December 17, 2018e

የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ከVOA ትግርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ከተናገርዋቸው አንዳንድ ነጥቦች

👉

“ሕገ መንግሥቱ ይከበር፣ ብሄር ተኮር ጥቃት ይቁም” በሚል ባለፈው ቅዳሜ በመቀሌ ከተማ የተደረገውን ሰፊ ሰላማዊ ሰልፍ ለውጡን በማይደግፈው ቡድን የተደራጀ እና የአስገዳጅ ሰልፍ ነበር::”

👉

“የፍትህ ሰቆቃ በሚል የቀረበውን ዘጋቢ ፊልም መቅረብ ያለበት ቢሆንም በአዘገጃጀቱ ላይ አቀራረቡ ላይ ጥሩ አልነበረም።”

👉

“በሰልፋ ላይ የታዩት መፈክሮች የህዝቡን ስሜት የሚያንጸባርቁ አልነበሩም። ለምሳሌ በስፋት ከታዩት መፈክሮች መካከል “ሕገ መንግስቱ ይከበር” የሚል ነው። ሕገ መንገስቱ ይከበር ማለት ምን ማለት ነው ብለን ስንጠይቅ ግን “ላለፋት 27 አመታት የነበረውን ሁኔታ ይቀጥል” ይህ ደግሞ የአፋኝ አገዛዙ ስርአት ይቀጥል ማለት ነው ይህ ደግሞ የህዝቡ ፍላጎት አይደለም። ስለዚህ ሰልፉ ለውጡን በማይደግፉ የህወሐት ጉጅሌ የተደራጀ የተቃውሞ ሰልፍ ነው።”

👉

”ሰልፉ ዶ/ር አብይን በመደገፍ የተደረገ ሰልፍ ሳይሆን ዶ/ር አብይን በመቃወም የተደረገ ሰልፍ ነበር። ሰልፋ ለውጥ በማይፈልገው ጉጅሌ የተደረገ ነው። እነዚህ ለውጡን የማይደግፉ አካላት “ሕገ መንግስቱ ይከበር” በሚል ብዙ ነገር ነው እያደረጉ ያሉት። ሐቁ ግን ሕገመንግስቱን ሲጥሱ የነበሩ እነሱ ናቸው። ለምሳሌ ፍርድቤቱ ነፃ ብሎ የፈረደባቸው ሰዎች ያስሩ ነበር። ህገ መንግስቱን ይጥሱ የነበሩ እነሱ ሆነው ሳለ ዛሬ ላይ ሕገመንግሥቱን ይከበር ሲሉ ሸፍጥ ክርክር መሆኑን ግልፅ ነው። ”

👉

”እርግጥ ነው ብሄር ተኮር ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው።በተለያዩ ቦታዎች በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው። ይህ ደግሞ መደረግ የሌለበት እና የተሳሳተ አካሄድ ነው። ነገር ግን እነዚህ ብሄር ተኮር ጥቃቶች ማን ነው እያካሄደው ያለው ብለን ስንጠይቅ ግን እነዛ በየአካባቢው ያሉ ጠባብ አገራዊ ምልከታ ያላቸው ሰዎች ናቸው። ይህ ብሄር ተኮር ጥቃትስ መቼ ተጀመረ ብለን ስንጠይቅ ደግሞ…ምናልባት ኢህአዴግ ሲከተለው የነበረው ፖሊሲ ያፈራው የዘረኝነት አስተሳሰብ ነው። እርግጥ ነው ብሄር ተኮር ጥቃቱ በትግራይ ተወላጆች ላይ የተወሰነ አይደለም።በሌሎች ብሄሮች ላይም እየተፈፀመ ነው። መነሻው (የብሄር ተኮር ጥቃቶች) ግን የነበረውን የኢህአዴግ ስርአት ነው።”

👉

”እየታሰሩ ያሉ ሰዎች ከትግራይ ብቻ አይደሉም።ከሁሉም ብሄሮች በዘረፉ ላይ የተሳተፉ፣ ስልጣናቸውን ያለ አግባብ የተጠቀሙ እና ሰብአዊ መብት የጣሱ ናቸው እየታሰሩ ያሉ። ይህ በትግራዎት ላይ ብቻ ያነጣጠረ አይደለም። በትግራዎት ብቻ ላይ ያነጣጠረ እስር ተደርጎ የሚቀርበው ነገር ከእውነታው የራቀ ነው። እነማን እየተሳሩ እንደሆነ ዝርዝር መረጃ ለህዝቡ በማቅረብ ላይ በመገናኛ ብዙሐን በኩል ክፍተት ይታያል። በትክክል እየቀረበ አይደለም።”

ጠቅላይ ሚነስትር አብይ አሕመድ እንዳሉት የትግራይ ህዝብ አልተጠቀመም። የተጠቀሙት እነዛ ጥቂቶቹ ጉጅሌ ናቸው።ልጆቻቸውን ወደ ውጭ አገር ልከው የሚያስተምሩ የሚያሳክሙ እነዛ ኖሮአቸው በውጭ አገር የመሰረቱ ናቸው የተቀሙት። እነዚህ ደግሞ በአመራር ላይ የነበሩ ጥቂቶች እና የነሱን ተከታዮች የሆኑ ውሾች ናቸው። የትግራይ ህዝብ ግን ከUSAID የስንዴ እርዳታ ያልተላቀቀ ህዝብ ነው። በሴፍቲኔት እርዳታ ህይወቱን እየመራን ያለ ህዝብ ነው። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ አልለማም 85 ፐርሰንቱ ነው በድህነት ችግር ውስጥ ነው ያለው።”

👉

“ህገ መንግስቱ ይከበር ከተባለ የፌዴራሉ መንግስት በክልላዊው መንግስቱ ላይ የበላይ ስለሆነ እነዛ በአገር ደረጃ አንድ የዘረፈ፣ ጥፋት የፈፀመ እና ሰብአዊ መብት የጣሰ ሰው ካለ የሚመለከተው የፌዴራሉ መንግስት ነው።በመሆኑም የፌዴራሉ መንግሥት አስፈላጊ የሆነ እርምጃ መውሰድ አለበት።”

ውይይቱን ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑ

https://tigrigna.voanews.com/a/ቃለ-መጠይቕ-ምስ-ኣቦ-መንበር-ደሞክራሲዊ-ምትሕብባር-ትግራይ-ዶ-ር-ኣረጋዊ-በርሀ-/4701007.html