December 7 at 3:11 PM


ሸህ ሁሴን ጅብሪል ስለ ሰሜኖች የተናገሩት! !!!!


ሃያቱ የቆየ ያያል ብዙ ገና፤
ከጅማ የሚዘልቅ አንድ ጎበዝ ጀግና ፤
ጦቢያ ላይ ይሾማል ሌቦቹ ያልቁና ፤
ባይሆን ለትንሽ ቀን ፤ አለበት ፈተና ።
ውሻና ጅቦቹ ስጋ የለመዱ ፤
ይበጠብጡታል በሬ እያስወለዱ ።
ተምኒሊክ ሃገር ከርመው ሙጭቅና ፤
ያገሬውን ጎጆ ትዳር ያፈርሱና ፤
በስተመጨረሻ ሲደናገራቸው ፤
ሰሜን ይገባሉ ከነልጅ ልጃቸው ።
አየ በዚያ ሰሞን ያለ ክፋታቸው ፤
ሰሜን ተቀምጠው ፤ ከነተንኮላቸው ፤
ደቡብ ላይ ይነዳል የሸር እሳታቸው ።
ሌባና ቀማኛ አይከርምም እንጦጦ ፤
መቀሌ ይገባል ሽሜጥ ፈርጥጦ ።
መቀሌ ላይ ሆነው እሳት እየሞቁ ፤
እንዴት ሆነ ሸዋ ብለው ሲጠይቁ ፤
ጥጋብ ነው ሲሏቸው ደንግጠው ወደቁ ።
አወይ በዚያ ሰሞን ምኑ ይነገራል ፤
እንኳን ሌባውና ፤
የሌባ አማችቻ ይደነጋገራል ።
የሌባ አይነ ደረቅ ይመጣሉ ገና ፤
በትንሽ ትልቁ ተረግመዋልና ፤
ብለው ይምላሉ የሞተውን ደህና ።
ሸዋ አልጋው ሲጠና ምድሩ ሲደላደል ፤
ከራስ ስዩም ግዛት ይቀጥላል በደል ።
መገን በያ ሰሞን ፤
በራስ ስዩም ግዛት ፤ይበዛል ሰልፈኛ ፤
ብሎ የሚፈክር ፤
ጦቢያን አንወዳትም አንፈልግም እኛ ፤
በሌባና በአባይ ፤
ሲነገር ይከርማል የጅል አማርኛ ።
አኡዙቢላሂ ፤
መቼም የዚያን ሰሞን ፤ ይታያል አይን አውጣ ፤
ሌባየ አይገልመጥ ፤
ሌባየ አይነካ ብሎ የሚመጣ ።
ሰልፍ ይበዛበታል፤
አገሩ ያን ጊዜ ፤ በተርታ በተርታ ፤
ይታያል ሰሜን ላይ ወረርሽኝ በሽታ ፤
ሌባ ልቀቅ የሚል በደህና ሰው ፈንታ ።
የሰሜኖች ነገር ፤ ታይቶናል ከሩቁ ፤
የጅማን ሰው ወንበር፤ አስበው ሊሰርቁ ፤
የራያ ድካውን ፤ ድብ ሲነቀንቁ ፤
አልሃምዱሊላሂ ፤
መብረቅ ተጭኗቸው ዘፍ ብለው ወደቁ ።
እርግጥ ይለፋሉ በሰልፍ ዳንኪራ ፤
መልሰው አይበሉት ያጡትን እንጀራ ፤
ጦቢያ እድለኛ ናት ፤
እንጀራዋ ያምራል ከጅማው ልጅ ጋራ ።
ታዲያ በዚያ ሰሞን ፤
በአለም ይነገራል ፤ የጀሊሉ ስራ ፤
እንጀራው ተጋግሮ፤
ብርዙ ተጥሎ ፤ እንጦጦ ተራራ ፤
ወንድሜ ወንድሜ ፤እየተባባለ ስሙን እየጠራ ፤
ሲጎራረስ ያድራል ፤ ወረሞና አማራ ።
ይቀጥላል…….
መገን ሸህ ሁሴን ጅብሪል….ወሎ ታምረኛው አገር….. ሰማዩ ተከፍቶ የሚነበብበት የደጋጎቹ ቀዬ…,መገን እኔ…