አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ በአሜሪካን አገር ባደረጉት ከኢትዮጵያዉያን ጋር ባደረጉት ውይይት በርካታ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አስተናግደዋል። ጥያቄ አክቀረቡ ወገኖች መካከል የአንዲት ኢትዮጵያዊት ንግግርና አስተአይየት በአዳራሹ የነበሩትን ብዙዎች ያስለቀሰ ነበር።

የጀግናው ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ልጅ ናት።  አባቷ ደጃዝማች ተሰማ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ ዘጠኝ ጊዜ የቆሰሉ ጀግና እንደሆነ የገለጸችው ይች እህት ወንድሞቿ ላለፉት ሃያ አራት አመታት ታስረው የት እንዳሉ እንደማታወቅ፣ ሌላ ወንድሟ ከዚህ በፊት ሎስ ኦንጀለስ ዶ/ር አብይን ጠይቆ፣ “አብረን እናፈላልጋለን” የሚል መልስ እንደተሰጠው፣ በባህር ዳርም ጥያቄው ቀርቦ ለመደባበስ እንደተሞከረ ገለጻ፣ ወንድሞቿን በተመለከተ ፣ የት እንዳሉ፣ ሞተውም ከሆነ እዉነቱ እንዲነገርና ፍትህ እንዲኖር ጠይቃለች። የዚች እህት ወንድሞች ሚኒሊክ ተሰማ፣ ወንድወሰን ተሰማ፣ ዳን ኤል አጎናፍርና፣ አለማየሁ ተሰማ  ናቸው።

“ወንድሞቼ ብቻ አይደሉም፣ ከሁለት ሺህ በላይ ዜጎች የት እንዳሉ አይታወቅም፤ መቀሌ ጉድጓድ ዉስጥ ትልቅ እስር ቤት አለ ይባላል። ሞተው ከሆነ ንገሩን፣ እንወቀው። ቤተሰቡን ወክዬ፣ አማራዉን ወክዬ ነው የምናገረው። ፍትህ እንፈልጋለን። ” ብላ ጠይቃለች።