December 15, 2018

Source: https://mereja.com/amharic/v2/75244

የደህንነት መሥሪያ ቤት የኅይል አሰላለፍ እና “የወያኔ ኅይል”

(በረራ ጋዜጣ_ ታህሳስ 4/2011 ዓም)
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት 7 መምሪያዎች አሉት። እነሱም፣ የውስጥ ደህንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ፣ የውጭ ደህንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ፣ የቴክኒክ ደህንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ፣ የጥበቃ ዋና መምሪያ፣ የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ፣ የስደተኞችና ስደት ተመላሾች ዋና መምሪያ እና የክንፈ የብሔራዊ ደህንነት ማሰልጠኛ ተቋም ናቸው።
በደህንነት መሥሪያ ቤቱ ሁለት ኅይሎች አሉ። አንደኛው “የወያኔ ኅይል” የሚባለውና መሥሪያ ቤቱን የተቆጣጠረው ሲሆን ሁለተኛውና በጣም ጥቂት የሆነው ኅይል “የኢትዮጵያ ኅይል” ተብሎ የሚጠራው ነው።
የወያኔ ኅይል የተሰኘው አካል የደህንነት መሥሪያ ቤቱን ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱን ተቆጣጥሮ ያሻውን ሲያደርግ የኖረ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈፀሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ማፈናቀሎች፣ የዘረፋና የሌብነት ተግባር በቀዳሚነት የተሳተፈ ነው። የወያኔ ኅይል የሚባለው የመጀመርያ ዓላማው ትህነግ/ህወሓትን ስልጣን ላይ ማቆየት፣ የራሱን ብልፅግና እና ሀብት ማካበት ሲሆን ለዚህም ከትግራይ ልጆች ባሻገር ሌሎችንም በጥቅም ገዝቶ ወደ ጎራው ያስገባ ኃይል ነው።
በሌላ በኩል፣ “የኢትዮጵያ ኃይል” የሚባል በቁጥር ጥቂት ኅይል ያለ ሲሆን፣ የሁለቱ ክፍፍል ከ2008 እና 2009 ዓ.ም. በኋላ እየጎላ መጥቷል። የኢትዮጵያ ኅይል ተብሎ የሚጠራው ደህንነት መሥሪያ ቤቱ ለሀገርና ለሕዝብ መሥራት አለበት የሚል አቋም የሚያንፀባርቅ ሲሆን ከዘረፋ፣ ከሽብር ወንጀልና ሌሎችኝ ጉዳዮች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በ”ወያኔው ኅይል” የተባረሩ፣ የተገደሉ፣ የተሰወሩ የኢትዮጵያ ኅይል አባላት ይገኙበታል።
እነ ጌታቸው አሰፋ፣ በእነ አማኑኤል ኪሮስ፣ ያሬድ ዘሪሁን፣ መድህኔ ታደሰ፣ አደራጀው፣ ዶ/ር