
ከአንድ አመት በፊት በደራ ጉዳይ ሰፋ ያሉ ጦማሮች ለቅቄ ነበር። በተለይም በኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰባት ላይ የሚደርሰው በደል፣ አፓርታይዳዊ ተጽኖና አድልዎ እንደማያዋጣና አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሳይሆኑ ሁሉም ዜጎች እኩል የሚታዩበት ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አጠንክሬ ለረጅም ጊዜ ተከራክሪያለሁ።
በተለይም ኦሮሞና አማራ የተደባለቀ፣ ለዘመናት አብሮ የኖረ በመሆኑ፣ ኦሮሞንና አማራን በክልል መለየት መዘዙ በጣም የከፋ እንደመሆነ በማሳሰብ ፣ በተለይም ኦሮሞዉም አማራዉም እኩል የሚታዩበት፣ ኦሮምኛና አማርኛ የስራ ቋንቋ የተደረጉበት ሸዋ የሚባለ የፌዴራል መስተዳደር እንዲኖር ክፊት አድርጊያለሁ።የአማራዉና የኦሮሞዉን መተሳሰር ዶ/ር አብይ “አማራና ኦሮሞው ሰርገኛ ጤፍ ናቸው” በማለት፣ አቶ ገዱ ደግሞ “አማራና ኦሮሞ ሰምና ፈትል ናቸው” በማለት ነበር ለማሳየት የሞከሩት። አሁንም አቶ ገዱን በመጥቀስ “ኢትዮጵያ ውስጥ በደንብ ቢጠና የአማራና የኦሮሞን ያህል የተቀላቀለ ህዝብ የለም” ።
ከአመት በፊት በጦመርኩት፡
“በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ደራ ውስጥ የተወለደ አማራ ገበሬ ክልሉ ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ ፍርድ ቤት ለመሔድ የአማርኛ ማመልከቻውን፣ ደረሰኝ ወዘተ በኦሮምኛ አስተርጉሞ መቅረብ አለበት፡፡ በዚህ መልኩ ገበሬው ለብጣሽ ሪሲት ሳይቀር መቶ ብር ወይም ከዚያ በላይ አውጥቶ ያስተረጉማል፡፡ ብዙ ኢንተርፕራይዞችም የአማርኛ ደብዳቤን በማስርጎም ሥራ የደሃ ገበሬዎችን ሀብት ይዘርፋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት 20 ወይም 30 ገጽ ያለው አቤቱታ ለማስተርጎም ብዙ ሺህ ብሮች ስለሚያስፈልግ ከፍትኅ ሥርዓቱ እንዲገለሉ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ በመሠረቱ እንኳንስ ትንሽ የማይባሉ ዜጎች ያሉበት አካባቢ ሆኖ አንድ ሰውም ቢሆን በራሱ ቋንቋ ፍትኅ ማግኘት የሚያስችል ሥርዓት መኖር
