December 16, 2018

ከብርሃነመስቀል አበበ ሰኚ

አንዳንድ በትናንትናው ጉባኤ ያልተሳተፉ ወዳጆቼ የስብሰባውን ጭብጥ እንዲገልፅላቸው ደገግመው ጠይቀውኛል።

ለመሰል ጠያቂዎች በጉዳዩ ላይ የተሰራ ወጥ ዜና ወይም የፕሬስ መግለጫ ስላላየሁኝ የነበረኝን ግንዛቤ እንደሚከተለው አቅርብያለሁ። ሌሎች የስብሰባው ተሳታፊዎች ልጨምሩበት ይችላሉ።

ጉባኤው የተከሄደው በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ሲሆን ከሁሉም የኦሮሚያ አከባቢዎች የተወከሉ ከሶስት ሺህ በላይ የኦሮሞ አገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ሙሁራን እና ወጣቶች የተሳተፉበት የሙሉ ቀን ጉባኤ ነበር።

ስብሰባው የተመራው በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ እና በክቡር ፕሬዚደንት ለማ መገርሳ ሲሆን አቶ ሽመልስ አብዲሳ(የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ) የመነሻ ፁሁፍ አቅርበዋል። ጉባኤው የተካሄደው በኦሮሚኛ ቋንቋ ነው።

የስብሰባው እና ውይይቱ ዋና ጭብጥ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚመራው የኢትዮጵያ የለውጥ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ የኦሮሞ ህዝብ ፖላቲካ በኢትዮጵያ የዳር ፖላቲካ መሆኑ ቀርቶ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍርካ ቀንድ ፖላቲካ ወደ መሃል ፖላቲካ መሸጋገሩ የተበሰረበት ትልቅ ታሪካዊ እና በአይነቱ የመጀመሪያው ጉባኤ ነው።

ጉባኤውን ታሪካዊ ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ ከዚህ በኋላ የኦሮሞ ፖላቲካ ለኢትዮጵያ ስጋት፣ የኢትዮጵያ ፖላቲካ ለኦሮሞ ህዝብ ስጋት የሆነበት ዘመን ማብቃቱን እና የዳር ፖላቲካ የነበረው የኦሮሞ የመገንጠል ፖላቲካ ወደ ኢትዮጵያ የመሃል ፖለቲካ መሸጋገሩ፣ እንድሁም የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄዎች የሚሆኑበት እና የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄዎች ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎች ሆነው የጋራ ችግሮቻችንን በጋራ ፈተን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍርካ ቀንድን የሁሉም የአከባቢው አገሮች እና ህዝቦች የጋራ ቤት ለማድረግ በአዲስ ራዕይ እና በአዲስ ዕይታ እየተሰራ መሆኑ ተገልፇል። ይህ አዲስ ራዕይ እና እይታ ለኦሮሞም ሆነ ለመለው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅም ታላቅ አገርዊ ራዕይ መሆኑ ተበስሯል።

ከዚህ አንፃር የኦሮሞ ህዝብ ፖላቲካ የኦሮሞ ህዝብ ውዝፍ የዘመናት ችግሮችንም ሆነ የኢትዮጵያን እንድሁም የአፍርካ ቀንድን ውስብስብ የጋራ ችግሮችን ከሌሎቹ ህዝቦች እና አገራት ጋር በመሆን በጋራ ወደ ሚፈታበት በአይነቱም ሆነ በይዘቱ የተለየ የፖላቲካ ምዕራፍ ውስጥ መግባቱ በመሪዎቹ ተሰምሮበታል። የአፍርካ ቀንድ አከባቢ ህዝቦች የፖላቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ችግሮች የተቆራኙ እና በተናጥል የማይፈቱ ነገር ግን በቀላሉ ተደጋጋፊ እና ተመጋጋቢ የጋራ መፍትሄዎችን ማግኘት እንደሚችሉ በመሪዎቹ በሰፊው ተብራርቷል።

