በስብዕናቸው ከፍ ያሉ ናቸው ምናልባት ተጋነነ ካልተባለ እንደ ለማ አይነት brilliant leader በክልሉ ተፈጥሮ አያውቅም ቢባል ማጋነን አይሆንም።

የሳቸው ስራ ምናልባት ዛሬ ላይ በስህተት ተገፍተው ተገፍተው እንደተለመደው ለውጥን የማጨንገፍ የአገሪቱ አባዜ አዙሪት ውስጥ ከተገባ ደንዳና ልብ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ለድጋሜ ስቃይ መዘጋጀት ግድ ይለዋል።

በኦሮምያ ክልል ከዛሬ ሰባት ወራት በፊት አንድ ፅሁፍ ፅፌ ነበር ትንቢት ይመስል ዛሬ ቃሉ ወደ እውነትነት እየተቀየረ ይመስላል

” ለውጡ በሁለት መልኩ አየዋለሁ የለማ መገርሳን ትክክለኛ አመራር የተቀበሉት እንዳሉ ሁሉ በኦሮምያ ምድር ከጥቂት ጊዜያት በሁዋላ ሌላ ግራ ክንፍ ይነሳል ያም አቅጣጫው ከባድ ይሆናል ኦሮምያ እነዚህን ከተከተለች እና ለማን ከስልጣን ካወረደች ሶስቱ የመከራ ጊዜያት ይጀምራሉ” ብየ ነበር በወቅቱ የዛን ጊዜ የስድብ ናዳ አላዋቂያን አወረዱ።

Wise people always see the future with clear path እንደሚባለው ታይቶን ነበር።

ኦሮምያ ክልል የለማን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በእጅጉ በሀያ ሰባት አመታት አይታ የማታውቀውን ብዙ ለውጥ አየች ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ስራ ያዙ በክልሉ በርካታ መሰረተ ልማቶች ተዘረጉ የክልሉ ተሰሚነት ጨመረ።

ሆኖም ግራዘመሞቹ ፅንፍ እየፈጠሩ ከሰማይ መና ይወርድ ይመስል ከድሀ አገራቸው አቅም አኩዋያ የማይቻለው ይሁን ማለት ጀመሩ።

ለማ መገርሳን ወደ ተጠያቂነት ጎራ መመደብ ያዙ ለማ ግን የክልሉን ፀጥታ ክፍተት ለመሸፈን ባለፈው ወር ከስድስት ሺ በላይ የፀጥታ እካላትን አሰልጥነው አሰማሩ ። ክልሉ በያቅጣጫው ብዙ ችግር የገጠመው በመሆኑ ሁሉም እንደፈለገው በአንድ ቀን ለውጥ አይመጣም።

ዛሬ ላይ ሰላማዊ ሰልፎች በክልሉ ከመደረጋቸው በላይ የተለያዩ የአለም ሚዲያወች የሰልፉን እንደምታ በሚገባ እያዩት ይገኛሉ።

እነማን አሉበት የሚለውን በሁለት ምላስ የሚተውኑትን ህዝብ ይመልስ ።

እነ ጃዋር መሀመድ ዳያስፖራ ሆነው ትግሉን እንደመሩት ሁሉ መሬት ላይ ያዩት እውነታ ግን በላፕቶፕ ቁጭ ብሎ ጃስ ብሎ እንደማዝመት ቀላል አልሆነም ክልሉ በርካታ ፍላጎቶች የታጨቁበት ከብዙ አቅጣጫ የታጠረ ብቻ ሳይሆን የትናንቱን የጭቆና ቀንበር ለመላቀቅ መስዋት የሆነው ህዝብ ትናንት እንዳዩት ውስጥ ብዙ ልዩነት አለው ።

እናም እነጃዋር ዛሬ ዳር ተመልካች መስለው አይደለም ለማ በአጭር ጊዜ ይቅርና እነሱ እና ህዝቡ እጅ እና ጉዋንት ሆነው ችግሩን ለመፍታት የአመታት ዳገት መውጣትን ይጠይቃል ።

እንደተለመደው ዳር ቆሞ ጃዋር ዛሬ የህዝቡ ጥያቄ ይሄ ነው ሲል ፅፉዋል ያን ጥያቄ ለማ መገርሳም ያውቀዋል ለማ አስቀድሞ ተናግሮት ነበር እንታገል ሲልም ጭምር ችግሩ እንደነ ጃንዋር በፅሁፍ በጥያቄ በወሬ የሚፈታ ሳይሆን በከፍተኛ ጥረት እና በህዝብ ትብብር የሚፈታ እንጅ።

