት :- የክልሉ መንግስት እውቅና ይኑረው አይኑረው አላውቅም ግን የሰሜን ወሎ ዞን አመራሮች እውቅና ነበራቸው በወቅቱ አስተዳዳሪ የነበረው አቶ ፀጋ አራጌ ጉዳዮን ያውቁት ነበር ከሱም አልፎ የፌደራል የማዕድን ሚኒስቴር ያውቀዋል። አቶ ሶሪና መሰረት የሚባሉት ከፌደራል እየመጡም እያዮ የትምህርት ቤቱን ግንባታ እየተከታተሉ ገንዘቡን እነሱ ናቸው የሚለቁት በአካልም እንተዋወቃለን የኔ ግንኙነት ከዞኑና ከፌደራል ነበር ከክልሉ የጠየቀኝም የምገናኘውም ሰው አልነበረም። በድሮው የዞኑ ድርጅት ኃላፊ አሁን የወልድያ ዮንቨርስቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ይኸነው በላይ ጉዳዮን በደንብ ያውቁታል። ከዛ በኃላ እኔም ከኃላፊነት ለቀቅኩ ወረዳውም ለሁለት ተከፈለ ከዛ በኃላ ጉዳዩ ምን ላይ እንደደረሰ እውቅና የለኝም ያኔ ግን እጅግ በጣም ተስፋ ሰጭ የሆነ ነገር ሲነግሩን ነበረ እናም አሁን እናንተ ጉዳዩን ገፋ አድርጋችሁ ብትጠይቁ ለአገርም ለወገንም ጠቃሚ ነው።
#################
መረጃውን ስላደረሱን እናመሠግናለን ።
ምንም እንኳን የነዳጅ መገኜት በጣም ደስ የሚል ዜና ቢሆንም ነዳጁን የማውጣት ሂደት በጣም ፈታኝ ከፍተኛ ገንዘብ እና እውቀት የሚጠይቅ ቢሆንም የክልሉ መንግስት ይሄን ጉዳይ በመረዳት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ለሀገር እና ለወገን በሚጠቅም መልኩ የነዴጅ ክምችቱ አገልግሎት ላይ እንዲውል ጥሪያችንን እናሰማለን።
በአሁኑ ሰአት የሀገራችን ህዝብ ስራ አጥቶ ለስደት ሂወቱን አሳልፋ እየሰጠ በሚገኝበት ሰአት ገንዘብ ላይ ተኝቶ ገልዘብ ፍለጋ መከራ ማየት ማቆም ከለበት
“ነዳጅ ከክልላችን አይወጣም” በሚባልባት ኢትዮጵያ ” ከደጃፋችን አውጡና በጋራ እንልማ እያልን ሰሚ ጆሮ የለም እና በአስቸኳይ ወደ ተግባር ቢገባ መልካም ነው።
#ላኮመልዛው/ይርጋዓለም_ታደሠ