የኦሮሞ ሙሁራን፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የፖላቲካ መሪዎች፣ ወጣቶች እና መላው ህዝብ እይታውን እና ትከሻውን አስፍቶ፣ የተሻለ እውቀት ጥበብ እና ማስተዋል ሰንቆ፣ ሆደ ሰፊና ታጋሽ ሆኖ ይህን አገራዊ እና ክፍለ አጉራዊ ራዕይ ከግብ ለማድረስ ከለውጥ መንግስቱ መሪዎች ጎን እንዲቆሙም ጥሪ ቀርቧል።

በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚመራው የለውጥ መንግስት ውዝፍ የኦሮሞ ህዝብ ችግሮችን፣ ውዝፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግሮችን እና ውዝፍ የአፍርካ ቀንድ ችግሮችን ሁሉንም ባሳተፈ እና ሪዕታዊ በሆነ መልኩ በየደረጃው ለመፍታት የሚያስችል ስትራቴጂ አውጥቶ እና የለውጥ መሪዎችን አደራጅቶ እየሰራ መሆኑ በስፋት የተመለከተ ሲሆን ሁሉም ችግሮች በየደረጃው እልባት እንደሚያገኙ የኦሮሞ ህዝብም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብ ማድረግ ከሁሉም የጉባኤው ተሳታፊዎች የሚጠበቅ ኃላፊነትም፣ግዴታም እንደሆነ መሪዎቹ አፅኖኦት ሰጥተው አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል የለውጡ ተቃዋሚዎች እና የኦሮሞ ህዝብ ጠላቶች አሁንም የኦሮሞን ህዝብ በፖላቲካ አስተሳሰብ፣ በሃይማኖት፣ እና በአከባቢ በመከፋፈል ኦሮሞን በኦሮሞ ጠልፎ ለመጣል፣ የኦሮሞን ህዝብ ከፋፍሎ ለማዳከም፣ ከተቻለም የኦሮሞን ህዝብ በአከባቢ እና በሃይማኖት ከፋፈሎ ለማባላት እንዲሁም የኦሮሞ ችግር ራሱ ኦሮሞ እንደሆነ በማስመሰል በወለጋ፣ በጉጂ፣ እና በቦረና አከባቢ ጠላት እየፈጠረ ያለውን ችግር እንደምሳሌ በማንሳት ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። መለው የኦሮሞ ህዝብ እነዚህን የጠላት ውጥኖች እንዲገነዘብ እና እንዲከላከል እንዲሁም ለኦሮሞ የውስጥ ችግሮች የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ሙሁራን እና ወጣቶች መፍትሄ በማፈላለጉም ረገድ በቀጥታ በመሳተፍ የጠላት ኦሮሞን በኦሮሞ ጠልፎ የመጣል እና የማባላት ፖሊሲ እንዲሁም አገር የማፍረስ አጀንዳ እንዲያመክኑ እና እንዲከላከሉ ጥሪ ቀርቧል።

የጉባኤው ተሳታፊዎችም በኦሮሞ የፖላቲካ ድርጅቶች ስም የኦሮሞን ህዝብ በፖላቲካ አስተሳሰብ፣ በሃይማኖት እና በአከባቢ ለመከፋፈል የሚጥሩ የለውጡ እና የኦሮሞ ህዝብ ጠላቶችን ስራ የኦሮሞ ህዝብ ለአንዳፍታ እንደማይታገሳቸው በአንድ ድምፅ ያስተጋቡ ሲሆን እስከ አሁን የተፈጠሩትንም ችግሮች ከመንግስት ጋር በመስራት ለመፍተት ቃል ገብተዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በኢትዮጵያ እና በአፍርከ ቀንድ ሰላም፣ ፍትህ እና እኩልነትን በማስፈን ለሁሉም ነዋሪዎቿ የሚትመች የበለፀገች እና የሰለጠነች ኢትዮጵያን መገንባት ብቻ ሳይሆን የአፍርካ ቀንድን የሁሉም ህዝቦቿ የጋራ ቤት አድርጎ ለመገንባት በለውጥ መሪዎቹ የቀረቡት አገራዊ እና ክፍለ አህጉራዊ ራዕዎችን በመደገፍ ጉባኤው ተጠናቋል። Sponsored by Revcontent