12/15/2018

አቶ አረፈ ወልደስላሴ በ1973 ነበር ከተወለዱበት መንደር እሳቸውን ጨምሮ15 ሰዎች ከሰፈራቸው ተወስደው የት እንደደረሱ ሳይታወቅ ይሄው ድፍን 38 አመት አለፋቸው ህወሓት ገና ስማቸው ተሓህት እያለ ደርግ በማይቆጣጠረው በእነሱ አባባል ሐራ በአማርኛው ነፃ መሬት በሚሉት አከባቢ ኢትዮጵዊነት ይሰብካሉ የፊውዳል አስተሳሰብ ያራምዳሉ የአማራ ተገዢ ናቸው በማለት ብዙ የትግራይ ተወላጆችን ደብዛቸውን አጥፍተዋል ከእነዚህም አንዱ የጥላሁን አባት ናቸው።

አቶ አረፈ ወልደስላሴ በአከባቢያቸው ጥሩ ተሰሚነት የነበራቸው እንዲሁም አስመራ ቀደም ብለው እንደኖሩና ባለቤታቸውም ያገራቸው ልጅ እዛው አስመራ ተገናኝተው በሰርግ ከተጋቡ በሃላ ወደ ትውልድ መንደራቸው መጥተው ልጆች ወልደው በግብርና ተሰማርተው እየኖሩ ሳለ ህወሓት በእዛ አከባቢ ሲንቀሳቀስ አይደለም ፊትለፊት ለተቃወማቸው በሀሜት ስማቸው ከተነሳና ወሬው እነሱ ጋር ከደረሰ ህይወቱ አደጋ ላይ ትወድቃለች የጥላሁን አባት ተናገሩት ተብሎ እንዲህ እንዲጠፉ ያደረጋቸው ቃል ይሄ ነበር

“ልጅ የሚያስተዳድረው አገርና ፍየል የገባበት ማሳ እርባና የለውም”

አዎ የዛሬ አዛውንት ወንበዴዎች በወቅቱ ልጅች ማለትም ወጣቶች ስለነበሩ ነው አቶ አረፈ ይህንን ያሉት የሚገርመው ግን የእነ ጥላሁን ቤተሰብ አባት ብቻ አይደለም ያጣው አንድ እህታቸውም የአባትዋ እንደወጡ መቅረት በተለይ ሲወሰዱ ህዝብ በተሰበሰበበት ቤተክርስቲያን ውስጥ ነበርና ሁሌ በሀዘን ልብ እንደተሰበረ መኖርን በመጥላት አሳዛኙ ሁኔታ በእራስዋ ላይ በመፍረድ በድስት ውሀ ሙሉ በማፍላት እራስዋ ላይ በመድፋት ለተወሰኑ ቀናት ተጉድታ በአልጋ ብትቆይም ላትመለስ እቺን አለም ተሰናበታች።

ውድ ኢትዮጵያውያን ህወሓት ከ1983 ጀምሮ ለ27 አመታት እሱ በሚመራውና እራሱ ባዋቀረው ህወሓት ኢህአዴግ በመላ አገራችን ከመሀል አገር ተባባሪዎቹ ጋር በመሆን ይህንን የምንሰማው ዘግናኝ ወንጀል በቅድሚያ የተለማመደው በሺዎች በሚቆጠሩ ህዝብ ትግራይ ላይ ነበር።

ከ1967 እስከ 1981በመላ ትግራይ ህዝብ ላይ ከእዛ በሃላም እንደ መሀል አገሩ እግሩ በረገጠበት ሁሉ ለመስማት የሚዘገንኑ ይጭካኔ ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱ የአደባባይ ምስጢር ነው።

ብዙ የተጋነነ ባይሆንም አረና እና ደምሂት ተብለው በስውር የት እንደገቡ የማይታወቁ አሉ በካድሬዎቻቸው አማካይነት በድንጋይ ያስፈነከቷቸውን በገጀራ ያስቆረጧቸውን ቤት ይቁጠራቸው።

በዚህ ሰአት እንኳን በመላ አገሪቱ የፖለቲካ እስረኞች ሲፈቱ ትግራይ ውስጥ ግን ከእድሜ ልክ እስከ 17 አመታት የተፈረደባቸው የአረና እስረኞች ያሉባት ብቸኞ ክልል ናት።