
በአዲስ አበባ ዜግች በከተማዋ አስተዳደር በግፍ እየተፈናቀሉ መሆኑ በስፋት እየተዘገበው ነው። የአዲስ አበባ ሕዝብ ሳይመርጣችው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ሳይሆንይ በኦሕዴድ/ኦዴፓ የተሾሙትና በምክትል ከንቲባነት ማ፤እረግ የከተማዋ ከንቲባ ሆነው እየሰሩ ያሉት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ የተሰሩ ናቸው በሚል ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ያፈናቀሉ ሲሆን ፣ ተፈናቃዮችም በአሁኑ ወቅት በቅዱስ ፋኑኤል ቤተክርስቲያን ሜዳ ላይ ፈሰው እንደሚገኙ ከስፋርው የደረሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ቤታቸው እንደሚፈርስ የተነገራቸው ነዋሪዎች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተነገራቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ሲሆን ቤታቸው እንዲፈርሰ የተደረገውም “ነዋሪዎቹ ወዴት ነው የሚኖሩት፣ ሕጻናት አረጋዉያን የት ነው የሚገቡት ” በሚል አስቀድሞ ታስቦበት በርጋታ፣ የዜጎችን ሰብአዊ መብት በጠበቀ መልኩ ሳይሆን በጭካኔ ነበር።
“ዜጎች የቤት እቃቸውን እንኳን መከወን አልቻሉም። መኪና የሚገባበትን በዶዘር፣ መኪና የማይገባበትን ደግሞ በርካታ ፖሊስ፣ ደንብ አስከባሪ የሚሉት ተሰልፎ አፍርሶታል ሲሉ ተፈናቃዮቹ በስልክ ገልፀውልኛል። በወቅቱ በርካታ የጭስ ቦንብም በዜጎች ላይ ተወርውሯል። በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስትያን ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ” ሲል የጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ሲጦምር፣ ” ኮልፌ ካራ ቆራ አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጎች ናቸው። ማስጠንቀቂያ በተሰጣቸው ሳምንት እንኳ ሳይሞላ፣ ቤታቸውን በኃይል አፍርሰው አባርረዋቸዋል። ተፈናቃዮቹ በቅዱስ ፋኑኤል ቤተክርስትያን ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን አብዛኛዎቹ አማራዎች እና የደቡብ ክልል ተወላጆች መሆናቸው ተገልፆአል።” ሲል ደግሞ ጦማሪ ራስ አስጠራው ከበደ በአዲስ አበባ በአ=ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስተዳደር እየተፈጸመ ያለውን ግፍ አስፍሯል።
ኢንጂነሩ በባለሃብቶች ለበርካታ አመታት ጥቅም ላይ ሳይወሉ ታጥረው የተያዙ በርካታ መሬቶች የከተማዋ አስተዳደር እንደገና እንዲይዝ ማድረጋቸው ይታወቃል። እነዚህ መሬቶችን የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለመጥቀም ሳይሆን ፣ የአዲስ አበባ ዲሞግራፊ ለመቀየር በታሰበና በታቀደ መልኩ ለማደላደል ውስጥ ውስጡን እየሰሩ እንደሆነ የሚነገርላቸው ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፣ በተለይም ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከአዲስ አበባ አስተዳደር እንድትርቅ ከተደረገችበት ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ አስተዳደር ፈላጭ ቆራጭ ንጉስ በመሆን፣ ተጠያቂነታ ግልጽነት የጎደለው አስተዳደር በማስፈን በኦህዴድ/ኦዴፓ የተሾሙበትን አላማ በትጋት እያስፈጸሙ መሆናቸው የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ።
ዶ/ር አብይ አህመድ በልማት ስም ዜጎች እንደማይፈናቀሉ፣ለባለ ሃብቶች መሬት ሲሰጥ በዋናነት በቢታው የሚኖረውን ማህበረሰብ በጠቀመ መልኩ እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ህኖም የኦህዴድ/ኦዴፓው ኢንጂነር ታከለ ኡማ ትላንት ሕወሃቶች ሲያደርጉ እንደበረው አሁንም በግፍና በጭካኔ የዜጎችን ቤት እያፈረሱ፣ ሕጻናትና አረጋዉያንን ሜዳ ላይ መጣላቸው በአገራችን መጣ የተባለው ለውጥ የላይ ላዩን እንጂ መሰረታዊ ለዉጥ ላለመሆኑ አንድ ምሳሌ ነው።
ከዚህ በታች የምታዩት፣ ኮልፌ ካራ ቆራ አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጎች ናቸው። ተፈናቃዮችን ለማፈናቀል ፖሊስ የጭስ ቦንብ የወረወረ ሲሆን በፎቶው የሚታዩት ኮዳ መሳይ ቁሳቁሶችም የጭስ ቦንብ እንደሆኑ ተገልፆአል።