ጃዋር እንደ ዳያስፖራ ዛሬ ላይ ማውራት አይችልም ችሎታ አለኝ ብሎ አስታርቃለሁ ብሎ የሞከረው እሱ ከስፍራው ሳይወጣ ደም ፈሱዋል ትናንት በላፕቶፕ የሚፅፈው ዛሬ መሬት ላይ ልተግብር ሲል እራሱ ሞክሮት ከሽፎበታል።

የህዝብን ጥያቄ ከህዝብ ጋር ለመመለስ መሞከር እንጅ እራሱ ሞክሮ ያልቻለውን ጥያቄ በማንሳት የህዝብን ብሶት በቀላሉ ህልም የመሰሉት ሲጠይቃቸው በትግባር ግን ዳገት የሆኑትን ችግሮች አግዝፎ በማንሳት ኦሮምያን የጦር አውድማ ለማድረግ መክፈት ልክ አይመጣም።

ዛሬ ላይ ብዙ እየለፉ በስንት ችግር ተከበው የሚጥሩት ለማ መገርሳ በእጅጉ አዝነው ይህን እንደተናገሩ ተስምቱዋል።

“ኦነግ እኔን ካልፈለገኝ ስልጣን መልቀቂያ አስገባለሁ!”

እኔ ደስተኛ የምሆነው የኦሮሞ ህዝብን ጨምሮ ፣ ለኦሮሞ ህዝብ የሚቆረቆሩ ተፎካካሪ የውስጥ ፓርቲዎች እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ህዝብ ደስተኛ ሲሆን ብቻ ነው”

“የምንደክመው ለብዙሃኑ እንጅ ለግል ጥቅምና ልዕልና አይደለም”

በሚል ትልቅ ስጋት ያዘለን ንግግር ተናግረዋል ።

እኔም ደግሜ ልናገር ጥያቄን መቆስቆስ ቀላል ነው በተግባር ግን ሁሉም ሲፈተን እያየነው ነው ሲከሽፍበት።

ኦነግ የጀመረው ስራ የውስጥ ግፊት እርስ በእርስ ንትርክ ከጠቀመ ስልጣኑን ለኦነግ ስጡት አይደለም የለማን ያህል ክልሉን ሊጠቅም ይቅርና የጦር ቀጠና አርጎት ቁጭ ይላል ምክንያቱም ኦሮምያ በሁለት ጎራ ተከፍላለች ኦነግ አርፎ ይቀመጥ በሚሉ እና ኦነግ ይቀጥል በሚሉ።

ውስጥ ገብቶ እራሱ እፈታዋለሁ ብሎ ሲውተረተር ገና እግሩ ሳይለቅ ባዶ የሆነበት ጃዋር ዛሬም ጥያቄን በማንሳት እራሱ ያልቻለውን በለበጣ ለማን የደገፈ በመምሰል ለማ መገርሳን በግልፅ አስነቅፉዋል።

ስልጣኑን ኦሮምያ ተሳስታ ህዝቡ ተታሎ ኦሮምያ ለጃዋር ትስጠው ገና በወሩ በኦሮምያ ምን ይፈጠራል ትንቢት ተንባይ መሆን አይጠበቅም ። አይተነዋል እችላለሁ ብሎ ይባስ ህዝብ በሱ ምክንያት ሲበጠበጥ። ጃዋር ስልጣን አልፈልግም በሚለው ቁማሩ ዳር ሆኖ ማቀጣጠልን የመረጠው ስልጣን ቢሰጠው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው. ዛሬ በእንግሊዘኛ የፃፈው ፅሁፍ ሶስት እንደምታ አለው ለገባው ሰው ።

ይችን ማስታወሻ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከሰባት ወር በፊት እንዳልኩት አስታውሱ

ኦሮምያ ለማ መገርሳን ካጣች ለከባዱ ማዕበል ትዘጋጅ ማን ዳር ሆኖ ይህን እንደለኮሰ ጠንቅቀን እናውቃለን። ለብዙወች ይህ ፅሁፍ ላይገባቸው ይችላል ከሰባት ወር በፊትም ስድብን ነበር የመረጡት መልሱ ግን ዛሬ እውን ሆኖዋል።

እንደኔ አሁንም አረፈደም ኦሮምያ ከታላቁ መሪዋ ከኦቦ ለማ መገርሳ ጋር ወደፊት ያለውን ችግር በመጋፈጥ ብትጉዋዝ ችግሩን በህዝብ ብርታት መፍታት ይቻላል።

ሰላም

@ልጅ አቤል